ግሪክ(ያቫን)
ማህደረ ትውስታቸው በሆፍ ሀካርሜል መካነ መቃብር ይገኛል።
ቦታ፦ ግሪክ(ያቫን)
ከሆሎኮስት(ሽዋ) በፊት በ 1938 የነበሩ ይሁዳዊያ፦ 78, 750 ይሁዳዊያን ነበሩ።

በ 1928 ዓ.ም ግሪክ ውስጥ በተደረገው የህዝብ ቆጠራው 72,791 ይሁዳዊያን እንደነበሩ እና ከአገሪቱን ህዝብ ብዛት 1.2% እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ በዚህ አገር የሚገኙ አብዛኛው ይሁዳዊያ ከ (98%) በላይ የሚሆኑ ይሁዳዊያን በከተማ የሚኖሩ ነበሩ። በግሪክ ትልቅ የይሁዳዊያን ህብረተሰብ የነበረባት ከተማ በሳሎኖኪ ከተማ ሲሆን፤ በከተማዋ 55, 250 ይሁዳዊያን ነበር። እንዲሁም በዋና ከተማዋ በአቱና 1,578 ይሁዳዊያን ይኖሩ ነበር። በግሪክ የተደረገው የይሁዳዊያን እልቂት የሚታወሰው እና የሚታወቀ በሰሎኖኪ ይሁዳዊያን ላይ በተደረገው አሰቃቂ ድርጊት ነው። በዝች ከተማ ይኖሩ የነበር ይሁዳዊያን በግምት ከሁለተኛው መቶ ዓ.ዓ በፊት ይኖሩ እንደነበረ እና የአውሮፓ ጥንታዊ የይሁዳዊያን ማህበረሰብ እንደሆኑ ይገለፃል፡፡

ወደ ግሪክ ጦርነቱ የደረሰው በአውሮፓ ከፈነዳ ከአመት በኋላ ነበር። በሰኔ 10 ቀን በ 1940 ዓ.ም የጣሊያኑ ሞሶሎኒ ከሂትለር ጋር ህብረት በመፍጠር፤ ጥቅምት 10 ቀን 1940 ጣሊያን ግርክን በጦር ሀይል ጥቃት አደረሰችባት። ስለዚህም ሞሶሎኒ ለጣሊያን ጦር ሀይል ማለፊያ፤ የግርክን መንግስት ደንበሩን እንዲከፍት አስገደደ። ነገ ግን ግርክ ደንበሯን ለመክፈት ፍቃደኛ እንዳልሆነች ጣሊያናዊያን ሲረዱ፤ ጣሊያኖች ግርክን ጦር ሀይል መጨፍጨፍ ጀመሩ። ግሪካዊያን እስከ መካከለኛው አልባኒያ ድረስ ግሪክን ለወር የመጣውን የጣሊያን ጦር ሀይል አስመለሱት። ሚያዚያ 6 ቀን 1941 ጀርመኖች በቡልጋሪያ እና ዩጎዝላቪያ በኩል በመግባት ግሪክን ወረሩ ፡፡ የእንግሊዝ ጦር ያገሪቱን መወረር እከላከል አልቻለም። እንዲሁም የክሪቲም ደሴትንም እንዳትማርከ ለማድረግ አልቻለም።
በጦርነቱ አማካኝነት ግሪክን ሶስት አገሮች በሶስት የተለያየ ያገሪቱ ክፍል ከባዋት ነበር፦ ጀርመን፣ ጣሊያን እና ቡልጋሪያ ነበሩ። የጀርመን ጦር ሀይል የምስራቅ ታርኪያን፣ የምስርቃ እና መካከለኛ ሜክዶንያን፣ እና የክሪቲም የብስን የዘው ነበር። የዚህ ምክንያት የሜዲትራንያንን ምስራቃዊ ክፍል ለመቆጣጠር በስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ምክንያት ነው ፡፡ ስለዚህ በሳሎኒኪ የሚገኙ ይሁዳዊያን በዚህ ጊዜ በጀርመን ግዛት ስር ነበሩ። ጣሊያኖች የግርክን መካከልኛ ቦታ እና ዋና ከተማ አቱናን እና በምዕራባዊ ጠረፍ ላይ ያሉ ሌሎች ግዛቶችን ጨምሮ የመካከለኛው ግሪክን ክልሎች ተቀበሉ ፡፡ እንዲሁም ቡልጋሪያ የምዕራብ ትሬስ እና የምስራቅ መክዶንያ ግዛቶችን ተቀበሉ። በይፋ ፣ ግሪክ ነፃነቷን እንደቀጠለች እና የትብብሮችን መንግሥት አቋቋመች።
በ 1942 ዓ.ም በቫንዛ በ ተደረገው የስብሰባ ጉባኤ በግሪክ የሚኖሩ ይሁዳዊያን አጠቃላይ 75, 000 ይሁዳዊያን ነበሩ። ይህ ቢሆንም በጦርነቱ የተገደሉት ይሁዳዊያን ከ 90% ደርሷል። በመጀመሪያ ደረጀ ይሁዳዊያን ለምጥፋት በጥበብ በታቀደው "የመጨረሻ መፍትሄ" በሚል ስም፤ በጀርመን ግዛት የሚኖሩ ይሁዳዊያን ተገደሉ። በሁለተኛ ደርጃ ደግሞ የጣሊያን ጦር ሀይል በጀርመን ጦር ሀይል ከተቸነፈ በኋላ፤ በቡልጋሪያ ግዛት የሚገኙት ይሁዳዊያን በሙሉ ሲገደሉ፤ በ 1943 ዓ.ም በጣሊያን ግዛት ውስጥ የነበሩ ይሁዳዊያን እንዲገደሉ ትዕዛዝ ቢወጣም፤ ፍፃሜ ላይ ግን እስከ ከፀዳይ- በጋው ወር 1944 ድረስ ዘገየ።
