ቡርሽቴይን
ማህደረ ትውስታቸው በሆፍ ሀካርሜል መካነ መቃብር ይገኛል።
ቦታ፦ ምስራቅ ጋሊሲያ፣ ፖላንድ
ከሆሎኮስት(ሽዋ) በፊት በ 1938 የነበሩ ይሁዳዊያ፦ 3581 ሰዎች

የህብረተስቡ ታሪክ፦ ይሁዳዊያን ሰፍረ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀመሮ፡
ቡርሽቴን የሚባለው ቦታ በፅሁፍ ላይ ተፅፎ የሚገኘው ከ 1629 ዓ.ም ጀመሮ ሲሆን፤ የሚታወስበት ምክንያትም በፖላንድ እና በታታሪም መካከል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ነበር። ከዚህ በፊት ግን በዚህ ቦታ ኖቫ ሲዩሎ የሚባል ቦታ በ 1550 ዓ.ም እንደነበረ ይታወሳል። እስከ 19 ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ከተማ ቡርሽቴይን ብዙ ባለስልጣኖች የተቀያየሩባት ከተማ ነበረች። በ 17 ክፍለ ዘመን በነበርው ጦርነት የከተማዋ ህዝብ በጣም ስለተጎዳ እና ስለተሰቃየ በ 1681 ዓ.ም ከግብር ነፃ እንድትሆነ ተደረገ። ይሁዳዊያን ወደዚህ ቦታ የመጡት በ 17 ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ እንደሆነ ሲገመት፤ አብዛኛዎች በንግድ ስራ ሲተዳደሩ ነበር። ከ 1641-1642 ዓ.ም ድርስ ሁለት በቦታው ይኖሩ የነበሩ ይሁዳዊያን ከጋዳንሸ ጋር በንግድ እንደሰሩ ይታወቃል። በ 1797 ዓ.ም የቡርሽቴይን ከተማ ኖዋሪ ይሁዳዊያን በቤተሰባቸው ቁጥር ግብር በአጠቃላይ 86 ዝሁቪም እንድከፈሉ እና አንድ ዛልማን ይሚባል ይሁዲ 86 ዝሁቪም እንደከፈለ ይታወቃል። በ 18 ክፍለ ዘመን መጀምሪያ የይሁዳዊያን ህብርተሰብ በአንድ በመደራጀት መካነ መቃብር ለራሳቸው እንዲኖር እና በዚህ አካባቢ የነበሩ ይሁዳዊያን በጦርነቱ ምክንያት በታታሪም እጅ ስለታያዙ ግዴታ እነርሱን ማስለቀቅ ነበረባቸው። ስለዚህ የእስረኞችን ለማስለቀቅ የሚያገለግል ተቋማት ወይንም የሚመልስ ኮሚቴ የተቋቋመበት ጊዜ ነበር። በ 18 ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ራቢ ፅቪ ቤን ናታን አሸከናዚ የሚባለው ራብ ህብረተሰቡን በሀይማኖት ተቋም በመስራት ሲያገለግል ነበር። በዚያን ጊዜ የይሁዳዊያን ህብርተሰብ ትልቅ ተፅኖ ለመማር የተመቻቸ እና በ 1714 ዓ.ም በሪይሰናገር በተደረገው ስብሰባ እና በመጨርሻ የፕላንድ ግዛት ላይ ይሁዳዊያን የነበሩበት ደርጃ የተስተካከል እንደነበር ይታወቃል። ይህም በነፃነት በንግድ እንዲሰማሩ እና ቤት ከደንጋይ መስራት እዲችሉ የተፈቀደበት ጊዜ ነበር። እነዚህ ቤቶች እስከ ሁለተኛው የአለም ጦርነት እንደበሩ ይታወቃል። ነገር ግን በ 1772 ዓ.