ዶርሀቪ
ማህደረ ትውስታቸው በሆፍ ሀካርሜል መካነ መቃብር ይገኛል።
ቦታ፦ ሮማኒያ
ከሆሎኮስት(ሽዋ) በፊት በ 1938 የነበሩ ይሁዳዊያ፦ 45, 000 ሰዎች

የሮማንያ ከተማ በሰሜናዊው የሞልዶያ ከተማ በቦኮቢና ደንበር ትገኛለች። በ 1930 ዓ.ም 5820 ይሁዳዊያን ነበሩባት። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ጊዜ በዚህ ከተማ ይኖሩ የነበሩ ይሁዳዊያን ከጥንቷ የሮማኒያ ይሁዳዊያ የበለጠ ተሰቃይተዋል። ይህ የሆነው ምክንያት ከሶቭየት ህብርት ጋር በነበራት ደንበር ምክንያት ነበር። በ 1940 ዓ.ም የሶቭየት ህብረተ ሰሜናዊ የቦኮቢና ክፍል በእርሷ ስር በማድረጓ ምክንያት ነው። በ 1940 ዓ.ም በሮማንያ የመጀመሪያው የይሁዳዊያ ጭፍጨፋ የተጀመረው በዚህ አመት ሲሆን፤ የሮማንያ ልዩ ጦር ከቡኮቢና ለቀው ሲወጡ በዶሮሀቪ የሚኖሩ ብዙ የይሁዳዊያን ወታደሮች እና ይሁዳዊያን ዜጋዎች የገደሉበት ጊዜ ነበር። ከእነዚህም እናቶች እና ልጆች አብረው ተገደሉ። ከ 200 ያለነሱ ይሁዳዊያን በዚህ እልቂት ተገደሉ። ይህ በዶሮሀቪ ከተማ በሮማንያ በመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ እልቂት ልዩ የሚያደርገው በሮማንያ የመጀመሪያ ሲሆን፤ እንዲሁም ይህ ይሆነው ሮማንያ እና የናዚማዊ ጀርመን መካከል ስምምነት ገና ስይፈፅሙ እና የጀርመን ጦር ወደ ሮማንያ ሳይገባ ነበር። ሮማንያ ከጀርመን ጋር በአንድ በመሆን የሶቭዬት ህብረትን ለመውረር በ 1941 ዓ.ም ሲደራጁ፤ በይሁዳውያን ላይ ብዙ ጥቃት አድርሰዎባቸዋል። በዶሮሀቪ አካባቢ በሚገኙ ከተሞች የሚኖሩ ይሁዳዊያን ተባረው ወደ ዶሮሀቪ ተፈናቀሉ። ለምሳሌ በሳቨኒ፣ ዳራባኒ፣ ሚሀይለኒ፣ ቫርዳውች 300 እና የዶ ይሁዳዊያ እና የህብረተሰቡ አስተዳዳሪዎች የነብሩ በምዕራ ሮማንያ ስር ተሰደዱ። አብዛኛዎች ወደ ጀው-ትርራጎ የሚባል ቦታ እንደኮሚንስቶ ስለተጠረጠሩ ተሰደዱ። የዶ ይሁዳዊያን በሙሉ ልዩ ምልክት እንዲያደርጉ ተገደዱ። በ 1941 ዓ.ም በነህሴ መጨረሻ ወር እና በመስክረም ወር መጀመሪያ 3000 ወንድ ይሁዳዊያ ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ዶ ተይዘው ከመጡ በኋል ፤ 300 ብቻ ተመልሰው ወደ ምዕራብ ሮማንያ ተወሰዱ። የዶ ይሁዳዊያ በሙሉ ገንዘባቸውን በጦርነቱ ጊዜ በብድር እንዲሰጡ ተገደዱ። በጥር 5 ቀን 1941 ዓ.ም የአገሪቱ ባለስልጣኖች በከተማው የሚኖሩትን ይሁዳዊያን ለምባረር አዋጅ አውጀው ለህብረተስቡ አስተዳዳሪዎች አስታወቁ። ስለዚህ ለዶ ወርዳ በቦኮቢና የሚኖሩ ይሁዳዊያን ወደ ትራንዚስተሪያ እንዲላኩ ተደረገ። የዚህ አላማም የወጣው ከቡክረሸት ሲሆን አላማውም በስሜን ሞልዶቫ የሚኖሩ ይሁዳዊያን ቁጥር ለመቀነስ ነበር። ስለዚህ ይሁዳውያን ንብረታቸውን ለሮማንያ ባንክ ልኦሚ ለመሸጥ ተገደዱ። እንዲሁም ጎረቤቶቻቸው ንብረታቸውን ያለፍቃድ ወሰዱባቸው። በጥቅም 7 ቀን 1941 ዓ.ም በዶሮሀቪን እና በቫርዳውች የሚኖሩ ይሁዳዊያን ተሰደዱ። እንዲሁም በበነገታው ጥቅምት 8 የ በሳቨኒ፣ ሚሀይለኒ፣ የሚኖሩ ይሁዳዊያን ሲባረሩ፤ በጥቅም 12 ቀን ደግሞ የዶ ይሁዳዊያን መፈናቀል ጀመሩ። ከእንዚህ ይሁዳዊያን ውስጥ 450 ይሁዳዊያ ጎቦ በመስጠት በዶ ከተማ ከመኖር ፍቃድ አገኙ። ነገር ግን ግማሾች በዶ ከተባረሩት 8000 ይሁዳዊያን ጋር ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመለያየት ስላልፈለጉ አብረው ተሰደዱ። አብዛኛዎች እነዚህ የተባረሩት ይሁዳዊያን በቡር ውስጥ ዲኔሴተርን ከመሻገራቸው በፊት ህይወታቸው አለፈ። አብዛዝኛው የተባረሩት ይሁዳዊያን እናቶች እና ልጆች ነበሩ። ወንዶች ግን በሮማንያ በተዘጋጀው የስራ ካምፕ ቀሩ። . ወደ ሌላ ቦታ ያልተባረሩትና በሮማንያ ይሁዳዊያን መካከል የተቋቋሙት የማኅበረሰቡ አስተዳዳሪዎች የዶ አውራጃ በድሮው ሮማንያ ዳግም ለመመስረት ከፍተኛ ጥረት አድርዋል ፡፡ ምክንያቱም የተባረሩት ይሁዳዊያን ወደ ቦታቸው መመልስ እንዲቻል ነበር። የሶቭዬት ጦር ሀይል ወደ ዶ በተቃረበ ጊዜ፤ የተሰደዱ ይሁዳዊያን ወደዚህ እንዲመለሱ ፍቃድ ተሰጠ። ስለዚህ በግል ሀይል የሚንቀሳቀስ የእርዳታ ኮሜቴ ለዑካን ቡድን ስደተኞችን ለማስመለስ ወደ ትራንስተሪስትሪያ በመሄድ ከ 10863 ይሁዳዊያን ውስጥ 6350 ይሁዳዊያን አስመለሱ። ከ 3470 ከዶ ወረዳ ከተባረሩት 2000 ተመለሱ። የአካባቢው ባለሥልጣናት ስደተኞቹን ቀይ ጦር ሠራዊት በሚያዝያ 1944 ከተማዋን ነፃ እስኪያወጣ ድረስ በማስፈራራት ያሳዷቸው ነበር።