የጀረመን ጦር ሀይል ወደ ግሪክ ከመጋብቱ በፊት በ 1941 ዓ.ም ዞንድራኮማንዶ ሮዝንችርግ የሚባል ልዩ የጦር ሀይል በፎን ኢንግራም መሪነት ተቋቋመ። ይህ ልዩ ጦር ከ 80 ሰዎች በላይ ነበሩ። ከዚህ በኋላ ይህ ጦር ሀይል ለሁልት ተከፈለ። አንዱ የጦር ክፍል አቱናን እንዲይዝ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ሳሎኒኪን እንዲቆጣጠር ነበር። በህዳር 15 ቀን 1941 ዓ.ም የተወሰኑ ወታደሮች ወደ ግሪክ ተልከው በአገሪቱ ምን ያህል ይሁዳዊያን እንዳሉ አጣርተው፤ 78, 750 ይሁዳዊያን እንደነበሩ እና ከእንዚህ ደግሞ ወደ 55,000 ይሁዳዊያን በሳሎኒኪ እንደሚኖሩ አጣርተው እንደመጡ ይታወቃል። ከእነዚህ በተጨማሪ ደግሞ የቀሩት በሌሎች ከተሞች እና ክልሎች ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ብዙ የይሁዳዊያን ህብረተሰብ የነበሩባቸው ሌሎች ከተሞች ደግሞ፦ በኮርፖ (3000 ይሁዳዊያን ) ፣ በካቫላ (3,000 ይሁዳዊያን) ፣ ቢኒያና (3,000 ይሁዳዊያን) እና አቱና (2 500 ይሁዳዊያን) ነበሩ ፡፡
በሚያዚያ 9 ቀን 1941 ዓ.ም ጀርመናዊያን ወደ ሳሎኒኪ ገቡ። ወደ ከተማው ከገቡ ከሁለት ቀናት በኋላ ሁሉም የይሁዳዊያን ጋዜጦች እና ህትመቶች እንዲዘጉ አዘዙ። እንዲሁም በእነርሱ ምትክ የፀረ-ሴማዊ ጋዜጦች እና ህትመቶች እንዲታተሙ እና እንዲወጡ ሆኑ።
በሚያዚያ 15 ቀን 1941 ዓ.ም ሁሉም በከተማዋ የሚኖሩ ይሁዳዊያን እና የተከበሩ የህዝብ አገልጋዮች ይሁዳዊያን እንዲታሰሩ ተደረገ። ከዚህም በኋል ይሁዳዊያን እየተያዙ መታሰር ቀጠለ። ጀረመናዊያን የድሮ የማህበረሰብ ስልጣን የነበረውን ሻቭታይ ሻአልቴኤልን ለሳሎኒኪ ከተማ እና በአካባቢው ለሚኖሩ ማህበረሰብ ሀላፊ አድርገው ሾሙት። ነገር ግን ሻቭታይ ሻአልቴኤል የተሰጠውን የተወሳሰበ ሀላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉት አስፈላጊ ችሎታ ስላልነበረው፤ ዣክ አልቨላን እንዲያግዘው እና ለጀርመናዊያን የሰራውን ስራ ለማስተላለፍ እንዲተረጉምለት እርሱን ሾመው። ከዚህ በኋላ በከተማዋ የነበሩ ይሁዳዊያን ት/ቤቶች እና ድርጅቶች በተጣለባቸው ከፍተኛ የገንዘብ እዳ ተዘጉ። በሚያዚያ 29 ቀን ይሁዳዊያን የነበራቸውን የራዲዮ ጣቢያ መሳቢያ ለጀርመኖች እንዲያስረክቡ እና ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ቤታቸውን ለቀው ለጀረመናዊያን መኖሪያ እንዲሰጡ ተገደዱ። ነገር ግን ቤታቸውን ለቀው ለጀርመናዊያ እንዲሰጡ የተገደዱ ይሁዳዊያን ብቻ ሳይሆኑ፤ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችም ጭምር ተገደዋል።
በ 1941 ዓ.ም የጀረመናዊ ልዩ "ኮማንዶ ሮዝንበርግ" ተብሎ የሚጠራው ልዩ የኮማንዶ ጦር በሳሎኒኪ የሰራው የመጀመሪያ ስራ፤ በከተማዋ የይሁዳዊያን ባህላዊ ንብረት ማውደም ነበር። የይሁዳዊያን ቤተ-መጻሕፍት እና ጥንታዊ የእጅ ጽሑፎች ተወሰዱ። የኦሪት መጽሐፍት፤ የጸሎት መጽሐፍት እና የብር ቅዱስ ዕቃዎች ሁሉ ተወሰዱ። በዚህ ጊዜ ህዝባዊያን ንብረት ሳይሆን የተወሰደው፤ የይሁዳዊያን የግል ንብረት ጭምር ነበር የወሰዱ። ከእንዚህ መካከል የህብረተሰቡ ራብ ኮርፅ የሚባለው ሊቅ መጽሐፍ ቤት ተወስዶበታል። ወደ 3,000 ገደማ የሚሆኑ መጻሕፍት እና የሌሎች ራባናት ቤተ-መጽሐፍቶች ፣ በመቶ የሚቆጠሩ የመጽሐፍት ፍልስፍና ነበሩ ፡፡ ጽሑፉ ተሰብስቦ በጀርመን ፍራንክፈርት ውስጥ የይሁዳዊያን ጥናት ተቋም የኢብራይስጥ ዲሬክተር በሆነው ዮሃን ፖል ቁጥጥር ስር ወደ ጀርመን ተልኳል። ብዙዎቹ እነዚህ ባህላዊ ሀብቶች የተሰበሰቡት በሳሎነኪ ማህበረሰብ ውስጥ ለዘመናት የተሰበሰቡ እና ለስፔን ይሁዳዊያን ታሪክ እና ለመንፈሳዊ ህይወት ልዩ ምንጭ የነበሩ ቢሆኑም ከጦርነቱ በኋላ አልተገኙም።
