ቪልና

ማህደረ ትውስታቸው በሆፍ ሀካርሜል መካነ መቃብር ይገኛል።

ቦታ፦ ሊታ

ከሆሎኮስት(ሽዋ)  በፊት  በ 1938 የነበሩ ይሁዳዊያ፦ 100,000  ይሁዳዊያን ነበሩ።

 

በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በቪልና ከተማ  የሚኖሩ ይሁዳዊያን እደገት ከፍ እያለ የመጣው እና ከፍተኛ እድገት ላይ የደረሰው በዚህ ጊዜ ነበር። በዚህ ጊዜ በቪልና ከ 100,000   ይሁዳዊያን ሲኖሩ፤  በከተማው ከሚኖረው ህብርተሰብ ግማሾ ነበር።  ቪልና የሊታ ዋና ከተማ ብትሆንም ታዋቂው  የቅፅል ስሟ  "የሩሻላይም ሊታኢት"  እየተባለች ትጠራ  ነበር። ምክንያቱም ይሁዳዊያን በነበራቸው ተፅዕኖ እና ከፍተኛ ድርሻ ነበር። በቪልና  105 ፀሎት ቤቶች ነበሩ። የዘመናዊው የአውሮፓ ይሁዳዊያን የፖለቲካ ፣ ርዕዮተ ዓለም እና የሃይማኖት እንቅስቃሴ በቪልና ውስጥ ይንቀሳቀሱ ነበር።  

 

ቀደምት ታሪክ 

የቪልና ይሁዳዊያን ከግብር የባህር መዝገብ ላይ በከተማዋ  እንደተመዘገቡ የሚያሳቱት ሰነዶች ከ 1568 ዓ.ም አንስቶ  ነው።  ነገር ግን የታሪክ ተማራማሪዎች እንደሚገልፁት ከዚህ ዓ.ም በፊት ለብዙ አስር አመታት ይሁዳዊያን በከተማዋ እንደነበሩ ይገልፃሉ። በ 1633 ዓ.ም በቪልና ለሚኖሩ ይሁዳዊያን በከተማዋ በፈልጋቸው የንግድ ስራ ተሰማርተው እንዲሰሩ  እና በከተማዋ በፈለጉት ጎዳና እንዲኖር የተፈቀደላቸው በዝህ ዓ.ም ነበር። ምንም እንኳን ከማዕከላዊ አውሮፓ የቪሊኒየስ መልክዓ-ምድራዊ ርቀት ቢኖርም ፣ ከምዕራብ እና ከማዕከላዊ አውሮፓ የመጡ ይሁዳዊያን ወደ ከተማዋ ገቡ። በተላይ ከፍርናክፎር እና ከፕራግ እንደመጡ ይታወቃሉ።  በ 17 ክፍለ ዘመን በቪልና ከተማ 15, 000   ኖዋሪዎች እንደነበሩ እና ከኖዋሪዎች  3,000  ይሁዳዊያን እንደነበሩ ይታወቃል። 

በ 1974 ዓ.ም በራሻ እና በሊታ መካከል ጦርነት ስለተከፈተ፤  የራሽ ጦር ሀይል የሊታን ከተማ ስለተቆጣጠራት፤ ከዚያው ራሻንዊያን ለማስለቀቅ አመፅ ተነሳ።  የዚህ አመፅ የሊታ ዜጎች ዋና እንቅስቃሲያቸው በቪልና ነበር። በበሆኑም የይሁዳዊያን ወጣቶች በዚህ አመፅ ለመሳተፍ አብረው ተቀላቀሉ። ነገር ግን ይህ አመፅ በመውደቁ  የቪልና ከተማ በራሻ ግዛት ስር ሆነች። በዚህም ምክንያት በሊታ የሚኖሩ  የይሁዳዊያን የነበራቸው ደረጃ በጣም በመቀነስ እና ብዙ ጉዳት ደረሰቭባቸው።  ምክንያቱም በ 1794 ዓ.ም  የይሁዳዊያን ወጣቶች አብረው በአመፁ ስለተሳተፉ በቂም በቀል ጉዳት አደረሱባቸው።

