በቀብሩ ሥነ ሥር ዓት ላይ እንዴት መላበስ እንደሚያስፈልጋ ጠቃሚ ምክር፦

እንዴት መላበስ እንዳለብዎት፦ 

በዚህ አስቸጋሪ አጋጣሚ ጊዜ ምን መልበስ ያስፈልጋል የሚለው ጥያቄ ተገቢ ባይሆንም፤ በቀብር ሥነ ሥርዓት ጊዜ  የምንለብሰው ልብስ ትርጉሙ ምንድን ነው?  የሟቹ ቅርብ ዘመዶች (ወላጆች፣ ባል/ሚስት፣ ወንድ እና ሴት ልጆች፣ ወንድም እና እህት) የልብስ ቀደዳ ሥነ ሥርዓት መፈፀም የሚፈልጉ ከሆነ፤ በተለመደው ባህል መሰረት በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ይህን ሂደት ይፈፅማሉ። ስለዚህ ከገላቸው ባለው ልብስ ላይ በተደረገው የልብስ ቀደዳ ሥነ ሥርዓት ያን ልብ እንደለበሱ ለሰባት ቀን ከመሬት ወይንም ከትንሽ ወንበር በመቀመጥ ያሳልፋሉ። ከእነዚህ ቀናት በኋላ ደግሞ ልብሱ ይጣላል ወይንም አይለበስም።  ስለዚህ ይህን ሳምንት በሙሉ ተለብሶ ስለሚሰነብት  ለሀዘኑ ተስማሚ ልብስ ማስብ ያስፈልጋል። በምዕራብ አለም የሀዘን ምልክት ጥቁር ልብ መልበስ የተለመደ ሲሆን፤ በይሁዳዊያን ዘንድ ይህ ባህል አይደረግም።