የጀርመን ወረራ ኃይሎች እንደገቡ ወዲያውኑ ሳሎኒኪ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ደርሶበታል ፡፡ ጀርመናዊያን ማዕድን ማውጫዎችን ፣ የእህል መጋዘኖችን ፣ የጥጥ እና የእርሻ ምርቶችን በከተማው ዙሪያ ጨምሮ ሁሉንም ለፍላጎታቸው አነሱ ፡፡ በከተማ ውስጥ የስራ እና የምግብ እጥረት ነበር። ከዚህ ችግር የተነሳ የይሁዳዊያን ስቃይ በጣም ከሌሎች ኖዋሪዎች የበለጠ ነበር። ከ1941-1942 ዓ.ም የይሁዳዊያን ችግር ተባብሶ፤ ይሁዳዊያን በረሀብ እንደሞቱ ተመዝግቧል። እንዲሁም ረሀቡ የተለያዩ በሽታዎችን እንዲስፋፉ ምክንያት ሲሆን፤ ይሁዳዊያን በሚኖሩበት አካባቢ ወረርሽን አለ ስለተባለ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛወሩ ማአቀብ ተጣለ። ይህ ችግር ለመቋቋም ደግሞ ህዝባዊ የማዕድ ቤት ተከፍቶ በሺ ለሚቆጠሩ ይሁዳዊያን ምግብ ይሰጥ ነበር። የቀይ መስቀል ድርጅት እና የይሁዳዊያን ህብረተሰብ በ 1941 ዓ.ም ለ 2000 ይሁዳዊያን እርዳታ ለመስጠት ብዙ ጥረት አድርገዋል። በየቀኑ 5000 ማዕድ እና 1700 ለህፃናት ወተት ይሰጡ ነበር። በሳሎነኪ ዓለም አቀፍ አካላት በተሰጡት ግምቶች መሠረት ይሁዳዊያን የተቀበሉት የገንዘብ መጠን ከከተማዋ ህዝብ አንፃር ሲታይ በጣም ጥቂት ነበር፡፡
በሚያዚያ 1942 ዓ.ም የጀርመን ጦርነትን ለማስፈፀም ሲቪል ዜጎችን ማንቀሳቀስ እንዳለበት ትዕዛዝ ወጣ ፡፡ ወታደራዊ ምልመላ ሀላፊዎች በ 24 ሥዓት እንዲቀርቡ ግዴታ ይጠበቅባቸው ነበር ፡፡ በዚህ ጊዜ የከተማዋ የጦር አዛዥ ጄኔራል ፎን ክራንስኪ ከ 18 - 45 ዕድሜ ያላቸው ይሁዳዊያን በሙሉ በሰንበት ቀን እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጠ። ምክንያቱም በሀምሌ 11 ቀን 1942 ዓ.ም በ 8፡00 ሥዓት በነፃነት አደባባይ ለስራ በቂ አቅም ያልቸው ይሁዳዊያን መዝገብ ለማዘጋጀት ነበር። የማኅበረሰቡ ፕሬዚዳንት በግዳጅ የጉልበት ሥራ ምልመላ በተዘጋጀው መዝገብ፣ ራባናትን ፣ መምህራን እና የእርዳታ ሠራተኞች ከዚህ መዝገብ ማስወጣት ችሏል። በዚህ ቀን 6,500 ይሁዳዊያን የሰንበትን ልብስ እንደለበሱ ወደዚህ ቦታ ቀረቡ። ይህ ቀን "ጥቁር ሰንበት(ሻባት ሀሽሆራ)" በመባል ሊጠራ ይችሏል። ጀርመናዊያን ለረጅም ሰዓታት በከባድ ፀሀይ ይሁዳዊያን በማቆም እና በውሻ እያሳደዱት፤ ያለ የውሃ በፀሐይ እብዙ ሥዓታት በማቆም ሲወድቁ እንኳ ማንኛውንም የሕክምና ዕርዳታ ሳይሰጡ እና ይከለክሉ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ ጀርመናዊያን ይሁዳዊያን እንዲበተኑ አዘዙ ፡፡ ነገር ግን መመዝገብ ያልቻሉ ሰዎች ሐምሌ 13 ቀን ወደ አደባባይ መመለስ ነበረባቸው ፡፡
በሥራ ላይ ያሉት ይሁዳዊያን ወደ በርካታ የጉልበት ስራ ካምፖች ተላኩ ፡፡ የመመልመል ዓላማ ወደ 5000 የሚሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎችን መንከባከብ ነበር ፡፡ በካምፖቹ ውስጥ የኑሮ እና የሥራ ሆኔታ አስቸጋሪ ነበር ፣ ምክንያቱም ይሁዳዊያን ለዚህ አይነት ሥራ ሰርተው ስለማያዉቁ ነበር፡፡ እንደምሳሌ ቢወሰድ፦ በቀን 12 ሰዓት ያህል በፈረስ ማቆሚያ ቦታ ውስጥ ይሰሩ ነበር ፡፡ ለእነሱ ምግብ በቂ አቅርቦት አልነበራቸውም ፣ እንዲሁም የእነሱ የበላይ ተመልካቾች አመለካከት ግትር ነበር። በተለያዩ ግምቶች መሠረት 700 ያህል ይሁዳዊያን ለስራ ከተቀጠሩ በኋላ በአራቱ ወራቶች ውስጥ በካምፑ ውስጥ ሞተዋል ፡፡