የይሁዳዊያን የነበሩበት ደረጃ የተለወጠው በ 1812 ዓ.ም ነበር።  ይህም የሆነበት ምክንያት  የፈረንሳይ ጦር ሀይል  በናፖሊዮን መሪነት ሊታን በቁጥጥር ስራ ካዋሉ በኋላ፤ ብዙ የይሁዳዊያን  ወንዶች ወደ ራሻ ጦር ሀይል የፈረንሳይን ጦር ሀይል ለማጥቃት ተቀላልቀሉ። ከእንዚህ ይሁዳዊያን ብዙዎች ህይወታቸውን በጦርነቱ አጡ። ከዚህ የተነሳ በ 1814 ዓ.ም  የራሻን መንግስት ለይሁዳዊያን ነፃ የኢኮኖሚ ስራ እንዲኖራቸው አደረጉ።

በ 18 እና 19 ክፍለ ዘመን የቪልና ይሁዳዊያን ደረጃ በጣም ከፍ ያለ እና  በአውሮፓ የሚኖሩ ይሁዳዊያን የሀይማኖት መማሪያ መካከል   እንድትሆን አስችሏል።  ታላላቅ ሊቃውንቶች በቪሊና ነበሩ። በመሆኑም  በመሪ ራባናት ወይንም ሊቃውንቶች  እና በሌሎች ራባናት ይካሄድ የነበረው የሀይማኖት፤ የህግጋታ ክርክር እና የሀይማኖት አስተሳሰብ  ለየት ያለ እና በብዙ መንገድ ይሚታይ እንዲሆን ተፅዕኖ አሳድሯል።  በ 18 እና በ 19 ክፍለ ዘመነ በቪልና የነበሩ ታዋቂ ሊቃውንቶች  መካከል፦ ሀራብ ኤሊያሁ ቤን ሣሎሞን ዛልማን(የቪልና ሊቅ)፣ ሀራብ ፅቪ  ሂርሽ  ካኢድኖበር እና ሀራብ  ባሩህ ሀሪፍ ነበሩ።

የቪልና ሊቅ( ሀራብ ኤሊያሁ ቤን ሣሎሞን ዛልማን) ተፅዕኖ  ምክንያት   በቪልና ከተማ  የሚኖሩ ይሁዳዊያን በሁለት ተክፍለው፦ በሀሲዲም ዘርፍ የሚሄዱ እና የቪልና ሊቅ አመራር በሚቃወሙ መካከል ተከፍለው ከተማዋን የሀይማኖት ደማቅ መካከል አድርገዋታል።  በ 18 ክፈ ዘመን ለሁለት አስር ዓመታት ያህል እና በ 19 ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ  በሁለቱ የሀይማኖት ዘርፍ ተከታዮች በጣም የባሰ ብጥብጥ እና ጠብ ነበር። በሃሲዲም እና በተቃዋሚዎቹ መካከል የተነሳው ግጭት አንዳንድ ጊዜ ተቃዋሚዎችን ወደ እስር ቤት ለማስገባት በባለሥልጣናት መካከል በመሄድ እና የሐሰት ክሶችን በመክፍት ችግር ፈጥሯል።   እንዲሁም  በመውረስ እና በኢኮኖሚያዊ እና ቤተሰባዊ  ትስስር እንዳይፈጠር ወይንም እንዲያቋርጥ አድርጓል።  ይህ ቢሆንም በ 19 ክፍለ ዘመን በሁለቱ መካከል ሥምምነት ወርዶ  አብረው መኖር ቢጀምሩም፤ በዚህ ዘመን አንዳንዴ  ግጭቶች በሁለቱ የሀይማኖት ዘርፍ ተከታዮች  ይከሰቱ ነበር።

 