ም አውስትራሊያ የቡርሽቴን ከተማ ስትወር የይሁዳዊያን ኖሮ እየከፋ መጣ። ይህም በጋሊሲያ በሚኖሩ ይሁዳዊያን ላይ በተደረገው የግብር ክፍያ እና ሌሎች የተከለከሉ ነገሮች ነበሩ። ከዚህም የተነሳ የቡርሽቴይን ከተማ ይሁዳዊያን በከተማዋ በአስተዳዳሪዎች የታውቀ ራብ በገንዘብ እንዳያሰሩ ተከለከሉ። ነገር ግን ይሁዳዊያን ይህን ትዕዛዝ ሳያከብሩ ራቡ በነፃ ህብረተሰቡን ሲያገለግል ነበር። በ 19 ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በተላይ በ 1868 ዓ.ም ከተማው በጣም እያደገች ስትመጣ፤ ይሁዳውያ ቁጥርም እየጨመረ መጣ። ስለዚህ በቡርሽቴይን ከተማ የሚኖሩ ይሁዳዊያን ቦታ በመግዛት ርስት እንዲኖራቸው ፋቃድ ነበራቸው። በ 40ቹ ዓመታት በ 19 ክፍለ ዘመን አንድ ዶክቶር በከተማ መቀመጥ ከጀመረ በኋላ ከተወስኑ ዓመታት በኋል ሌላ አንድ ተጨማሪ ዶክትር ይሁዲ መጦ አብሮ መኖር ጀመረ። በ 20 ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በተደረገው የህዝብ ቆጠራ፤ 762 ይሁዳዊያን በንግድ ስራ ተሰማርተው እንደሚሰሩ፤ 84 ባለ እጅ ጥበቦች፤ 23 ሰዎች ባለ ነፃ ባለሙያዎች እና 131 በሌላ ስራ የተሰማሩ ይሁዳዊያን እንደነበሩ ይታወቃል። በከተማዋ ዘመናዊ የህል መፍጫ ወፍጮ ነበር፤ ይህ ወፍጮም በፍሪድላንደር በተባለ በተሰብ ስር እንደነበረ ይታወቃል። ከዚህ የትወሰኑ ይሁዳዊያን ሲሰሩ እንደነብር ይታወቃል። በዚህ ጊዜ በቡርሽቴይን ሁለት ባንኮች ነበሩ፦ አንደኛ በ CIA የተመሰረተ ባንክ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ኮፓራቲቪ ነበሩ። እነዚህ ሁለት ባንኮ በ 1918 ዓ.ም በአንድ በመሆን ባንክ አሽራኢ በመባል ስማቸው ተሰየመ ወይንም ተቀየረ። የእጅ ጥበብተኞች በ 20 ክፍለ ዘመን በአንድ በመተባበር ስማቸውን "የታታሪዎች እጅ" በማለት ሰየሙ። በቡርሽቴይን የህዝብ አገልግሎቶች፡ መካነ መቃብ ኮምፓኒ፣ የኦሪት ትምህርት፣ የታመመ ጥየቃ፣ ለተቸገሩ መፅዋት መስጫ ተቋም፣ አስተማሪዎች እና የሴቶች ድርጅት ናቸው። ከላይ ከተጠቀሰው የፀሎት ቤት ተጨማሪ፤ በ 19 ክፍለ ዘመን ትንሽ ፀሎት ቤት፤ የኦሪት መማሪያ(ቤት ምድራሽ) እና 8 ለአክራሪዎች የፀሎት ቤት እና ለባለ እጅ ጥበብተኞች ተገንብተዋል። ከ18 ክፍለ ዘመን እስከ 20 ክፍለ ዘመን ድረስ በቡርሽቴይን የነበሩ ራባናት፡ ራብ ፅቢ ሂርሽ ቤን ናታን አሽከናዚ ከእርሱ በኋላ ራብ ዮሴ ቱሚም ተመርጠ። ከዚህ በኋላ የሀይማኖት ልዩ ዳኛ(ዳያን)ሆኖ በ በስታንሲላው አገለገለ። ከዚህም በኋላ የራብ ራሽ ስራ ድርሻ ወደ ራብ ዮሴፍ ሽቫርፅ ተላለፈ። ከእርሱን በኋላ ራብ ሜኢር ላንዳ እስከ 1898 ድረስ አገለገለ። በህይወት እያለም ልጁ ራብ ሞሼ ላንዳ በምትኩ ተመረጠ። እነዚህ ሊቃውንቶች የሞቱ በ 1907 ዓ.ም ነበር። ከሞቱ በኋላም በራብ ምርጫ ምክንያት በህብረተሰቡ ብጥብጥ ተነስቶ- ከራብ ሞሼ ከሁለቱ ልጆች የትኛው ይሁን(ራብ አይዝክ ወይንም ራብ ኤርፅ) በማለት ብጥብጥ ከተነሳ በኋላ ራብ ኤርፅ ላንዳ በከተማዋ ለሚኖሩ ይሁዳዊያን ሆኖ ተመረጠ። እርሱም የይሁዳዊያን ጭፍጨፋ እስከሚጀመር(ሽዋ) ድረስ ህብርተሰቡ አገለገል።