በ 1942 የበጋ ክስተቶች በህብረተሰቡ ውስጥ በጣም ድንግጤ ነበር፡፡ በሐምሌ ወር አጋማሽ ላይ ወደ 1,200 የሚጠጉ ሀብታም ይሁዳዊያን የተለያዩ ትክክለኛ ያልሆኑ ወረቀቶችን(ሰርፍትኬቶችን) በመጠቀም ወደ ጣሊያን ወረራ ለመሄድ የቻሉ ሳሎነኪን መልቀቅ ችለዋል፡፡ በታህሳስ 11 ቀን 1942 ጀርመናዊያን የማኅበረሰቡ መሪነት ተተክተው በሳሎነኪ ዋና አለቃ ዶ / ር ዛቪ ኩርትዝ የሚመራ ሲሆን ስድስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ነበር ፣ ሁሉም ለሥራ አስፈፃሚ አካላት በጋራ የወጡ ናቸው ፡፡ በግሪክ ውስጥ “የመጨረሻው መፍትሄ”
በጥር 1943 መገባደጃ ላይ ወደ ሳሎነኪ ከተማ ሮለፍ ጊንተር፤ የአይህማን ምክትል የከተማዋን ይሁዳዊያን ለማስወጣት ለማዘጋጀት መጡ ፡፡ ከከተማይቱ ወታደራዊ ባለሥልጣናት እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞች ጋር በመተባበር ዝግጅቱ ጀመረ ፡፡ የካቲት 1943 ቀደም ሲል የሰሎባኪያ ይሁዳዊያን ለመልቀቅ ካዘጋጃቸው ከኤሺማን ታላላቅ ሰዎች አንዱ ወደ ሳሎነኪ ገባ፡፡ እስከዚያ ድረስ በግሪክ ውስጥ በነበረበት እና የከተማዋን ይሁዳዊያን ለመጥፋት ያዘጋጀው አሎይስ ብሩነር ነበር ፡፡ ከከተማይቱ ወታደራዊ ገዥ ጋር በመተባበር በሳሎነኪ ውስጥ ይንቀሳቀሱ ነበር። እንዲሁም የኤስ ኤስ ወታደራዊክ ክፍል ካምፑን በቫሊሳሪዮ 42 በመመስረት 50,000 ይሁዳዊያን እዲሰደዱ አድርጓል፡፡
በየካቲት 6 እድሜያቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉም ይሁዳዊያን በልብሳቸው ላይ “ቢጫ ባጅ” እንዲለብሱ እና ወደ ተመደቡባቸው ልዩ ማዕከላት እንዲገቡ የሚጠይቅ ትዕዛዝ ወጣ ፡፡ ከመሻገሪያው አንስቶ እስከ ባጅ ድረስ የውጭ ዜግነት ያላቸው (ጣሊያናዊ ፣ ስፓኒሽ ፣ ቱርክ) ያላቸው ይሁዳዊይን ትክክለኛ ፓስፖርት ከማሳየት ነፃ ሆነዋል ፡፡ ከቦታ ወደ ቦታ የይሁዳዊያን ማህበረሰብ እዘዋወር እና ለእነርሱ ተብሎ ከተዘጋጀው የመስብሰቢያ ካምፕ መውጣት እና መዘዋወር በድርጅት የተከለከለ ነበር። በየካቲት 13 ላይ ይሁዳዊያን መኖሪያቸውን ያለፍቃዳቸው እንዳይለውጡ የሚከለክል ሌላ አዋጅ ወጣ ፡፡ ይህን ትዕዛዝ የሚጥስ የሞት ፍርድን ወሰንበት ነበር ነበር ፡፡ ከድንጋጌው በተጨማሪም ይሁዳዊያን የሕዝብ መጓጓዣን እንዳይጠቀሙ፤ በተወሰኑ የከተማዋ ክፍሎች እንዳይገቡ እና ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ከቤታቸውን እንዳይወጡ ተከለከሉ። በይካቲት 17 ቀን ሦስተኛው ትዕዛዝ እጣ፤ ይሁዳዊያን ነጋዴዎች በጀርመንና በግሪክ “የይሁዳዊያን ሱቅ” ላይ ምልክት እንዲያደርጉ ይጠየቁ ነበር ፡፡ ከየካቲት 25 በተጨማሪ ቤታቸውን በተለያዩ መንገዶች ምልክት እንዲያደርጉ ተጠየቁ ።
በሳሎነኪ ከተማ ሶስት ካምፖች ሲቋቋሙ፤ ሁለቱ ተክፍተው ለይሁዳዊያን መሰብሰቢያ ሲሆኑ፤ ሶስተኛው አምፕ ደግሞ ወደ ተለያዩ የማጥፊያ ካምፕ የሚሰደዱ ይሁዳዊያን መሸጋገሪያ ነበር፡፡ ይህ አውራጃ ፣ ‹ባሮን ሂርሽ› ዲስትሪክት ፣ ከባቡር ሐዲዱ ቅርብ ስለሆነ ነበር፡፡ ወደ ካምፑ መሄድ መሄድ እና ከዚህ ካምፕ በሰው ልጅ ላይ ታይቶ የማይታወቅ አስቸጋሪ ሰቆቃዎች ይፈፀሙ ነበር። በጀርመናዊያን ቁጥጥር ስር የነበረው የይሁዳዊያን ፖሊስ አባል ወደ 250 ይሁዳዊያን በቦታው የሚደረገውን እንቅስቃሴ ይቆጣጠር ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ ቀደም ሲል በግሪክ ጦር ውስጥ በጄኔራል ደረጃ ውስጥ ያገለገሉ ሲሆን፤ ከመካከለኛው አውሮፓ የመጡ ስደተኞችም ጭምር ነበሩ፡፡ ከእነዚህም ጀርመናዊው ተናጋሪ የነበረ ሲሆን ለሥራው ባለሥልጣናት ቅርበት የነበረው ዣክ አልባላ የሚመራ ነበር ፡፡ ወደ ካምፑ መሻገር መጋቢት 6 ቀን ሲጠናቀቅ፤ ነገር ኝ በካምፑ ውስጥ አስከፊ ሁኔታዎችን አላቋረጡም፡፡ በእያንዳንዱ አፓርታማ ውስጥ ከሶስት እስከ ስድስት ቤተሰቦች ይኖሩ ነበር ፣ እና አንዳንድ ጊዜ የቤቶች መጠኑ በ 16 ካሬ ሜትር ስፋት 30 ሰዎች ይኖሩበት ነበር ፡፡ ሌሎች ይሁዳዊያን መላው ሰፈር በእንጨት በተሠራ ገመድ አጥር የተከበበ ነበር ፡፡
