ከቀብር በኋል ስለ ሚካሄደው ማዕድ ምክር-
ሥኡዳት ሀብራዓ
ከቀብር በኋላ ለሀዘንተኞች የሚቀርበው ማዕድ በጎረቤቶች አማካኝነት እንደሚዘጋጅ የተለመደ ነው። ይህ ማዕድ ሥኡዳት ሀብራአ ሲባል፤ ሥኡዳት ሀብራ የሚባለው ማዕድ ከምስር፣ ከተቀቀለ እንቁላል የተሰራ መሆነ አለበት። ለዚህ ምግብ የሚቀርቡ ነገሮች ድንቡልቡል መሆን አለባቸው። ይህም ህይወት እና ሞትን ያመለክታል። ምክንያቱም በአለም ላይ ሁሌ ስለሚከሰቱ ነው። አንዱ ይሞታል ሌው ይወለዳል፣ አንዱ ይነሳል፤ ሌላው ይወድቃል። ስለዚህ ይህ የሀዘን ቀን አልፎ እንደገና የደስታ ቀን ይመጣል። ወዲያው እንደቀርቡ ይህ ማዕድ(ሥኡዳት ሀብራአ) ይቀርብላቸዋል። ይህ ማዕድ የሚቀርበው ከሀዘንተኞች መካከል አንድ ባለሆነ ሰው ነው።ወይንም ቤተ ዘመድ ባልሆነ ሰው መቅረብ አለበት።