በከተማዋ የስትሪን ሀሲዱት ተከታዮች ተስፋፍቶ ነበር። ይህ የሃይምኖት ዘርፍ በመጀምሪያ የጀመረው ራቭ ናሁምቼ በራንስዊያን ይባል ነበር። ከእዚህ በኋላ በ 1865 ዓ.ም በ 18 ዓመቱ አድሞር ሆኖ ተመረቀ። የሀሲዱት እና የካባላ(የሚስጥራዊ) መፃሀፎችን ፅፏል። ለምሳሌ "ኤምሪ ቶቭ" ፣"ኤምሪ ብርሀ" ፣ "እምሪ ሀይም" እና "ኤምሪ ራፆን" ናቸው። በ 1914 ዓ.ም ቡርሽቴይንን ለቆ ወደ ስታንሲላቦብ ሄዶ መኖር ጀመረ። ከዚህ በኋላ በ 1915 ዓ.ም ከዚህ አለም ተለየ። ከዚህም በኋላ የልጅ ልጁ ራብ ሞሼ እርሱን የጀመረውን መንግድ እንደገና በ 1935 ዓ.ም ካደሰው በኋል በሽዋ ሞተ። ከስትራቲን የሀሲዲም ተከታዮች በተጨማሪ የበልዝ እና ቾርኮቭ ሀሲድሞች በከተማው ይገኙ ነብር። በ 40- ዓመታት በ 19 ክፍለ ዘመን በቡርሽቴይን ብዙ የተማሩ ነበሩ። ከእነዚህም ሁለት ወንዶች ወደ ክርስትና ሀይማኖት ከገቡ በኋል በፖላንድ ባህል ትምህርት እና በክብር ትልቅ ደረጃ ደርሰዋል። አንደኛው አድዋር ሪትነር ሲባል፤ ሁለተኛው ደግሞ ሎድቢክ ፒንከል ሲባል፤ የፖላንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ታሪካዊ ታሪክ የታወቀ ታዋቂ ተመራማሪ ነበር። እንዲሁም ከ 1892- 1927 ዓ.ም ድረስ በሌቡብ ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር ሆኖ እንዳገለገለ ይታወቃል። ምንም የራብ ሞሼ ቢቃወምም በ 1898 ዓ.ም ለይሁዳዊያን ልጆች ብሎ ትምህርት ቤት በባሮ ሂርሽ እገዛ እና አማካይነት ተቋቁሞ በመጀመሪያ ዓመት 135 ይሁዳዊያን ተማሪዎች ነበሩ።
ይህ ት/ቤት በ 1902 ዓ.ም የህዝብ መብት ተቀበል፡፡ በ 1902 ዓ.ም ከተቀበለ በኋላ፤ በአመቱ አዲስ ቦታ ተገዝቶ የተማሪዎች ቁጥር ወደ 214 ተማሪዎች አደገ። አብዛኛው ተማሪዎች የመጡት ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ይሁዳዊያን ቤተሰቦች ስለመጡ ለ 80 ተማሪዎች ምሳ በነፃ ይሰጣቸው ነበር። እንዲሁም ለ 100 ተማሪዎች ደግሞ በልብስ እና የመማሪያ ማቴሪያ እገዛ የደረግላቸው ነበር። ከዚህ በተጨማሪ ከትምህርት ቤቱ አጠገብ ለታላልቅ ሰዎች የትምህርት ስልጠና ተከፈቶ፦ የልብስ ስፌት ት/ቤት ተከፍቶ ለሶስት ዓመት ይማሩ ነበር። በ 1909 ዓ.