ኮሎ
ማህደረ ትውስታቸው በሆፍ ሀካርሜል መካነ መቃብር ይገኛል።
ቦታ፦ ሎስጅ እና ሀጋሊል፣ ፖላንድ
ከሆሎኮስት(ሽዋ) በፊት በ 1938 የነበረው የህብረተሰቡ ብዛት፦ 10, 300 ይሁዳዊያን

የህብረተሰቡ የታሪክ አጀማመር
የኮሎ ከቬርታ ወንዝ መተላለፊያ ላይ የተመሰረተችው በ13 ክፍለ ዘመን ሲሆን፤ የከተማ ስልጣን የተሰጠችው በ 1362 ዓ.ም ነበር። አስተማማኝ ምንጮች እንደሚያሳዩ፤ ይሁዳዊያን በዝች ከተማ መቀመጥ የጀመሩት በ 16 ክፍለ ዘመን እንደሆነ ያሳያሉ። በ 1564 ዓ.ም የኮሎ ንጉስ ለይሁዳዊያ የመቀመጥ መብት እንዳላቸው የሰጠበት ዓመት ነበር። በ1571 ዓ.ም መብታቸው በፅሁፍ ተገልጿል። የክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች መሰረት ፤ አመታዊ የከተማ ግብር መስጠት ነበረባቸው። የዚህ ክፍያ አላማም ይሁዳዊያን ከጥቃት ለማዳን ነበር። በ 1764/65 ዓ.ም በተደረገው የህዝብ ቆጠራ 65 የይሁዳዊያ አባላውራዎች በኮሎ ከተማ እንደተገኑ ተገልጿል።
በኮሎ ከተማ ይኖሩ የነበሩ ይሁዳዊያን ዋና የገቢ ምንጮች የእጅ ስራ እና ንግድ ነበር። ነገር ግን በ 19ኛው ክፍለ ዘመን አብዛኛዎች በፋብሪካ ተሰማርተው ይሰሩ ነበር። በዋናነት የሚጠቀሰው የፋብሪካ ስራ የቴክስትል ፋብሪካ ነበር። ይሁዳዊያን በሶስት ባንኮች እና በሁለት የኩባት ግማህች ታገዙ ነበር። እንዲሁም በከተማው ለልገሳ የሚንቀሳቀሱ ስዎች እና ለተቸገሩ የምግብ አቅርቦት የሚያደርጉ ነበሩ። በኮሎ ከተማ የሚኖሩ ይሁዳዊያ በሁለት የኢብራዊያን ትምህርት ቤቶች ሲማሩ ነበር። አንደኛ ያብኔ ሲባል ሁለተኛው ደግሞ የኢብራዊያ መዋለ ህፃናት ነበር። በትምህርት እና በባህል መስክ የፅዮናዊ ፓርቲዎች ሲያንቀሳቅሱ ነበር።
በ 19ኛው ክፍለ ዘመን የኮሎ ራባናት(ሊቃውንቶች) መካከል ራቢ ሜኢር ኦየርባህ (1813-1887) የበለጠ ታዋቂ ነበር። የኮሎ ከተማ ራብ(ሊቅ) ቆኖ የተመረተው በ 1846 ዓ.ም ነበር። ከዚህ በኋላ በ 1859 ወደ የሩሳሌም መጦ፤ የአሽከናዚም ህብረተሰብ ዋና ሊቅ ሆኖ አገልግሏል።
በመጀመሪያው እና በሁለተኛው የአለም ጦርነት በኮሎ ከተማ ከ 6000 ያላነሱ ይሁዳዊያን ይኖሩ ነበር። ይህ ብዛት የከተማዋን የህዝብ ብዛት ግማሽ ማለት ነው። ከአለም ጦርነት በፊት በመቶ የሚቆጠሩ ይሁዳዊያ የኮሎን ከተማ ለቀው የተወሰኑት ወደ የሩሳሌም መጡ።
የኮሎ ከተማ ይሁዳዊያን በሆሎኮስት ጊዜ
