የራዶም ኪሂላ(ህብርተሰብ)

ማህደረ ትውስታቸው በሄይፋ መካነ መቃብር ይገኛል።

ቦታ፦ 90 ኪ.ሜ ከቫርሻ በስተደቡ፣ ፖላንድ

ከሆሎኮስት(ሽዋ)  በፊት  በ 1938 የነበረው የህብረተሰቡ ብዛት፦ 24745  , ይሁዳዊያን

 

የህብረተሰቡ የታሪክ አጀማመር

በ 13ኛ ክፍለ ዘመን ራዶም ወደ ከተማ  ስትቀየር፤   በዚህ ቦታ የነበሩ ይሁዳውያን በፅሁፍ የሚታወሱት በ 17 ክፍለ ዘመን  ንደሆነ በታሪክ እንደተፃፈ ይነገራል።  ፖላንድ መንግስት ከቫርሻ በስተደቡብ  ያሉትን ከተሞች  ሀይል ለማጠናከር ሲያደርገው ከነበረው ጥረት  አንፃር የራንዶም የከተማ ኖሪዎች  ኢኮኖሚ መብት ተሰጣቸው።  ነገር ግን  ይሁዳዊያን በዚህ መብት መጠቀም አይችሉም ነበር። የራዶም ባለስልጣኖች ለሁለት መቶ ዓምት ያህል ይሁዳዊያን በከተማዋ እንዳይኖር ብዙ ጥረት አድርገዋል።  ነገር ግን ነጋዴ ይሁዳዊያ ወደ ራንድም መምጣት አላቆሙም። ከዚህም ተጨማሪ ብዙ ነጋዴዎች በራንዶም ከተማ ሲኖሩ ነበር።  ይህ ቢሆንም  ቦታውን እንዲለቁ የሚደረገው ጥረት መቼም አላበቃም። በ18 ክፍለ ዘመን መጨረሻ  የቫርሻ ፍ/ቤት  ይሁዳዊያን ከከተማዋ እንዲባረሩ ወሰነ። ሆኖም  ግን  በከተማዋ ይኖሩ የነበሩ ይሁዳዊያ ቁጥር ለዓመታት አልቀነሰም።

የራዶም ከተማ ኖዋሪዎች በ17 ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በፖላንድ እና በስዊዲን ጦርነት ምክንያት በጣም ተሰቃይተው ነበር። ከተማውም እስከ መጥፋት ድረስ ደርሳ ነበር። የስዊዲን ጦር ሰራዊት የከተማዋን  አቃጥሎ  እና ከ 90% በላይ የሚሆኑ የከተማዋ  ቤቶች አፍርሰዋል።  በዚህ ጊዜ በከተማዋ ሲኖሩ የነበሩ ይሁዳዊያን፤ ከተማዋን ለቀው ወደ  በከተማዋ አጠገብ ወደ ሚገኙ ገጠር  ቦታዎች ተሰደዱ። ከዚህ በኋላ በ 19 ክፍለ ዘመን ከተማዋ እንደገና በኦስትሮ-ሁንጋሪያ ስልጣን አማካኝነት  እንደገና ተቋቋመች። በዚህ ጊዜም ይሁዳዊያን እንደገና ወደ ከተማ መጠው መኖር ጀመሩ። በ 1826 ዓ.ም ከሺ በላይ ይሁዳዊያን በከተማዋ ይኖሩ ነበር።

በራንዶም ሲኖሩ የነበሩ የይሁዳዊያን  ህብረተሰብ የኦርቶዶክስ አክራሪ ይሁዳዊያ ሲሆኑ፤ ዋና ገቢያቸው ንግድ ፣ የእጅ ስራ እና በፋብሪካ ስራ ይተዳደሩ ነበር።  የይሁዳዊያን ሥራ ደረጃ እየተስፋፈ እና ከፍ እያለ በመምጣቱ፤ ይሁዳዊያ ለከፍተኛ ተቋም ትምህርት  እንደ ሶሻሊዝም እና ጽዮናዊነት ትምህርትን እንዲከፈት በር ከፍቷል።  ከዚህም የተነሳ እነረሱን የሚደግፉ ሰዎችን አገኝተዋል።  ይህ ቢሆንም አብዛኛው የሁዳዊያን ህብረተሰብ አክራሪዎች እንደነበሩ እና የኮሚቴ ምርጫ ሲኖር ለ"አጉዳት እስራኤል" ለሚባለው ፓርቲ ሲመርጡ ነበር።  በ 1930 ዓ.ም መጨረሻ ላይ  የአጉዳት እስራኤል አክራሪ ይሁዳዊያን እና የሀቦንድ ግሩፕ በሀገር ውስጥ ሶሻሊስቶች መካከል የነበረው የሃይል  ወደ እኩልነት ተቃርቧል።

