ያአሲ
ማህደረ ትውስታቸው በሆፍ ሀካርሜል መካነ መቃብር ይገኛል።
ቦታ፦ ሮማኒያ
ከሆሎኮስት(ሽዋ) በፊት በ 1938 የነበሩ ይሁዳዊያ፦ 45, 000 ሰዎች

የመጀመሪያው የመኖሪያ ቦታ
የታሪክ ተማራማሪ ያቆብ ፕስንቲር ቢአሺ ቦታ የይሁዳዊያን መቃብር ፈልጎ ካገኘ በኋላ፤ እነዚህ መቃብሮች በ 1467 ዓ.ም እና 1549 ዓ.ም እንደተሰሩ ይገመታል። ይህ ቢሆንም ከዚህ ዓመታት በፊት ይሁዳዊያን በከተማዋ እንደነበሩ ይታወቃል። የታሪክ ተማራማሪው ሀራብ ዶ/ር አብርሀም ሜኢር ቢአሽ ከተማ የሚገኙ መቃብሮ በ 1968 ዓ.ም እንደተሰሩ ይናገራል። ነገር ግን የጥንቱን የይሁዳዊያን መቃብር እንዳላገኘው ይገምታል። ያአሺ የሚኖሩ ይሁዳዊያን ስፋራዲሞች(የስፋራ ይሁዳዊያ ባህል) ተከታዮች እና የኦትመኒም ዜጎች እንደነበሩ ይታወቃል። ስልዚህ በ 16 ክፍለ ዘመን የአሮን ቮዳ ባለስልጣን የቱርኮችን (እንደ ሚሃኢ) ሲገድል፤ ከቱርኮች ጋር የነበራቸውን ይሁዳዊያንም አብሮ ገድሏቸዋል።
በ 15 ክፍለ ዘመን ሽቴፋን- የመልዶቫ አገር ገዥ በይሁዳዊያን ዶ/ሮች እንደተረዳ ሲገለፅ፤ አንዳንዶች ደግሞ ይህ አገር ገዥ በይሁዳዊያን እንደታገዝ ትክክለኛ ምንጭ እንደለለ የሚናገሩ አለ። ሌላው በያአሽ ከተማ ይፅሀቅ ቤን ቢናሚን ሾር የሚባል ሎጊፋት ይሁዲ እንደነበረው ይነገራ።
በያአሽ የሞልዶቫ ዋና የግዛት ዋና ከተማ ስትሆነ፤ በከተማ የሚኖሩ ይሁዳዊያ በሁሉም የበለፀጉበት ጊዜ ነበር። ሌላው በ 1648 ዓ.ም በይሁዳዊያን ላይ በታወጀው አዋጅ መሰረት እና በኩዝካኢም ጦሮች ምክንያት የተሰደዱ ይሁዳዊያን ተመልሰው በያአሽ እና በሞልዶቫ መጠጊያ ቦታ አገኙ። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሳይቆዩ የኩዝካኢም ጦር ወደ ሞልዶቫ በጋብቻ ምክንያት( የሞልዶቫን ገዥ- ሲሎ ሎፎ ሴት ልጁን ሮክሳናን ለ ቲሙሽ የኩዝካኢ ገዥ- ቦግዳን ሀምላኒችኪ እንዲያጋባ ለማስገደድ ሲባል) የኩዝካኢ ጦር ወደ ሞልዶቫ በመግባት፤ ብዙ ይሁዳዊያንን ገንዘባቸውን የት እንዳስቀመጡ እንዲነግሯቸው አሰቃይተዋቸዋል። ግማሾችን በገንዘብ በመቀብል ሲለቋቸው፤ ሌሎችን ግን ገድለዋቸዋል። ይህ ድርጊት ብዙ ጊዜ በድግም በይሁዳዊያን ላይ ተከስቷል። ለምሳሌ በ 1652 ዓ.ም በያአሽ ከተማ የሮክሳናን እና የቲሙሽን ሰርግ ሲያጀቡ ብዙ በይሁዳዊያን ላይ ጥቃት አድርሰዋል። በከተማ የነበሩትን ይሁዳዊያን ከጥፋት ያዳናቸው ያአሽዊው ማርኪዮስ ማንቲዮሂያ እርዳታ ነበር። ይህ ከባድ ጊዜ በያቫን ምፁላ የሚባለውን መጽሕፍ በፃፉት በራብ ናትን ናታአ ተገልጿል። ፕሮፌሶር ግኦርጋ ጊብንሸህ ባየው ሰንድ ያአሽ ከተማ የይሁዳዊያን ት/ቤቶች በያአሽ ከተማ ከ 1668-1666 ዓ.ም በኢሊያአሽ አለክሳንደር ግዛት እንደነበር ይገልፃል።
የመጀምሪያዎች ራባናት እና የጥበበኛ ተቋም_ሞሳድ ሀሀም ባሺ (1600-1800)