ጀርመናዊያን መስከረም 18 ቀን 1939 ዓ. ም የኮሎን ከተማ በቁጥጥር ስር ካዋሏት በኋላ፤ በበነገታው ብዙ ይሁዳዊያ መግደል እና የግዴታ ስራ ለማሰራት ይሁዳዊያንን በመልመል ጀመሩ። መስከረም 20 ቀን 1939 ዓ.ም የፀሎት ቤት ከአቃጠሉ በኋላ የግንዘብ ክፍያ በይሁዳዊያን ላይ ወሰኑ። እንዲሁም በ 1939 ዓ.ም ከ 14 ዓመት በላይ ይሆኑ ይሁዳዊያን ወንዶች የግዴታ ስራ በጀረመናዊ ፋብሪካዎች እንዲሰሩ ተገደዱ። ይህ እንደዚህ እያለ፤ ይሁዳዊያ በመጀመሪያ ላይ ቢጫው ጨርቅ በግራ ክዳቸው እንዲያደርግጉ ከታዘዙ በኋላም፤ የማጌን ዳቪድ ያለበት ቢጫ ኮከብ ከደረታቸው ላይ እንዲያደርጉ ታዘዙ። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ከክርስቲያኖች ጋር እንዳይገኛኙ እና በሱቅ እንዳይገዙ ተከለከሉ። የአብዛኛው ይሁዳዊያን ንብረት ታግዶባቸው ነበር።
ጥር 1939 ዓ.ም በከተማው የተወሰኑ ይሁዳዊያ ሲገደሉ፤ ከተገደሉ መካከል የተማሩት እና ሀብታሞች ነበሩ። ከዚህ በኋል ዮንድራንት ከ 11 ሰዎች አባል ያሉበት ተቋቁሞ ሀላፊ ፒንሀስ ብረነር ነበር።
በታህሳስ 10 ቀን 1939 ዓ.ም 1,139 ይሁዳዊያን ታፍነው ለሳምንት ተይዘው ከቆዩ በኋላ ወደ ሉበልስካ እና ወደ ኢዝባያፃ ከተባረሩ በኋላ ሀብት ንብረታቸው ለጀርመናዊያን ተሰጠ። ወደ እነዚህ ቦታዎች የተሰደዱ ይሁዳዊያን አብዛኛዎች በራብ ምክንያት ህይወታቸውምን አጡ።
ጥቅምት ሁለት ቀን 1940 ዓ.ም በከተማዋ የሚኖሩ ከ 150 ያላነሱ የይሁዳዊያን ቤተሰቦች፤ በገጠር አካባቢ ከተሰሩት ለይሁዳዊያ መሰብሰቢያ ወደተዘጋጀው ካምፕ ተሰደዱ። ካምፖች የተሰሩበት ቦታዎች፦ ቦጋኢ፣ ኖቢኒ እና ብርዶብስኪያ ነበሩ። ከእነዚህ ሰዎች መካከል የተወሰኑት 1941 የግዴታ ስራ እንዲሰሩ ወደ ኢንብሮፅላብ ሲላኩ፤ የቀሩት ደግም በ 1942 ዓ.ም ሀላምኖ የጋዝ መግደያ ቦታ ተሰደው ህይወታቸው ተሰዋ።
በ 1940 ዓ.ም በኮሎ ከተማ የይሁዳዊያ መሰብሰቢያ ቦታ ተሰርቶ መውጣት እና መግባት ስለተከለከለ ብዙ ይሁዳዊያን በበሽታ ምክንያት ህይወታቸውን አጠዋል። ሰኔ 19-21 1941 ዓ.ም 500 ወንዶች ከካምፑ በግዴታ ስራ እንዲሰማሩ ወደ ፖዝናን አካባቢ ተወሰዱ። በነሀሴ 1941 ዓ.ም 100 እናቶች ከካምቱ በግዴታ ስራ እንዲሰማሩ ወደ ብረስሎው ወደ ሚባል ቦታ ተወሰዱ።
ከታህሳስ 8-11 ቀን 1941 ዓ.ም የጀረመን የፖሊስ ሀይል በግርያነና ሽትራክ አማካኝነት የኮሎን ይሁዳዊያን በአንድ በመሰብሰብ ወደ ሀላምኖ ወደ ሚባል በጋዝ መግደያው ማሽን ቦታ ላኳቸው። ከጦርነቱ በኋላ በህይወት የተረፉ በአስር የሚቆጠሩ ይሁዳዊያ ወደ ኮሎ ከተማ ተመልሰው መጠው ከቆዩ በኋል፤ በዘረኝነት ምክንያት ወዲያው ከተማዋን ለቀው ወደ ትላልቅ ከተሞች በፖሊን መኖር ጀመሩ።