በመጀመሪያው የአለም ጦርነት ጊዜ  በዚህ ከተማ አካባቢ የነበሩ ህብርተቦች እና ይሁዳዊያ በኢኮኖሚ ችግር  ተሰቃይተዋል። ይህ ቢሆንም በ 1922 ዓ.ም  የኢኮኖሚው ውድቀት ሆኔታ እየተረጋጋ ሲመጣ፤ በይሁዳዊያ ህብረተሰብ ጥሩ ለውጦች እየታዩ መጡ። በትምህርት መስክ በኵል የይሁዳዊያን ት/ቤቶች  ተቋቋሙ። ለምሳሌ  በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ የፅዮናውያን ወጣቶች  ንቅናቄ  እና የሶሻሊስት ተንቀሳቃሾች ደግሞ   ቤተ-መጽሀፍት እና ክለቦች አቋቋሙ። ስለዚህ የይሁዳዊያን የኢኮኖሚ ደርጃ በጣም የተሻሻለ ነበር። ነገር ግን በይሁዳዊያ ላይ የነበረው ዘረኝነት በ 1930 እንደገና ተመልሶ  ከተማዋን ወረራት። 

ብዙ ይሁዳዊያ በፀረ-ሴማዊ ዘራፊዎች ትንኮሳ ደርሶባቸዋል።   የፖላንድ የቀኝ-ወገን ፓርቲዎች የይሁዳዊያ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዳያገኙ፣ ፖሊሶች የይሁዳዊያን ሶሻሊስት ወጣቶች በሶቪዬት ህብረት የመሰለል ወንጀል በመጠረጠራቸው እና ይሁዳዊያን ባልፈፃሟቸው ከባድ ወንጀሎች ለማስመሰል የተለያዩ ሙከራዎች ተደርገዋል ፡፡ የይሁዳዊያን ሱቆች መጥፋት እና የሱቆች መስኮቶች መሰባበር በጣም የተለመደ ሆነ።

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት እና ሆሎኮስት(ሽዋ)

የጀረመን ጦር የራንዶም ከተማን በመስከረም 8 ቀን 1939   ዓ.ም  ከወረሩ በኋል፤ ብዙ ይሁዳዊያ ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አደረጉ።  ጀርመናዊያን ልክ ወደ ከተማዋ እንደግቡ  በይሁዳዊያ ላይ  ጥቃት እና ውርደት አደረሱባቸው።  በተላይ በአክራሪ ይሁዳዊያ ላይ ጥቃቱ ይበዛ ነበር። ጀርመናዊያን እስከ ጥቅምት ወር ድረስ በራንዶም ከተማ  የሚገኙ የይሁዳዊያ ንብረቶች ነነርሱ ቁጥጥር አደርጉ።

በራንዶም ከተማ በፖላንድ ይሁዳያን አማካኝነት ታሪክ  የጀግንነት ስራ፤  120 ሴት እና ወንድ ወጣቶች  ከሾሜር ሀፃኢር  ከሚባለው  ተንቀሳቃሽ የፅዮናዊነት ስራ የሚሰሩ ወጣቶች  ነበሩ። እነዚህ ወጣቶች  የሰሩት ቤት ነበር። ነገር ግን የጀርመን የጦር ሀይል  ጦሩን የሚያሰፍርበት ቦታ ስለፈለገ፤ እነዚህ ወጣቶች ይህን ቦታ እንዲለቁ ትዕዛዝ ሰጣቸው።  ወጣቶች ይህን ትዕዛዝ ሲቀብሉ፤ በቫርሻ ለሚገኘው  ላሾመር ሀፃኢር መስሪያ ቤት ደብዳቤ  ምን ማድረግ እንዳለባቸው ትዕዛዝ ለመቀብል ደብዳቤ ላኩ። እነዚህ ወጣቶች የደብዳቤውን መልስ  ለመቀል ለሳምንት ያህል ከጠበቁ በኋላ፤ ደብዳቤው በጊዜ እንዳልደረሰ  በተረዱ ሥዓት በራሳቸው ፍቃድ እና ውሳኔ ቦታውን ከለቀቁ በኋላ ወደ ቫርሻ ሄዱ።  ከእነዚህ ወጣቶች ግማሾች ደግሞ በ 1943 ዓ.ም በቫርሻ ካምፕ (ጌቶ) ውስጥ በተደረገው አመጽ ተሳትፈዋል።