ም ሌላ ትምህርት ቤት ተቁቋመ። በመጀመሪያ ዓመት 29 ተማሪዎች ተማሩ። በቡርሽቴይን ከተማ የጽዮናዊነት እንቅስቃሴ የተቋቋመው በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ነበር። ከዚህ በኋላ ነበር ኢጉድ ሆብቤ ፅዮን የሚለው ድርጅት የተቋቋመው። በ 1900 ዓ.ም ዶ/ር ዳቪድ ሜልፅ በቡርሽቴይን መኖር ጀመረ፤ በዚህም ምክንያት እየፅዮናዊ እንቅስቃሴ በጣም እየጠነከረ መጣ። እርሱም በህብረተሰቡ ተመርጦ በ 1908 ዓ.ም በጋሊሲያ በተካሄደው ኮንፍረንስ ላይ ይሁዳዊያን ወክሎ በሉቦብ ከተማ ቀርቦ ነበር። ከዚህም በኋላ በ 1912 ዓ.ም ፖአሌ ፅዮን የሚለው ድርጀት ተቋቋመ። ከዚህ በኋል በቡርሽቴይን ከተማ የተለያዩ የግድያ እና የዝቃይ ሆኔታዎች ዪክሬናዊያን በሁዳዊያ ላይ ተከስተዋል። በነሀሴ 1898 ዓ.ም በተደረገው የይሁዲ ነጋዴ እና ዩክሬን ገበሬ ገዥ ጠብ ምክንያት ይሁዳዊያን እና ዩክሬያንዊያን ተጣሉ። ከዚህም የተነሳ 10 ይሁዳዊያን ታሰሩ። ከዚህ በኋል ይሁዳዊያን በማሰቃየት እና ቤታቸው በመግቫት ዘርፋ ተጀመረ። በዚህ ጠብ ምክንያት የራብ ምሼ ላንዳ እጅ ተሰበረች እንዲሁም የልጅ ልጁ ተደበደበ። በመጀመሪያው የአለም ጦርነት በመጀምሪያዎቹ ቀናት ብዙ ይሁዳዊያን ከራሻዊያ ስለፈሩ ተሰደዱ። በቦታው የቀሩት ይሁዳዊያን ከራሻዊያን ወታደሮች ብዙ ስቃይ ደረሰባቸው። በ 1914 ዓ.ም ከተማዋ ተቃጠለች። ኩዝካዊያን በከተማዋ ላይ በጣም የከፋ ድርጊት አደረጉ። አንድ ኩዝካዊ አንዲት ይሁዳውያን ልጅ አገረድ ሊደፍር ሲያባራት፤ ከፀሎት ቤት ገባት የ 70 ዓመት ሽማግሌ አዳናት። ነገር ግን ይህ ይሁዲ ተደብድቦ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሞተ። በጦርነቱ መጨረሻ ላይ የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ መጦ በድምሩ 7 ይሁዳዊያን ሞቱ። በእነዚያ አስቸጋሪ ቀናት በዶክተር ወልፍ ሽሞራክ አማካኝነት የሚመራ የእርዳታ ኮሚቴ ይሠራ ነበር፡፡
በሁለቱ የአለም ጦርነት መካከል
በዩክሬናዊያን ግዛት ዘመን ብዙ ይሁዳዊያን ከጥቅምት 1918 ስከ ነሀሴ 1919 ዓ.ም ድረስ በሚኖሩበት አካባቢ ባለስልጣኖች ስቃይ ደርሶባቸዋል።
በሶቪዬት-በፖላንድ ጦርነት ወቅት የፔትሩራ ሠራዊት ከተማዋን ለትንሽ ቀናት ተቆጣጥሮ 11 ይሁዳዊያን ገድሏል ፡፡ ከጦርነቱ በኋላ የቡርሽቴይን ከታማ የሚኖሩ ይሁዳዊያን ከተማዋን ለቀው ወደ ሊለአ ቦታ ተሰደዱ። በአጠቃላይ በከተማዋ የቀሩት ይሁዳዊያን 1000 ሰዎች ነበሩ። 400 ሰዎች በከተማዋ አካባቢ በሚገኙ ገጠሮች የሚኖሩ ይሁዳዊያን ወደ ከተማዋ መጡ።በ 1921 ዓ.