በ 1657 ዓ.ም የያሺ ከተማ ኖሪያዎች ይሁዳዊያን መሬት በመግዛት በያሺ የነበሩውን ትልቅ ፀሎት ቤት ሰርተዋል። የመጀመሪያ ፀሎት ቤት የተሰራው ከሮማኒያ አግሮች ከመጡ ደንጋዮች ሲሆን፤ ፀሎት ቤቱ የመረቀው በራብ ናታን ናታአ ሀኖቨር ነበር። መሬቱን ሲገዙ አብረው በሰነድ ላይ ከፈረሙ ሰዎች ሞይሳ የሚባለ ዶ/ር አማች አብሮ እንደፈረመ እና በ 19662 ዓ.ም ሞይሳ የተወሰኑ ቦታዎች በያሺ በአኩም ጉዳና እንደገዛ ተገልፃል።
የያሺ ከተማ በታሪክ ሰነዶች ላይ ተፅፎ የሚገኘው የመጀመሪያ ዋና ሊቅ(ራብ ራሺ)ሽሎሞ ቤን አራቪ ይባል ነበር። የመጣውም ከየመን አገር ሲሆን፤ ዋና መተዳደሪያው በህክምና እና በ 15 ክፍለ ዘመን መጨረሻ እና በ 16 ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የሚስጥር መፅሀፎችን(ስፍሬ ካባላ) እንደፃፈ ተገልጿል። በዚህ የታሪክ ሰንድ ይሁዳዊያ ነጋዴዎች ተፅፈው ሲገኙ፤ ከእነዚህ መካከል በከተማዋ የተቀመጡት ይሁዳዊያን፦ በህክምና እንደተሰማሩ ተገልጿል። ለብዙ ጊዜ በከተማዋ ራባናት እንዳገለገሉ ተገልፆ ይገኛል።
በ 1779 ዓ.ም የኦትማናዊያን ገዣ ሀሀም ባሺ ፣ በፃልኤል ኮየን እና ልጁን ናፍታሊን ኮየንን የሚባሉትን ሊቃናት የያሺ ከተማ ዋና የይሁዳዊያን የሀይማኖ መሪ እንዲሆኑ ሾሙት። ከዚህ በኋላ የሀይማኖት መሪነት ከልጅ ወደ አባት እየተላለፈ ከመጣ በኋላ፤ ከንፍታሊ ኮየን በኋላ ልልጁ ልራብ ይፅሀ ሲተላለፍ፤ በ 1777 ዓ.ም ሲሞት ሀራብ መርዶካይ ቤን ሞሼ ሃይም የሚባል ሊቅ በሞልዶቫ የሀይማኖት የመሪነቱን ገንዘብ ለንጉሱ-ኮንስታንቲን ዳፒንቴ በመስጠት ሀላፊነቱን ወሰደ። ከዓመት በኋላ በማስተማር ደረጃ በብቃት ሆኔታ ስላልገለገለ ተባረረ። በእርሱ ፈንታም ናፍታሊ ቤን ይፅሀቅ ተመረጠ። ሶስተኛ ጊሪጎራ የሚባለው ገዥ እንዲሁም በቅጥል ስም አሌክሳንደር ጂካ እየተባለ የሚጠራው የሀይማኖቱን መሪነት ስልጣን እንደፈቀደ እና የሀሀም ባሻ የግብር ክፍያውን እንዳሰፋው ይታወቃል። ከ 1790 ዓ.ም በኋላ የሀሀም ባሺ ስልጣን ወደ ኮየን ቤተሰብ በናፍታሊ አማካኝነት እንደተመለሰ እና በ 1793 ዓ.ም ልጁ ይፅሀቅ ከአገር ገዥው ፍቃድ እንደተቀበለ ተገልጿል። ከናፍታሊ ወደ ለጁ ይሻያው ስልጣኑ ተላለፈ። ነገር ግን በነበረበት የአስተዳደር ችግር ይህ የሀይማኖት አገልግሎት መስጫ ተቋም እንዲዘጋ አደርጓል።
የህብረተሰቡ እድገት(1800)
በ 18 ክፍለ ዘመን አጋማሽ የያሺ ይሁዳዊያ በአንድ አካባቢ በመቀመጥ እና በንግድ ላይ የነበሩ ስራዎችን በራሳቸው ቁጥጥር ላይ አድርገው ነበር። ከዚህም በኋላ እ 19 በክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የቱርኮችን እና የግሪኮችን በማስለቀቅ ቦታቸውን ያዙ። በ 1831 ዓ.ም ይሁዳዊያን ነርጋዴዎች እና ባለ እጅ ጥበቦች 43% የሚሆኑ ነጋዴዎች ነበሩ። ከዚህ በኋላ በ 1860 ዓ.ም 78% ደርሰው ነበር። በ 1755 ዓ.ም በያሺ ቤት ውስጥ የሚሰሩ(የሚተገበሩ ስራዎች) ወደ 1,353 ደርሰው ነበር። 65 የይሁዳዊያ፣ 30 ወደ ክርስትና ሀይምኖት የገቡ ይሁዳዊያን፣ 33% ይሁዳዊያ ከሌሎች ህይማኖት ትከታዮች ጋር የተጋቡት ናቸው። በ 1808 ዓ.ም በያሺ 547 አባውራዎች እንደነበሩ እና በነብስ ቁጥር 2, 404 እንደነበሩ ይታወቃል።