መጋቢት 10 300 ባቡሮች ወደ ሳሎኒኪ የባቡር ጣቢያ እንደደረሱ ህብረተሰቡ ሰማ፡፡ ሀራብ ኮርፅ እና ከእርሱ ጋር አብረው የሚሠሩ ኮሚቴ አባላት ለሳሎነኪ ለሚገኘው የጀርመን ወታደራዊ አስተዳደር የሲቪል ጉዳዮች አማካሪ ለነበረው ለማክስ ማርተን የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ በከተማዋ የሚኖሩትን ይሁዳዊያን ግማሹን ንብረት እንዲወስዱ ማመልከቻ ካቀረቡ በኋላ፤ ከሃያ አራት ሰዓታት በኋላ ማርተን ከበርሊን አውንታዊ መልስ እንደተሰጠው ነገራቸው፡፡ የሳቸው አስተያየት የተለያዩ የግሪክ ድርጅቶች የይሁዳዊያን ከሳሎኒኪ እንዲባረሩ ይጠይቃሉ ብሎ ስለ አስበ ነበር፡፡ መጋቢት 13 ቀን 1943 ማርተን ለጀርመናዊያን ጥቅም በከተማዋ የሚገኘውን የይሁዳዊያን ንብረት እንዲወረስ ትዕዛዝ በመስጠት ለዶክተር ኮርትፅ ተላ፡፡ከእነዚህም ጥሬ ገንዘብን እና ሌሎች ውድ ንብረቶችን ያካተተ ነበር፡፡ ህብረተሰቡ እስከ መጋቢት 15 ድረስ ንብረቱን ለጀርመናዊያን የማዛወር ግዴታ ነበረባቸው ፡፡ መጋቢት 14 ፣ ከሳሎነኪ የመጀመሪያው መጓጓዣ ከመድረሱ በፊት ፣ ራብ ኮርፅ ወጣቶችን በ ‹ባሮን ሂርስሽ› ካምፕ ውስጥ ለተሰበሰቡ ይሁዳዊያን ንግግር አደረጉ፡፡ ወጣቶች በግሪክ ካምፖች ውስጥ መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ እና ወላጆቻቸውም በሳሎነኪ እንደሚኖሩ ነገሯቸው ፡፡ የመጀመሪያው ትራንስፖርት ወደ ኦሽቪፅ የሄደው በ 20 ኛው ቀን መድረሻ ላይ መድረሱን ለአምስት ወራት ያህል አውሮፕላኖቹ ይመላለሱ ነበር፡፡ ስዊዘርላንድ ከ “ባሮን ሂርስሽ” ሰፈር ውስጥ በመጋቢት ውስጥ 5 ትራንስፖርቶች፤ በግንቦት 9 - ሁለት ፣ ሰኔ - አንድ እና ነሐሴ - ሁለት ከተባረሩ ነፃ የወጡ ሲሆን ይሁዳዊያን ግዛቶች ወይም እንደ ቱርክ እና ስፔን ላሉ ገለልተኛ ሀገሮች ተገዥ ነበሩ ፡፡ የተወሰኑት - 500 ይሁዳዊያን የስፔን ዜግነት ያላቸው ፣ 280 የጣሊያን ዜጎች ፣ እንዲሁም የቱርክ ፣ ፖርቱጋሎች ፣ አርጀንቲና ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ግብፅ ፣ ሃንጋሪ እና ቡልጋሪያ ዜግነት የያዙ ይሁዳዊያን - መጓጓዣው በሚነሳበት ጊዜ ሁሉ ‹የባሮን ሂርስሽ› ካምፕ አካባቢ ለትራንስፖርት በተዛወሩት ይሁዳዊያን ተሞልተው ነበር፡፡ በእያንዳንዱ የጭነት መርከብ ውስጥ የነበሩት ይሁዳዊያን ቁጥር ከ 1000 እስከ 4,500 ይሁዳዊያን ይደርስ ነበር፡፡
እንዲሁም በሳሎነኪ መጓጓዣ ከሌሎች ትሬቶች እና መክዶንያ የመጡ ሌሎች ይሁዳዊያን ተቀላቅለው ነበር። በሚያዝያ ወር መጨረሻ 318 ይሁዳውያን ከቪሪያ እና ከፍሎሪና ደግሞ 372 ከሳሎነኪ ተልከዋል ፡፡ በግንቦት ወር ሌሎች 900 ይሁዳዊያን በእነዚህ ወረዳዎች ካሉ ከተሞች ተላኩ ፡፡ በጠቅላላው ፣ ጀርመናዊያን ባደርጉት መዝገብ ከሳሎኒኪ ወደ አውሽቪፅ የተላኩት ይሁዳዊያን 48,533 ነበሩ ፡፡ ሆኖም ፣ የተላኩትን ይሁዳዊያን ቁጥር በትክክል ይህ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም አንድ መጓጓዣ 46 ሠረገላዎችን እና የማይታወቁ ይሁዳዊያን ቁጥር ወደ ትሬብሊንካ ካምፕ ስለመጡ፤ የእነዚህ ሰዎች ከመጋቢት 23 እስከ 27 በ1943 ባለው ጊዜ ውስጥ ከሳሎኒኪ ንደመጡ ይገመታል፡፡ እንዲሁም ከትራስ እና ከመክዶንያ የመጡ ይሁዳዊያን ያካተተ እንደሆነ ይገመታል። ከሳሎኒኪ ተሰደው ወደአውሽቪፅ ከመጡ ይሁዳዊያን ውስጥ መካከል 11,147 ወጣት ወንዶችና ሴቶች በካም ውስጥ እንዲሠሩ ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህም 7000 ወንዶች እና ጥቂት ከ 4000 ሴቶች ነበሩ ፡፡ ሌሎች ይሁዳዊያን በህይወት ማጥፊያ የጋዝ ማሽን ህይወታቸውን በቦታው አጡ፡፡