ም ከተማው ለሶስተኛ ጊዜ ተቃጠለች። በዚህ ጊዜ ጆይንት ለብዙ ይሁዳዊያን አግዟል። እንዲሁም በከተማው የነበሩ ይሁዳዊያ እና አሁን በአሜርካ ኖሮዋቸውን ያደረጉ ይሁዳውያን የገንዘብ እርዳታ ለከተማዋ ኖዋሪዎች አደረጉ። ከዚህም በእሳት የተቃጠለው እርዳታ የተነሳ በከተማዋ የሚገኘው ፀሎት ቤት እንደገና ተገነባ። ለእርዳታ ከተቋቋሙት ተቋሞች ከ 1936-1937 ብድር ሲሰጥ የነበረው ተቋም፤ በ 30 ዓመታት ኩፓት ግሚሉት ሀሲዲም የተባለው የእርዳታ መስጫ በጣም ከፍተኛ አስተዋፆ አድርጓል። ይህም ተቋም ለ 317 አጋዞች ታላላቅ ነጋዴዎች ብድር አበድሯል። በመጥኑ በንግድ ለተሰማሩ ለ 202 ሰዎች እና ለእጅ ጥበብተኞች ደግሞ ለ 74፤ ለገበሬዎች ደግሞ 20 እና ለተራ ሰራተኞች 10 እንዲሁም ለሌሎች 11 ሰጧል። ከባለሙያ ምሁራኖች ፣ ከብዙ ትላልቅ ነጋዴዎች እና ከብዙ ጥሩ ሥራ ፈጣሪ የእጅ ባለሞያዎች በስተቀር ሌሎች ሁሉም አድማጮች የገቢውን ብድር እንደፈለጉ ከላይ ከተመለከቱት መረጃዎች መረዳት ይቻላል ፡፡ በሙያዊው አስተዋይነት መካከል ሶስት ዶክተሮች ፣ የእንስሳት ሐኪም ፣ ወደ 10 የሚሆኑ ጥበቆች እና በርካታ መምህራን ነበሩ ፡፡
ይሁዳዊያን በከተማው ውስጥ በሦስቱ ብሔረሰቦች መካከል በተደረገ ስምምነት መሠረት በከተማው ውስጥ የተወከሉ ሲሆን እያንዳንዱ የከተማዋ ግዴታ መፈፀም አለባቸው።
አንድ ከይሁዳዊያን ህብረተሰብ ለብዙ ጊዜ የከተማ አስተዳደሩ አባል ሆኖ ያገለግል ነበር። ለማህበረሰቡ የተደረጉት ምርጫዎች በፓርቲዎች ላይ አልተካሄዱም ፡፡ የኅብረተሰቡ ኃላፊ ወይም የሕብረተሰቡ ከፍተኛ አባል ዴቪድ ኔብገርገር የተባለ ሀብታም ዩዳዊያን ለብዙ ዓመታት አሲያገለግል ቆይቷል፡፡ ለማህበረሰቡ ፍላጎቶች ገንዘብ ማሰባሰብ ችሏል ፣ አልፎ ተርፎም የገንዘብ መዋጮ አድርጓል። አብዛኛዎቹ የይሁዳዊያን ሕፃናት በዚያ የፖላንድ ህዝባዊ ትምህርት ቤት ያጠናሉ። ከዚህ በኋላ ደግሞ ተጨማሪ የኢብራይስጥ ትምህርት ቤት ተቋቋመ። በፖላንድ የሚገኙት የይሁዳዊያን ፓርቲዎች በከተማው ውስጥ የተወከሉ ነበሩ። የጄኔራል ጽዮን ፓርቲ ቅርንጫፍ ከቀድሞዎቹ እና በጣም ኃይለኞቹ ነበሩ። በ 1923 ዓ.ም የፖአሌ ፅዮን ፓሪቲ ተቋቋመ። ምክንያቱ በስሙ በቅርብ የኮሚኒዝም ኮሚዩኒኬሽንን በማራመድ ባለሥልጣናት ተጠርጥሯል ፡፡ ስልዚህ በሌላ ስም ልምድ የለላቸው የሰራተኞች ማህበር (ኢጉድ ሸል ፖአሊም ብልቲ ሚክፆኢም) ተባሉ። በዚህ ዓመትም ኢትሀዱት ድርጀት ከተቋቋመ በኋል፤ ሀፖኤል ሀሚዝራሂ እና ሀርቢዚዮኒስቲም ተቋቋሙ። ከወጣቶች እንቅስቃሴ ተቋሞች መካከል፦ በ 1924 ዓ.ም ጎርዶኒያ፣ በ 1930 ኬን ቤታር እና በዚህ ጊዜ የወጣቶች ኬን ኖአር ሀፅዮኒ የተባለ ተቋም ተደራጅቶ፤ ከዚህ ቦታ አጠገብ የሙያ ትምህርት ማስልጠኛ ተከፈተ። በቡሻንቲን ውስጥ የተወሰኑ ይሁዳዊያን ሕገ-ወጥ የኮሚኒስት ፓርቲ አባላት ነበሩ። ከእነዚህም አንዱ ወደ ሶብዬት ህብረት በ 1930 ዓ.