በራንዶም ከተማ የቀሩት የሾሜር ሀፃኢር  አባላት በከተማው መራራ ዕድል አጋጥሟቸዋል።  በመጋቢት 1940 ጀርመናዊያን  ይሁዳዊያን ሶሻሊስት አባላት እና የሾሜር ሀፃኢር አባላት በአንድ በመሆን ተቃውሞ ለማደራጀት እንደጀመሩ በተረዱ  ሥዓት፤  የሁለቱ ፓርቲዎች አባላት  በአንድ ላይ ተገደሉ።

ከዚህ በኋላ ጀርመናዊያ በከተማ ዮድንራት አቋቋሙ፡፡  በሀላፊነት ዮሴፍ ዲያመንት የሚባል   ይሁዲ ሾሙ። የዮድንራት ዋና አልማ ብር እና ውድ እቃዎችን መሰብሰብ፤ ለስደተኛ ይሁዳዊያን መኖሪያ ቤት ማዘጋጀት እና ይሁዳዊያ የግዳጅ ስራ ላይ እንዲሰማሩ ማድረግ ነበር።

በራንዶም ከተማ የተቋቋመው  ጌቶ(የይሁዳዊያ መሰብሰቢያ ጣቢያ) በ 1941 ዓ.ም ሲሆን፤ ወደ ካምፑ ይሁዳውያን ሲገቡ የሚቆጣጠሩ  ዮድራንቶ  ከይሁዳዊያ "ሚስቴሬት ሴደር" በማቋቋም፤ ይህ አካል ወደ ጌቶው የሚገቡትን ይሁዳዊያን  ይቆጣጠር ነበር። መጋቢት  7 ቀን  1941 ይህ ቦታ ተዘጋ። በቦታውም  27 ሺ ይሁዳዊያ ነበሩ። እነዚህ ይሁዳዊያ የመጡትም በከተማዋ አካባቢ የነበሩ  ይሁዳዊያን እና በገጠር ተሰማርተው የሚኖሩ ይሁዳዊያ ናቸው።

ዮድንራት የሚሰሩ ሰዎች በካፑ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች  ህይወታቸውን በትንሹ ለማቅለል ሲባል  አንደኛ ደርጃ ትምህርት ቢያቋቁምም፤ ጀረመናዊያን ከካምፑ ውስጥ ትምህርት ቤት እንዲኖር ፍቃድ አልሰጡም። ከዚህ በተጨማሪ ወጣቶች የግድጃ ስራ እንዳይወሰዱ፤ ለሙያ ማሰልጠኛ መካከል ተከፍቶ ነበር። እንዲሁም በካምፑ ውስጥ ሆስፒታል በዶ/ር  ካልይንበርገር አማካኝነት ተክፍቶ ሲያገለግል ነበር።

የመጀመሪያው አክፂያ(የተልዕኮ ስራ) በራንዶም  ካምፕ የተፈፀመው  በይካቲት 1942  ዓ/ም ሲሆን፤ 40 የግራ ክንፍ ፓርቲ አባላትን ያጠቃለለ ነበር።  ከሁለት ወር በኋልም እንደገና በአስር የሚቆጠሩ የዚህ አባላት ከቦታው ውደ አውሽቪፅ ካምፕ  እንዲሰደዱ ተደረገ።  በካምፑ ውስጥ የይሁዳዊያን፤   ጀርመናዊያን  ለመቃወም  የአንድነት ስራ እንዳይካሄ  ዮድንራትን ግሩፕ እንዲፈርስ አደረጉ።

በነሀሴ 16 ቀን 1942 ዓ.ም  ትልቁ ከራንዶም ጌቶ(ካምፕ)  የማባረር ድርጊት የተፈፀመው በዚህ ቀን ነበር። በነሀሴ መጨርሻ ወር በራንዶም ካምፕ 2,500  ይሁዳዊያን ቀሩ። ያ ትንሽ ካምፕ  የስራ መስሪያ መስክነት ተለወጠ። ከነሀሴ ወር 1942 ዓ.ም  እስከ ሰኔ 26 ቀን 1944 ዓ.ም ድረስ ጀርመናዊያን ከዚህ የነበሩ የራንዶም ይሁዳዊያን በዘዴ  ገደሏቸው። ግማሾች  ወደ ጋዝ መግደያው ተወሰዱ ግማሾች ደግሞ የግዴታ ስራ ለመስራት ተወሰዱ። ሌሎች ደግሞ በፖላንድ  እና በዩክሬናውያን ፖሊሶች ተገደሉ። ትንሽ የቀሩት ደግሞ በ 1944 በ  SS ሰዎች አማካኝነት ተገደሉ።