ስለሀዘን ጥያቄዎች እና መልሶች

መልስ
አንድ ሰው ሊሞት እየተናዘዘ ከሆነ እና የመጨረሻው ጊዜ ከሆነ፤ ከአጠገቡ በመቆም አብሮ በአስተሰርዮ ፆም የሚደረገውን የይቅርታ ፀሎት ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ጊዜ እርሱን መንካት የተከለከለ ነው። ምክንያቱም ሰው በሚሞትበት ጊዜ ሌጠፋ እንደተቃረበ ሻማ ይቆጠራ። ስለዚህ በሚነካ ጊዜ ወይንም የሰውነቱን አካል በሚያንቀሳቅሱ ጊዜ የሰየውን ሞት ሊያፈጥን ስለሚችል መንካት የተከለከለ ነው። የይቅርታውን ፀሎት ከተባለ በኋላ የዳዊት መዝሙ መዕራፍ 121-ዓይኖቸን ወደ ተራራው አነሳሁ የሚለውን፤ ምዕራፍ 130 -አቤት አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ፤ 91- በልዑል መተጊያ የሚኖሩ የሚሉትን መዝሙሮች ይነበባሉ። ነብሱ ልትወጣ ስትል "እስራኤል ሆይ ስማ እግዚአብሄ አምላካችን እግዚአብሄር አንድ ነው" የሚለውን ፀሎት ማለት ያስፈልጋል። እንዲሁም " የመንግስቱ ግርማ ሥም ለዘላለም ብሩክ ይሁን" የሚለውን ፀሎት ሶስት ጊዜ፣ ሰባት ጊዜ እግሞ "እግዚአብሄር እርሱ አምላክ ነው" የሚለውን እና አንድ ጊዜ ፡እግዚአብሔር ንጉስ ነው፤ እግዚአብሔር ነገሰ፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሳል" ማለት ያስፈልጋል።
መልስ
ነብሱ ከወጣች በኋላ፤ አንድ ሰው መሞቱን የመወሰን ሀላፊነት ያለው ሰው ከወሰነ በኋላ የሟቹን የቤት መስኮቶች መክፈት ያስፈልጋል(ከሆስፒታል ከሞተ ደግሞ የሞተበን ክፍል መስኮት)። ከዚህ በኋላ በእቃ የነበሩትን ውሃ ሁሉ መድፋት ያስፈልጋል። ከዚህ በኋላ አስከሬኑን ከመሬት በማውረድ እና እግሩን ወደ በሩ በኩል በማድረግ እናስቀምጠዋለን። እንዲሁም እጁን ከሰውነቱ ጋር በማስጠጋት እጣቶችን በመክፈት እናቀናቸዋለን። ከዚህ በኋላ ዓይኑን መልሰን በአንሶላ እናለብሰዋለን። እነዚህ ተግባራት ካደረኝ በኋላ፤ ከእራሱ በላይ ሻማ እና የዳዊት መዝሙርን ነብሱ እንድትማር ይነበባል።

ማንኛውንም የህግጋትን ጥያቄዎች በተመለከተ ለራብ  ይስራኤል ሮዝንታል በሚቀጥለው ስልክ ቁጥር መደወል ይቻላል፦ ሥልክ ቁጥር-  0527965020