የቪልና ከተማ የይሁዳዊያን የፖለቲካ እንቅስቃሴ መካከል

ከመቶ ሀምሳ ዓመት በላይ ቪልና የይሁዳዊያን የሀይማኖት  ትልቅ መካከል  ሆና ይቆይታለች።  በ 19 ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ልዩ የይሁዳዊያን  የሀይማኖት ዘርፍ (ክስተት) ተከሰት።  ይህ ክስተት በጣም አስፈላጊነቱ እና ጉልህነቱ  በጣም ከፍ ያለ ነበር። ይህ ቢሆንም በከተማ በሚኖሩት የሀይማኖት ታከታይ ዘርፍ ላይ ብዙ ክርክር እና ተቃውሞችን መፍጠር ችሏል። (በይሁዳዊያን ዓለም ውስጥ ድንጋጤ እና አለመግባባትም አስከትሏል ፡፡)  በ 1842 ዓ.ም በይሁዳዊያን እንቅስቃሴ እጅግ ወሳኝ ከሆኑት ዐበይት ዓይነቶች መካከል፤ ለይሁዳዊያን ማኅበረሰብ ተብሎ የተመደበው በራሻ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገው ኢ፟ሀይማኖታዊ ትምህርት ቤቶች ሲቋቋሙ ነው ፡፡ አዲሱ የራሻ መንግስት በይሁዳዊያን  በትምህርት መስክ ትልቅ እምቅ አቅም ያለቸው መሆኑን ስለተረዳ፤ የራሻዊያን ዜጎች ለማድረግ በጣም ከፍተኛ ጥረትን አደረገ።  የመንግስቱ ዋና አላማም የክርስትና-ምዕራባዊያን ትምህርቶችን እንዲማሩ ነበር።    በ 1847 ዓ.ም በራሻ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ   በቪልና ከተማ ለራባናት መማሪያ ሴሚናር ተቋቋመ።  ከዚህ በተጨማሪ ኢሀይማኖታዊ የሆኑ ት/ቤቶች  በመቁቋማቸው፤ ይህ ድርጊት ወደ ሌሎች ከተሞች መሰራጨት ጀመረ። ለምሳሌ፦ ሊታን  እና ፖላንድን መጥቀስ ይቻላል።

ይሁዳዊያን ባደርጉት የትምህርት እንቅስቃሴ ምክንያት  በቪልና ከተማ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችም የበለጠ እያደጉ እንደመጡ ይታወቃል።  በ 1861 ዓ.ም በሶሻሊስት የሚያምኑ ይሁዳዊያን በቪልና መንቀሳቀስ ጀመሩ።  እንዚህ ሰዎች ደግሞ የተማሩ  በቪልና በተቋቋመው የራባናት ማሰልተኛ  ሴሚናር ሲሆን፤   በሶሻሊስት ሀሳቦች እና በይሁዳዊያን አስተሳሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳየት ሞከሩ። እንዲሁም  በ 20 ክፍለ ዘመን የሀይማኖታዊ ድርጅቶች በአውሮፓ መካከለኛ አገሮች እና በምስራቅ አውርፓ መንቀሳቀስ ጀመሩ። በ 19 ክፍለ ዘመን  በአስሩ ዓመታት መጨረሻ ላይ በቪልና ከተማ መስራት ጀመሩ።

የሶሻሊስት ይሁዳዊያን እንቅስቃሴ በ 1970 ዓ.ም በጣም  እንደተዳከመ እና በ 1980 ዓ.ም እንደገና በጠነከር ሆኔታ እንቅስቃሲያቸው ታድሷል። ስለዚህ ቪላና ዋና የሶሻሊስት ይሁዳዊያን እንቅስቃሴ መካከል  ነበረች። በዚህ ጊዜ በቪልና  ጠቅላላ ኖዋሪዎች  ከ 70,000 ሰዎች  በላይ ሲሆኑ፤  40%   ይሁዳዊያን ነበሩ።     

በ 1895 ዓ.ም የሶሻሊስት ሊቃናት ይሁዳዊያን ጉባኤ በቪልና ከተማ  ተካሄደ። በአውሮፓ ውስጥ ታላቁ የይሁዳዊያን  የሶሻሊስት ፖለቲካ  ንቅናቄ ቡድን "ባንድ"  በ 1897 በቪልና ከተማ  የይሁዳዊያን ሰራተኞች አማካንኝነት በተደረገው ስብሰባ ነበር የተቋቋመው፡፡  ከፖላንድ ዋና ከተማ ቫርሻ ጎን ለጎን ቪልና ዋና የቦንድ የፖለቲካ ንቅናቄ ስራ መካከል ነበረች።  ከዚህ ቦታም የፓርቲው ዋና ጽ / ቤቶችም ተቋቋሙ።

በቪልና ከተማ  ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሶሻሊስት ይሁዳዊያን ብቻ አይደሉም፤ የኦርቶዶክስ  ይሁዳዊያን ጭምር በዚህ ቦታ ሲንቀሳቀሱ ነበር።   ከእንዚህ የፖለቲካ ተንቀሳቃሶች መካከል አንዱ እና ከመጀመሪያዎቹ እና ትልቁ ቅርንጫፎች መካከል ሆብቤ ፅዮን የሚለው ድርጅት  በ 19 ክፍለ ዘመን በቪልና ከተማ ተቋቋመ። ሄርፄል የሚባለው የይሁዳዊያን መሪ በ 1903 ዓ.ም በቪልና ከተማ ለጉብኝት ሲመጣ፤ በሺ እሚቆጠሩ  ይሁዳዊያን  እርሱን ለመቀበል እና በደመቀ ድጋፍ ተቀባይነትን አግኝቷል። ሌላው የራሻ ጺዮናዊ  ዋና የድርጅቶች መስሪያ ቤቶች  በቪልና  ከአስር ዓመት በላይ ተቀምጠዋል።  እንዲሁ የፖአሌ ጽዮን መስሪያ ቤቶች ከዚህ ነበሩ።

