ስለሀዘን ጥያቄዎች እና መልሶች
መልስ
ዝጋ
በሀዘን ምክንያቱ የልብስ ቀደዳ ሲካሄድ "ባሩህ ዳያ ሀኤሜት" በማለት ይባረካል። ይህ ቡራኬ የሚባረከው አንድ ሰው መርዶ ሲሰማ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚያደርገው እውነት እና ትክክል እንድሆነ ለመቀብል ሲባል ይባረካል። አንድ ሰው ዘመድ ሲሞትበት እስከ ሚቀብር ድረስ ማንኛውንም የሀይማኖት ትዕዛዝ መፈፀም የለበትም። ነገር ግን በዚህ ችግር ላይ እያለ ግዴታ ይህን ቡራኬ መባረክ አለበት። ሰልዚህ በቡራኬ ላይ አሸር ቅድሻኑ በማለት የማይባረከው የሞተው እስካልተቀበረ ድርሰ ዘመዶቹ ሀይማኖታዊ ትዕዛዝ መፈፅም ግዴታ ስለለባቸው ነው። ስለዚህ ማንኛውም የምስጋና ቡራኬ እና አሸር ቅድሻኑ በሚፅቮታ የሚለው የቡራኬ ክፍል የለለበትን ቡራኬ ግዴታ መባረክ ያስፈልጋል። ምክንያቱ አንድ ሰው አባቱ መሞቱን መርዶ ሲሰማ፤ "ባሩ ዳያን ሀኤሜት" የሚለውን ስለመርዶ ሲባርክ፤ ውርሱ ለእርሱ ብቻ የሚሆን ከሆነ ደግሞ ግዴታ "ሽሄያኑ" የሚለውን ቡራኬ መባረክ አለበት። ነገር ግን ሌላ ከእርሱ ጋር ሌሎች ወራሾች ካሉ ሀቶቭ ሀሜቲቭ በማለት ይባርካል።
ማንኛውንም የህግጋትን ጥያቄዎች በተመለከተ ለራብ ይስራኤል ሮዝንታል በሚቀጥለው ስልክ ቁጥር መደወል ይቻላል፦
ሥልክ ቁጥር- 0527965020