የሳሎኒኪ ይሁዳዊያን ልዩ ዕጣ፟ በሳሎኒኪ በሕይወት የተረፉ ሰዎች በሰጡት የምስክርነት እና በማስታወሻዎች፤ እንዲሁም ከሌሎች የአውሮፓ አገራት የተውጣጡ ይሁዳዊያን እስረኞች በሰጡት የምስክር ወረቀት ላይ ተመዝግቧል ፡፡ ወደ አውሽቪፅ የመጡት ግሪካውያን ይሁዳዊያን ከፖላንድ ወይም ከመካከለኛው አውሮፓ ከይሁዳዊያን እስረኞች በተለየ መልኩ የምሥራቃዊ አውሮፓን የአየር ጠባይ ስለአለመዱት፦ ቀዝቃዛው ፣ ከባድ ስራው ፣ አስቸጋሪው የኑሮ ሁኔታ እና ቤተሰቦቻቸውን በጋዝ ክፍሎች ውስጥ የማጣት ቀውስ ለራሳቸው ትልቅ ውድቀት ደረሶባቸዋል፡፡ በመጀመሪያዎቹ ወራት የካምፑ ዋና ቋንቋዎቹ ጀርመንኛ ፣ ይዲሽ ወይም ፖላንደኛ ስለማይናገሩ ከባድ ያለመግባባት ችግሮች አጋጠማቸው ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች እስርኞች የተለያዩ ጉዳቶችን አድርሰውባቸው ነበር፡፡ እንደምሳሌ፦ በተለያዩ አዋራጅ ስድቦች ሰድቦቸው እና የቅጥል ስም ይሰቷቸው ነበር፡፡ ሆኖም ግን የሳሎኒኪ ሰዎች በካምፑ ውስጥ እንደ ትልቅ እና አስፈላጊ የሰው ኃይል ይቆጠሩ ነበር። በትጋት እና በአካላዊ ችሎታቸው የታወቁ ሲሆኑ ልዩ ሁኔታቸውም በእስረኞቹ መካከል አንድነትና ህብረት የሚያደርግ ነበር ፡፡
በ 1943 ዓ.ም በፀደይ-የበጋ ወራት ወደ አውሽቪፅ የመጡ ወጣቶች በተለያዩ ማዕድናት ወይም በግብርና ሥራ ውስጥ ተሰማርተው ነበር ፡፡ በ 1943 መገባደጃ ላይ ብዙ በመቶ የሚቆጠሩ እስረኞች ከአውሽቪፅ ወደ ጉልበት ሥራ ካምፕ ተላኩ ፡፡ ሥራቸውም በቫርሻ በሚገኘው የጉልበት ስራ የፈረሱ የክምፕ (ጌቶወችን) ማፅዳት ነበር ፡፡ በጋንሻ ጎዳና ላይ ቢያንስ ሁለት የይሁዳዊያን ቡድኖች ወደዚያ ለስራ ተልከው ነበር፡፡ ከነዚህም መካከል አብዛኛዎች የሳሎኒኪ ይሁዳዊያን ነበር፡፡ በነሐሴ ወር ወደ 500 የሚጠጉ ሠራተኞች ወደ ቫርሻ መጡ፡፡ እንዲሁም በጥቅምት ወር 1943 ደግሞ ወደ 500 የሚጠጉ ሰራተኞች ደርሷል ፡፡ እነሱ የተመረጡት ፖላንደኛ ስለማያውቁ እና ከፖላንዶች ጋር ያለቋንቋ መግባባት ስለማይችሉ ስለታወቀ እና እንዳይግባቡ ስለተፈለገ ነበር፡፡ ጥር 1944 በ “ጋንሽኮቫ” ካምፕ ውስጥ በሠራተኞቹ መካከል ወረርሽኝ በሽታ ተከስቶ የነበረ ሲሆን፤ በየቀኑ አሥራ ሁለት እስረኞች ይሞቱ ነበር፡፡ በግንቦት-ሰኔ አንድ ሌላ የእስረኞች ቡድን ደረሰ፡፡ ከካምፑ ከወጡ በኋላ ጀርመናዊያን ለመልቀቅ ያልቻሉ 300 በሽተኞችን ገድለዋል ፡፡ በፖላንድ ውስጥ የፖላንድ አመፅ ከመነሳቱ በፊት አብዛኛዎቹ የግሪክ እስረኞች ከካምፕ የተፈናቀሉ በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት ነበር። ከዚህ በኋላ የይሁዳዊያን ዕጣ ፈንታ በግሪካዊያኑ የግዞት አካባቢ የተሻሻለ ሆነ ፡፡ በጠቅላላው 1200 ይሁዳዊያን በዚህ አካባቢ ይኖሩ ነበር ፡፡
ከጣሊያን ወረራ ጀምሮ እስከ መስከረም 8 ቀን 1943 ድረስ ፣ በጀርመን ወረራ ወቅት ይሁዳዊያን የጣሊያን ባለስልጣናት ባላቸው ልግስና ተደስተው ነበር ፡፡ እነዚህ በጀርመናዊያን ግፊት አልተሸነፉም። ፀረ-ይሁዳዊያን ህጎች ለመጣል አሻፈረኝ አሉ፤ እናም የግሪክን ህዝብ እንኳን ይሁዳዊያን እንዲረዱ እና እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡ ነገር ግን መስከረም 20 ጀርመናዊያን ወደ ግሪክ ከገቡ በኋላ “የመጨረሻውን መፍትሄ” ለማሳካት የሚያስፈልጉ እርምጃዎች በእነዚህ አካባቢዎችም ማንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ ቪስሊፃኒ ወደ አቱና ተላከ፡፡ የኤስ_ኤስ ጄኔራል ያርጋን ስትሮፕ ደግሞ የቫርሻን የመሰብሰቢያ ካምፖችን አመፅ ካወደመ በኋላ እና የቀሩትን ይሁዳዊያን ከበተነ በኋላ ወደዚህ መጣ፡፡ በጥር 1944 ቶኒ ቡርጅ ዳተር ዊልትዝኒን ፈንታ ተተካ።