በአንደኛ የአለም ጦርነት ሊታ  በጀርመን ጦር ሀይል ብትወረስም፤ ከጊዜ በኋላ የሯሷን ነፃነት አግኝታለች። ይህም የፖላንድ ጦር ሀይል አገሪቱን  እንዲቆጣጠር ሚና ተጫውቷል።   በእሆኑም ሊታ ከ 1914-1920 ዓ.ም በጦርነት ነበረች። ይህ ጦርነት አገሪቱን በጣም የኢኮኖሚ ውድቀት ሲያደርስ፤ ይሁዳዊያን በዚህ ጦርነት በጣም እንደተጎዱ እና በታላይ በቪልና የሚኖሩ ይሁዳዊያን በጣም ጥቃት እንደደረሰባቸው።  በቪልና የሚኖር የይሁዳዊያን ወጣቶች ወደ ጦርነቱ በመግባት የፖላንድን ጦር ሀይል ለማጥቃት ተዋግተዋል።  የይሁዳዊንያን ወጣቶች የፖላንድን ጦር አብረው ስለተዋጉ በ 1919 ዓ.ም  የፖላንድ ጦር ሀይል በቂም ምክንያት ወደ መቶ የሚቆጠሩ ከወንጌል ነፃ የሆኑትን በከተማዋ ዋና ጎዳና ላይ  ይሁዳዊያን ገደሉ ።

በ 1922 ዓ.ም ጦርነቱ ካበቃ በኋላ፤ እንደገና በቪልና ከተማ የሚኖሩ ይሁዳዊያን በጣም እያደጉ እና የበለፀጉ መጡ። በዚህ ጊዜ ቪልና ከእድገት እና ከብልፅግናዋ የተነሳ የሊታ የሩሳሌም እስከመባል ደርሳ ነበር።  በዚህም ጊዜ በቪልና ብዙ ለኢብራይስጥ መማሪያ ት/ቤት ሲከፈት፤  በይዲሽ መማር እና በኢብራይስጥ መማር በሚፈልጉት  መካከል ውስጣዊ ግጭት ተፈጠረ። ጺዮናዊ ተንቀሳቃሶች በኢብራይስጥ የሚሰጠውን ትምህርት ለማስፋት እና ለማሳደግ ሲፈልጉ፤  የቦንድ አባላት ደግሞ  የይዲሽ ባህል እና ቋንቋ ማሳደግ እንደለበት  ስለሚያምኑ ክርክር ተፈጠረ።  በ 1924 ዓ.ም  አለም አቀፍ የይዲሽ ቋንቋ ጥናት መዕከል  ተቋቋመ።

 

ከ 1920-1939 ዓ.ም( እስከ ሁለተኛው የአለም ጦነት)

በ 1939 ዓ.ም ሁለተኛው የአለም ጦርነት ሲፈነዳ  ነገሮችሁ ሁሉ ሳይታወቅ ተለወጡ። የሶቪዬት ህብረት የቀይ ጦር  ጦርነቱ እንደጀመረ ወደ ሊታ ከገባ በኋላ ሊታ በሶቪዬት ህብረት ስር እንድትሆን አደረገ።  ከዚህ ጦርነት የተነሳ የሊታ ከተማ ትልቅ ጥቃት ደረሰባት።  ነገር ግን ትልቁ የይሁዳዊያን ችግር የነበረ ፤ በጦርነቱ ምክንያት ይሁዳዊያን ከጀርመን ናዝም ለማምለጥ ሲሉ ከፖላንድ ወደ ሊታ ሲመጡ ነበር።  የራሻ አስተዳደር  ስልጣን ለሁለት ዓመት ያህል ቪልናን ይዞ ከቆየ በኋላ፤  በሰኔ 24 ቀን 1941 ዓ.ም የጀርመን ጦር ሀይል ቪልናን በቁጥጥር ስር አዋሏት። የጀርመን ናዚም የሚደግፉ ብዙ የሊታ ኖዋሪዎች፤ የጀርመን ጦር ሀይል አበባ ይዘው ተቀብሉት።  ወደ ከተማዋ በገቡ ቀን ጀመሮ በከተማው በሚኖሩት ይሁዳዊያን ላይ  ማቀብ ምድረግ ጀመሩ።  