ም ሸሽቶ ሄደ። ከዚያም በ 1934 ዓ.ም ለ 8 ዓመታት የስራት ተፈረደበት። በቡርሽቴይን ከተማ የፖአሌ ፂዮን የባህላዊ ትምህርት በጣም ከፍተኛ ተፅኖ ነበረው። ከዚህም ቦታ አጠገብ የድራማ ማስተማሪያ ቤት እና ከሚያተርፉት-በገቢያቸው ገንዘብ መጽሐፍት ቤት በ የ.ለ. ፔረፅ ስም ከሀባሮን ሂርሽ ከአንደኛ ደረጃ ትም/ቤት አጠገብ ተከፈተ። በ 1914 ዓ.ም መስራት አቆመ። ከቤተ መጽሐፍቱ ቀጥሎ የንባብ ክፍል ፣ የመማሪያ አዳራሽ እና ቲያትር ቤት ነበሩ ፡፡ ስለ ጽዮናውያን የተለያዩ የፖለቲካ አባሎች ሀይል ለፅዮናዊያን የግ=ኮንግሬስ ምርጫ ውጤት ብዙ መማር እንችላለን፡፡
ሁለተኛው( II) የአለም ጦርነት፦
ሁለተኛው የአለም ጦርነት እንደፈነዳ፤ ብዙ ይሁዳዊያን ወጣቶች ወደ ፖላንድ የጦር ሀይል እንዲዘምቱ ተደረገ። የተወሰኑትም በምርኮ በጀረመናዊያን እጅ ከወደቁ በኋል ህይወታቸውን ጠፋ። ሌሎች ይሁዳዊያን በፖላንድ ልዩ ጦር ክፍል እንደነበሩ እና በሶቢዬት ጦር ሀይል ምርኮ እንደሆኑ እና ከእንዚህ መካከል 3 ሞተው የተገኙት ወታደሮች የቡርሽቴይን ከተማ ኖዋሪ ነበሩ። የቀይ ጦር (ሀፃባ አዶም) በ 18.09.1939 ወደ ቡርሽቴይን እንደደረሰ ይታወቃል። በከተማው የሚኖሩ ይሁዳዊያን ይህን ጦር ወደ ከተማዋ ሲገባ በጣም ደስ ብሏቸው ነበር። ምክንያቱ ይዩክሬይን ጦር ሀይል ብዙ ሲያሰቃያቸው ስለነበር፤ አዳጋው ስላለፍ ነበር። ከዚህ በኋላ አንዳንድ ይሁዳዊያን በመዘጋጃ ቤት ተቋማት ውስጥ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል ፡፡ በ 1940 የፀደይ ወቅት የመታወቂያ ካርዶች በሚሰራጩበት ወቅት ፣ ቀደም ሲል 60 የሚሆኑ ሀብታም የነበሩ ይሁዳዊያን ሰብዓዊ መብታቸውን የሚገድቡ አንቀፅን ጨምሮ የምስክር ወረቀት አግኝተዋል ፡፡ በ 1940 ዓ.ም በኢኮኖሚ ምክንያት ተንቀሳቃሽ ፓርቲዎች እንዲታገዱ ሆነ። ከእነዚህም ትኑአት ሀኖአር ሀፅዮኒ የተባለው የወጣቶች ተንቀስቃሽ ፓሪቲ እና የተወሰኑ ቤተሰቦች እንደነበሩ ይጠቀሳሉ። በ 22.06.1941 ዓ.ም ጦርነቱ በጀረመን እና በሶብቪዬት ህብርት ከፈነዳ በኋላ ብዙ ይሁዳዊያን ወደ ሶቪዬት ጦር ሀይል ሄደው ማገልገል ጀመሩ። በ 02.07.1941 የጀርመን ጦር ሀይል ወደ ሮአቲን ቢደርስም፤ ከሁለት ሳምንት በኋላ ነው የጀርመን ተወካዮች ወደ ቡርሽቴይን ከተማ የመጡት። በዚህ ጊዜ ተወሰኑ ዩክሬያንዊያን ሰዎች በአንድ ላይ በመሆን በይሁዳዊያን ላይ ጥቃትን በማድረስ እና ንብርታቸውን ይወስዱ ነበር። ነገር ግን በ 20.07.1941 በጀረመናዊያን ድጋፍ የዩክሪዬን ፖሊስ ሀይል በቦታው የሚገኙት ይሁዳዊያን ብዙ ጥቃት አደረሱባቸው። ብዙዎቹ ከፀሎት ቤት እንዲገቡ በመታዘዝ እና ከዚያው ተደበደቡ። በ 1941 ዓ.