በጥቅምት 1943 መጀመሪያ ላይ ስትሮፕ በጎዳና ላይ ፖስተሮችን እና በጋዜጣዎች ይሁዳዊያን ወደ ፀሎት ቤት በመምጣ እንዲመዘግቡ አዋጅ አወጀ፡፡ የሌላ አገር ዜኘት ያላቸው ይሁዳዊያንን አይጨምር ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ጀርመናዊያን ህብረተሰቡ ልዩ የሽማግሌዎች ኮሚቴ እንዲመርጡ እና ጉዳያቸውን በእነርሱ አማካኝነት እንዲያቀርቡ አስታወቋቸው፡፡ ይህ ቢሆም ጀርመናዊያን በራሳቸው ሀላፊነት አዲስ ኮሚቴ መረጡ፡፡ የኮሚተው ዋና ሀላፊ ሞሼ ሻኪ ሲሆን፤ ምክትል ሀላፊው ይፅሀቅ ካቢልሊ ነበር፡፡ ሞሼ ሻኪ በጥር 1944 ዓ/ም ከሞተ በኋላ ይፅሀቅ ካቢሊ በእርሱ ፈንታ ተሾመ።
የአቱና ይሁዳዊያን ጀርመናዊያን እንዳዘዙት ለመመዝገብ ተሎ አልሄዱም፡፡ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ወደ ሌላ ቦታ በምሸሸት እና ወደ ደን በመግባት እና በገጠር ቦታ በምሄድ ተሸሸጉ፡፡ በአጠቃላይ ከ 300 ሰዎች የሚደርሱ የተሳሳተ ይምስክር ወረቀት በማኘት በአቱና እና በአካባቢዋ መሸሸግ ችለዋል፡፡
የግሪክ ወጣቶች እና ሌሎች ነዋሪ ቡድኖች ለይሁዳዊያን ማምለጫ መንገዶችን እመፈለግ እና በመደበቅ ከፍተኛ እገዛን አድርገዋል፡፡ ከአንድ ወር በኋላ የተመዘገቡት ይሁዳዊያን ቁጥር 2,000 ብቻ ነበር፡፡ ከ 300 ዎቹ ጣሊያኖች ሲሆኑ 200 ዎቹ ደግሞ ስፓኒሽ ፤ ፖርቱጋሎች እና ቱርክ ነበሩ፡፡ ከተመዘገቡት አብዛኞዎቹ ይሁዳዊያን ውስጥ በንብረታቸው አማካኝነት መሸሸጊያ ቦታ የማግኘት ወይም የምግብ መግዣ የሚቀብሉት ካርዶች የለላቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ከነዚህ ሰዎች መካከል እድሜው 14 ዓመት የሆነው በየቀኑ ከጀርመአዊያን ወታደሮች በምቅርብ መመርመር ነበርባቸው፡፡ እንዲሁም ከ 17፡00፟ 7፡00 ድረስ ህዝባዊ ቦታዎች አካባቢ እንዳይዘዋወሩ ተከልክለው ነበር፡፡
መጋቢት 1944 ጌስታፖ ፋሲካ ከመጀመሩ በፊት ይሁዳውያን በከተማው ውስጥ በሚሊዶኒ ጎዳና በሚገኘው ፀሎት ቤት ማፃ እና ስኳር እንደሚቀብሉ ለህብረተሰቡ አደርሱ፡፡ በመጋቢት 23 ላይ የአይህማን አዲሱ ተወካይ የሆነው ቶኒ ቡርገር ወደ ፀሎት ቤቱ በመጣት፤ ጦርነቱ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ በጀርመን ወደሚገኙት የጉልበት ካምፖች እንደሚላኩ በታው ለተሰበሰቡ ይሁዳዊያን አስታወቀ፡፡ እዚህ በኋል የፀሎት ቤቱ በር ሰዎች ሳይወጡ በመዝጋት፤ በዚህ ስብሰባ ላይ የነበሩ ይሁዳዊያን ተይዘው ወደ ጀርመን የግይልበት ስራ ለመስራት ተላኩ፡፡ አንዳን ሰዎ 300 ሰዎ እንደነበሩ ሲገልፁ፤ ሌሎች ደግሞ ከ 700 – 1000 ይደርሳሉ የሚሉ አሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደ “ሄይድሪ” ጊዜያዊ መሸጋገሪያ ካምፕ ተወሰዱ ፡፡ እዚያም ወንዶች ከሴቶች ተለያይተው በጦር ሰፈር ውስጥ ታስረው ነበር ፡፡ በማግስቱ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቀሉ እና በአካባቢው ይገኙ የነበሩት የይሁዳዊያን ቁጥር ወደ 1,500 ይደርስ ነበር፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ በአውራጃው ውስጥ ተማርከው የመጡ ይሁዳዊያን በመደብለቅ በአጠቃላይ በካምፑ 3000 ይሁዳዊያን ነበሩ፡፡
በሚያዚያ 2 ቀን 1944 1,200 የሚሆኑ ይሁዳዊያን ከሃይድሪ ጊዜዊ ካምፕ ወደ አውሽቪፅ ተወሰዱ፡፡ የ ሌላ አገር ዜጎች የነበሩ፦ ለምሳሌ የስዊዘርላንድ ና የጥሊያ ዜኘት የነበራቸው ይሁዳዊያን ተለቀቁ፡፡ ነገር ኝ የጣሊያን ግዛት ካበቃ በኋላ የፈረንሣይ ፣ ቡልጋሪያ ፣ ሁንጋሪያ እና የጀርመን ይሁዳዊያን ወደ አውሽቪፅ በ አፕሪል 11 ደረሱ፡፡