በ19 ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ የሞልዶቫ ባልስልጣኖች ይሁዳዊያን ላለመቀበል እና መተዳደሪያ የለላቸውን ይሁዳዊያ ለማስለቀ አዋጀ አወጁ። ስለዚህ በጥቅምት 14 ቀን 1843 ዓ.ም በጎዳና የሚዞሩትን ወይንም ቤት የለላቸውን ለማባረር ትዕዛዝ ወጣ። ነገር ግን ይህ ትዕዛዝ በጎዳና ተዳዳሪዎች ተመስሎ ቢወጣም ለይሁዳዊያ ነበር። ስለዚህ በያሺ የምክር ቤት ሀላፊ አማካኝነት የይሁዳዊያን ቤት እና ሱቅ በዋና የከተማዋ ጎዳናዎች እንዳይኖር ተከለከለ። ነገር ግን ለተወሰኑ ይሁዳዊያ በእነዚህ ጎዳናዎች ቤት የነበራቸው ሰኦውች ፍቃድ ተሰጣቸው ፡፡ ለክርሲቲያኖች ብቻ እንጅ፤ ለይሁዳዊያን መሸጥ እና ማከራየት እንዳይችሉ ከለከሏቸው። በከተማዋ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ሙስና ችግር ምክንያት ይህ ትዕዛዝ አልተፈፀም። ለሌላው በይሁዳዊያ ላይ የተከለከለው ነገር ቢኖር፤ ይሁዳዊያን ከ 30 ዓመት በታች የሆኑ የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮችን በአገልጋይነት እንዳያሰሩ ተከለከሉ።
በሁለተኛው የዓለም ጦርነት
በያሺ ከተማ ጎዳናዎች የይሁዳዊያን አስከሬኖች ወድቀው ይገኙ ነበር።
በሁለተኛ የአለም ጦርነት ጊዜ በይሁዳዊያን ላይ ነፍስ ማጥፋት ድርጊቶች በኢሮፓ ከተረጉት ድርጊቶች የበለጠ በያሺ ከተማ ይደረግ ነበር። ይህ ድርጊት የብዙ ይሁዳውያን ህይወት መጣፍ የኢሮፓን ይሁዳዊያ መጥፋት የጀመረበት ጊዜ ነው።
ሰኔ 29 ቀን 1941 ዓ.ም ዮን አንቶንኮ የተባለው የሮማንያ አገረ ገዥ በከተማዋ የሚገኙትን ይሁዳዊያን እንዲባረሩ አዘዘ። በዚህ ቀን የሮማንያ ጦር ሀይል እና የፖሊስ አባል እንዲሁም በይሁዳዊያን(ፀረ- ሴማዊ) የሆኑት ይከተማዋ ኖዋሪዎች ከ 13,266 ይሁዳዊያንን ሲገደሉ፤ የሮማንያዊ ባደረጉት ምዘገባ መሰረት፤ እንዲሁም ሁሉም የይሁዳዊያን ተቋም ሁሉ ተከፍተው ሀብታቸው እና ንብረታቸው ተወሰደ። በአገሪቱ የሚኖሩ ይሁዳዊያ ባደረጕት የምዝገባ አይነት ወደ 14,850 የሚደርሱ ይሁዳዊያን ተገድለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በህብረተሰቡ ባህር መዝገብ ያልነበሩ ይሁዳዊያን እንደተገደሉ ይታወቃል። ስለዚህ የተገደሉት ይሁዳዊያን ቁጥር አይታወቅም። ነገር ግን በግምት ወደ 20, 000 የሚጠጉ ይሁዳዊያን ተገድለዋል። እንዲሁም የተደበደቡ እና ጥቃት ና የተዋረዱ ይሁዳውያን ነበሩ።
ከዚህ ስቃይ እና መከራ በፊት፤ በያሺ ከተማ 45,000 ያላነሱ ይሁዳዊያን እንደነብሩ ይገመታሉ። በሚያዚያ ወር በተደረገው የህዝብ ቆጠራ መሰረት በያሺ ከተማ 34, 753 ይሁዳዊያን እንደነበሩ ይታወቃል። ይህ ቁጥርም ከተማዋን እና የገጠር ቦታዎችን ያለገንዘብ እና ንብረት እንዲለቁ፤ በባለ ስልጣኖች ትዕዛዝ መሰርት የተገደዱትን ይሁዳዊያን ሁሉ ያጠቃልላል። ከዚህ ችግር በኋላ በ 1941 ዓ.ም የይሁዳዊያን ዘርኛት የነበራቸው ወደ 32, 364 ይሁዳዊያን ተቆጥረዋል።