ም 8 ሰዎችን ያካተተ ዮድንራት እንዲቋቋም ትዕዛዝ ተሰጠ። ይህን ዮድራንት የሚያስተዳድረው ሊቀ-መነበር ሊፋ ሾሜር ሲሆን፤ አብረውት ከተመረጡት መካከል፦ ሚና ቶቪአስ፣ ፊልፕ ቶቪአስ፣ እና ይሁዳ ኤርሽ ፊሽማን ይባሉ ነበር። አላማቸውም በከተማው የሚኖሩትን ይሁዳዊያን ምን ያህል እንደሆነ ለመመዝገብ ነበር። በነሀሴ አጋማሽ ላይ ይሁዳዊያ 3 ሚልዮን ሩባል እንዲከፍሉ እዳ ተጣለባቸው። ስለዚህ ዮንድንራቶች ለጀረመኖች የይሁዳዊያን ገንዘብ እና ንብረተ፣ ጌጣጌጥ፤ የብር እቃ፣ ሻይ እና ቡና ማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው። በመስከረም ወር በ 1941 ዓ.ም ይሁዳዊያን በታላላቅ ጎዳና የሚኖርበትን ቤት እንዲለቁ ትዕዛዝ በመሰጠቱ፤ የይሁዳዊያን ቦታ አንድ አካባቢ ሆነ። ከዚህ በተጨማሪ የተከለከሉት ነገሮች፦ ከከተማዋ ውጭ እንዳይወጡ፤ በመኪና መስመር ዳር ለሰው መሄጃ በተዘጋጀው መነገድ እንዳይሄዱ እና የማጌን ዳቪድ ኮከብ ያለበት ልዩ ምልክት ማድረግ አለባቸው። እንዲሁም ዮድንራቶች በየቀኑ የተወሱ ስዎችን ልግዴታ ስራ እንዲመጡ ትዕዛዝ ስለተሰጣቸው ግዴታ ማቅረብ ነበረባቸው። እነዚህ ሰዎች በድልድይ ጥገና እና የመኪና መንገድ እንዲሰሩት ይገደዱ ነበር። እንዲሁም በ 1941 ዓ.ም በአስር የሚቆጠሩ ብዙ ወጣቶች ተይዘው ወደ ግዴታ ስራ በታርኖፖል አካባቢ እንደተወሰዱ ይታወቃል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ለቡርሽቴን ከተማ ይሁዳዊያን ለስራ ተገደው የተወሰዱ ሰዎች እንደሞቱ መርዶ እንደደረሳቸው ይታወቃል። ከ 1941-1942 ዓ.ም ድረስ በቡርሽቴይን የሚኖሩ የይሁዳዊያን ችግር የበለጠ እየባሰ እንደመጣ እና አብዛኛዎች በራብ እንደሞቱ ይታወቃል። የመጀምሪያው የዮድንራት ሊቀመነበር ሀላፊነቱን እንደተቀበለ፤ ወደሌላ ቦታ በመሄድ ሲሸሸግ፤ በእርሱ ፈንታ ሚና ቶቢአስ ተመረጠ። እርሱም ጀረምናዊያን በይሑዳዊያን ንብረት ላይ በጠየቁጥ ጓዳይ ፍቃደኛ ነበር። ነገር ግኝ 250 ሰዎችን ለግዴታ ስራ እንዲያመጣ ሲታዘዝ፤ እንቢ በማለት ህብርተሰቡን ከፀሎት ቤት በመሰብሰብ ከስራ መልቀቁን እንዳስታወቅ በታሪክ ይታወቃል። ለህብረተስቡ ችግር እና መፍትሄ ለማግኘት ባደረገው ነገር በከተማው የሚኖሩ ይሁዳዊያን በጣም ከፍተኛ ድጋፍ አገኘ። በእርሱ ፈንታም የዚህ ስራ ሀላፊነት ፊልፕ ቶቢአስ በመቀበል፤ ጀርመናዊያን ያሉትን ትዕዛዝ ካለውድ በግድ እንደፈፀመ ይታወቃል። በፀዳይ እና በበጋ እራት በ 1942 ዓ.