በሆሎኮስት ጊዜ የግሪክ ይሁዳዊያን መጥፋት በርካታ ግምቶች አሉ ፡፡ የእነሱ ልዩነት በዋነኝነት የተመሠረተው በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ ትክክለኛ የግሪክ ይሁዳዊያን ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ይሚገልፅ መረጃ አለመኖሩ ነው፡፡ ከአንድ ምንጭ የተገኘ መረጃ (በታሪክ ምሁር ሃጋን ፍሌይሸር) ከጦርነቱ በፊት በግሪክ የነበሩት ይሁዳዊያን ቁጥር 71,611 እንደንበረ ሲገልፅ፤ ከነዚህ ውስጥ 58,885 በጀርመናዊያን ንደተገደሉ ይገልፃል፡፡ ሚካኤል ሞልኮ እና ጆሴፍ ነሀማ በሚሰጡት መረጃ መሠረት ከጦርነቱ በፊት በግሪክ የነበሩ ይሁዳዊያን ቁጥር 79,950 እንደሆነ እና የሮዶስን ይሁዳዊያን እንደሚጨምር ይገልፃሉ፡፡ ከጦርነቱ የተረፉት ይሁዳዊያን ቁጥር 10,371 ሲሆን፤ በጥር 1945 በተካሄደው የግሪክ ይሁዳዊያን ህብርተሰብ ኮሚቴ ፕሮቶኮል መሠረት ከጦርነቱ በፊት 67,203 ይሁዳዊያን በግሪክ የነበሩ ሲሆን በጥር 1945 ደግሞ 9,825 ነበሩ ፡፡
ጀርመናዊያን ከለቀቁ በኋላ የግሪክ ይሁዳዊያን ከተሰወሩበት ቦታ በመውጣት ወደ ቤታቸው መመለስ ጀመሩ፡፡ በጥቅምት 1944 የግሪክ መንግሥት የጀርመን መንግስት የደነገገውን የመድልዎ ህጎች እና ፀረ፟ይሁዳዊያን በመሻር ለይሁዳዊያን ሙሉ እኩልነት እንዲሆን አወጀ ፡፡ ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ጦርነቱ ከደረሰ በኋላ ወዲያውኑ በግሪክ ውስጥ የተረፉ ይሁዳዊያን ቁጥር 10,000 ገደማ ይሆን ነብር፡፡ ከእንዚህ ይሁዳዊያን በተለያዩ ቦታዎች ተሸሽገው የነበሩ 1,500 ልጆች ነበሩ ፣ ብዙዎች ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ጆች ነበሩ ፡፡ እህይወት ከተረፉት ይሁዳዊያን መካከል 65% የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ 35% ብቻ ሴቶች ነበሩ ፡፡ በሕይወት የተረፉት አብዛኞቹ ሰዎች በአቱና፣ በሳሎኒኪ እና ቫልሪሳ በሚባሉ ከተሞች ተሰበሰቡ፡፡ በጥር 1945 ዓ/ም በአቱና ውስጥ 4,985 ይሁዳዊያን እና በሳሎኒኪ ወደ 2,000 ገደማ የሚሆኑ ይሁዳዊያን ነበሩ ፡፡
ወደ ቤት መመለስ ቀላል አልነበረም ፡፡ የቤተሰብ አባላትን ፍለጋ እና የቤተሰብ ንብረት ለመመለስ የተደረገው ትግል፣ የፍርድ ቤት ክርክር በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ ነበር፡፡ እንዲሁም በግሪክ የተፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እና የእርስ በእርስ ጦርነት ጋር በህይወት ተርፈ እና ህይወታቸውን እደገና ለማደስ በሚሯሯጡትን ይሁዳዊያን ላይ በጣም ክፍተኛ ችግር ፈጠረባቸው፡፡ በሌላ የአውሮፓ አገሮች በህይወት ይተረፉ ይሁዳዊያን እንደገና አዲስ የህይወት ምዕራፍ ለመጀመር ወደ ሌላ አገሮች በመሄድ፤ ኖሮዋቸውን እንደአዲስ ይጀምሩ ነበር፡፡ ስለዚህ በግሪክ አገር የነበሩ ይሁዳዊያን ወደ አዲስ አገር ከመሄድ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡ ከ 1948 ዓ/ም እስከ 1950 ዎቹ አጋማሽ ድረስ ለግሪክ ይሁዳዊያን የስደተኞች መገኛ ሥፍራ የነበረች እስራእኤል አገር ናት፡፡ እንዲሁም ሌሎች አገሮች እንደ፦ አሜሪካ ፣ ካናዳ ፣ አውስትራሊያ እና አንዳንድ የላቲን አሜሪካ አገራት ነበሩ፡፡ ወደተለያዩ አገሮች በመሄዳቸው የግሪክ ይሁዳዊያን ማህበረሰብ እየቀነሰ መጧል፡፡ ስለዚህ በ 1951 ወደ 6,000 የሚሆኑ ይሁዳዊያን እንደነበሩ ይታወቃል፡፡