በካምፑ የቀሩት የጺዮናዊ እና የቦንድ አባል መሪዎች ያለምንም ጦርነት ለጀረመን ናዚም እጅ እንደማይሰጡ ግልፅነበር።  በ 1942 ዓ.ም መሳሪያ  በመሰብሰብ እና በድብቅ ምስጢራዊ የጋር  ድርጅት መሰረቱ።  ነገር ግን ጀረመናዊ በነበራቸው የመርጃ ማግኛ ዘዴ ይህ ደርጅት እንደተቋቋመ ደረሱበት። ከዚህ በኋላ ይፅሀቅ ቫይትንብርግ የሚባለውን የድርጅቱን ሀላፊ ያዙት። ይህ በመሆኑም ይህ ምስጥራዊ ድርጅት  ይፅሀቅ ቫይትንብርግ ለማስለቅቅ በተደረገው የተቃውሞ ስራ ፤ የድርጅቱ አባላት ይፅሀቅ ቫይትንብርግ የያዙትን ወታደሮች እና ወደ ጋስታፖ መስሪያ ቤት የወሰዱትን ወታድሮች በመግደል እርሱን አስለቀቁት።

በዚህ ቀን ምሽት የጀረመናዊ የጦር ሀይል አዛዦች በቪልና ለሚገኙት ዮድንራት፤ ይፅሀቅ ቫይትንብርግ ግዴታ ይዘው ማምጣት እንዳለባቸው ትዕዛዝት ትቀበሉ። ይዘው ካለመጡት ግን በካምፑ የሚገኙ ይሁዳዊያን በምሉ እንደሚገደሉ ትዕዛዝ ሰጡ። ይፅሀቅ ቫይትንብርግ ኅብረተሰቡ እርሱ በሰራው እንዳቀጡ እና እንዳይሰቃዩ ሲል በራሱ እጁን ለጀርመን ናዚም ሰጠ። እርሱም በጋስታፖ የመመርመሪያ መስሪያ ቤት በስቃይ ተገደለ።  ሌሎች የድርጅቱ አባላት በቪልና አካባቢ ወደ ሚገኙት  ደኖች  በመሄድ፤ የሊታ ከፓርትዛናዊ  ድርጅት ጋር በመቀላቀል የጀርመንን ጦር ሀይል ለመዋጋት ተቀላቀሉ።

መስከረም አንድ ቀን በምስጥራዊ የይሁዳዊያን ድርጅት አባላት እና በጀርመን ወታደሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ጦርነት ከተከፈተ በኋላ፤ የጀርመን ጦር ሀይል ብዙ ጥቃት ደረሰባቸው። ምክንያቱም የእነዚህ ሰዎች ሀይል ግምት ላይ ባለማዋለች እና በመናቃቸው ፤ ብዙ ወታደሮች ተገደሉ። ስለዚህ ካፑን ትተው ሸሹ። እንደገና ደግም ይህ ድርጊት መስከረም 15  እን ተከሰተ። የተከሰተበት ምክንያትም ጀረመናዊያን ከ 10,000 የሚሆኑ ይሁዳዊያን ከካምፑ ወደ ጋዝ ማጥፊያ ለመስደድ ስላሰቡ ነበር።  የጀርመናዊያን የመረጃ ማሰባሰቢያ ስርዓት ክፍል የይሁዳዊያን ምስጥራዊ ድርጅት  አባላት በካምፑ ዙሪያ ቦንብ እንደቀብሩ ስለተረዱ ያሰቡት እቅድ እንደገና ሰረዙት።

ይህ ከሆነ በኋላ የይሁዳዊያ ምስጥራዊ ድርጅት አባላት የይሁዳዊያን የተሰበሰቡበትን ካምፕ ትተው በደን ወደ ሚገኙት  ፓርትዛኒም ሄደው ተቀላቀሉ። ከሳምንት በኋላ ልዩ ትዕዛዝ በመውጣት በቪልና የይሁዳዊያን በመሰብሰቢያ የሚገኙትን ይሁዳዊያን እንዲለቁ ሆነ።