ም ህይወታቸውን ለማትረፍ በጣም በየቀኑ መፍትኈ ሲፈልጉ ነበር። ወጣቶች ወደ ሮማንያ ደንበር ለመድረስ ሲሞክሩ በመያዛቸው ተገደሉ። እንዲሁም በከተማው ይሁዳዊያን የመሸሸጊያ ቦታ ለማግኘት በየቀኑ ሲፈልጉ ነበር። ነገር ግን ዩክሬያናዊያ ለጀርመናዊያን ይሁዳዊያን የት እንዳሉ ስለሚናገሩ ችግሩ በጣም የከፋ ነበር። በመስከረም እና በጥቅምት ወር በ 1942 ዓ.ም የቡርሽቴይን ከተማ ይሁዳዊያን በመያዝ ወደ ሮአቲን ካፕ ተወሰዱ። 200 ይሁዳዊያን በ 21.09.1942 ዓ.ም ወደዚህ ቦታ ተወስደዋል። በ 15.10.1942 ዓ.ም የቡርሽቴይን ይሁዳዊያን በሙሉ ከተማዋን ለቀው ወደ ቡካቻኩዋዛ ወደተባለ ካምፕ እንዲሄዱ ተገደዱ። ይህ ስደት ብዙ ችግር፣ ስቃይ እና የንበርት ዝርፊያ የተሞላበት ነበር። ብዙዎች ወደ ዚህ ቦታ ለመሄድ ስላልፈለጉ በአካባቢው ወደሚገኙ ከተሞች ሄዱ። ነገር ግን የጀርመናዊያን እና ዩክሬያዊን ፖሊሶች በሄዱበት እየተከተሉ እና በዓካባቢው በሚገኙ ገበሬዎች በመረዳት ከተሸሸጉበት ፍለጋቸውን አልተውም። ስልዚህ ከተያዙት ግማሾች በቦታው በገበሬዎች እጅ እንደተገደሉ ይታወቃል። በከተማው የቀሩት ይሁዳዊያን 30 ሲሆኑ፤ እነዚህም ይሁዳዊያን በመነገድ ስራ እንዲሰሩ እንዲያስተካክሉ ይታዘዙ ነበሩ። ከወር በኋላ ግን ወደ ሮአቲን ካምፕ ተወሰዱ። ከእነዚህ ግን ትንሾች ወዲዝህ ከመላከቸው በፊት ወድሌላ ቦታ ተሸሽገው ሄዱ።
የቡርሽቴይን ይሁዳዊያን ወደ በልዥፅ የጋዝ መግደያ ካምፕ በ 26.10.1942 ዓ.ም ነበር። ከ 1943-1944 ዓ.ም በአለው ጊዜ እና በ 27.07.1942 ዓ/ም እስከ ሚለቅቁ ድረስ የቡርሽቴይን ከታማ ይሁዳዊያን ህይወታቸውን ለማድን ሲታገሉ፤ በመሸሸጊያ ቦታ ሲሸሸጉ፣ እና በደን ውስጥ ተሸሽገው እንደቆዩ ይታወቃል። የተወሰኑ ክርስቲያኖች የሚያውቋቸውን የሁዳዊያን በህይወት ለምዳን ከቤታቸው አስገብተው ሲያዱናቸው፤ አብዛኛው የከተማ ህብረተሰብ ግን ይሁዳዊያን ከተሸሸጉበት ቦታ በመግለፅ በይፋ ንዲገደሉ ያሉበትን ቦታ በምመፈለግ ሲይሳድዷቸው ነበር። በአንድ ወቅት ጀርመናዊያን የዩክሬን ገበሬ ይሁዳዊያን እንደተሸሸጉ ስለተናገር፤ መ. ፊሽማን ጀርመናዊያን ስለተቃወመ አንዱን የጀርመን ፖሊስ በጥይት ጎዳው። በቦካቾቫፃ ደን ወስጥ ከቡርሽቴን ከተማ እና በአካባቢው የሚገኙ የተወሰኑ ይሁዳዊያን ተደራጀጅተው(ፓርቲዛናዊያን) የቡርሽቴን ከተማ የፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት በማድርስ እና ጥይት በመቀማት ሲንቀሳቀሱ ነበር። በሶቪዬት ህብረት ጦር ከተማዋ ስትለቀቅ ከእንዚህ ሰዎች 13 ተርፈው ተገኙ። በመጨረሻ 1944 ዓ.ም እና በመጀመሪያ 1945 ዓ.ም ከሶቪዬት ህብርት ቤተሰቦቻቸውን ስላለግኙ እና በቦታ የሁዳዊያን በነፃ መኖር እንደማይችሉ ሲረዱ ተመልሰው ወደ ቡርሽቴይን ከተማ መጡ። በ 1950 ዓ.ም የይሁዳዊያን መካነ መቃብር ለህዝብ መናፈሻ ቦታ ሆነ።
