የሄብራ ካዲሻ አገልግሎቶች፡

ቤተሰቦች መገንዘብ ያለባቸው ነገር

የሄብራት ካዲሻ (መካነ መቃብሩ)  አገልግሎት የሚሰጠው ያለምንም ክፍያ ነው።  ኩባንያው የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፦ ቀብሩ የሚከናወንበትን ቀን መወሰ፣ አስከሬኑን ከሞተበት ቦታ ወደ ሚቀበርበት መካነ መቃብር ማስተላለፍ፣ አስከሬኑን ለቀብር ማዘጋጀት፣ ወደ መቃብሩ ማምጣት፣ የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት ማዘጋጀት(መፈፀም) ናቸው።

የመካነ መቃብር የምዝገባ  ስራ አስኪያጅ እንደሚከፍል እስካልተናገር ድረስ፤  ማንኛውም ሰው የኩባንያው ሰራተኛ ነኝ ብሎ ቢቀርብ እና ክፍያ ቢጠይቅ ሀብረተሰቡ መክፈል የለበትም። ስለዚህ ህብረተሰቡ  ላለመክፈል መጠንቀ አለብት። 65

ለቢቱዋህ ልኦሚ ድህረ ገፅ ከዚህ ይጫኑ፡

ሰው በህይወት እያለ ቦታ ለመገዛት ከፈለገ የሚሸጡ ቦታዎች፡

ማንኝውም ሰው በህይወት እያለ ወደ መካነ መቃብሩመስሪያ ቤት  በመምጣት የቀብር ቦታ ለእርሱ ሆነ ለቤተሰቡ  በፈለገው መንገድ መግዛት ይችላል።  ከፈልገ  የሳዴ የቃብ ሥነ-ሥርዓት፣ የማክፔላ የቃብር ሥነ-ሥርዓት፣  የሳንሄድሪን የቀብር ሥነ-ሥርዓት (ኩሂት)፤ ይህ የሚሆነው ክፍት ቦታ ካለ ነው።

የቃብር ቦታ ለመግዛት ዋጋውን በሄብራት ካዲሻ ድህረ-ገጽ ወይንም ከኩባንያው የፅሀፊ ሰራተኞች የበለጠ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።

 

አስከሬን የማስተላለፍ አገልግሎት፡

የሄብራት ካዲሻ ኩባንያ አንድ ሰው ሲሞት ከሆስፒታል፤ ከአረጋዊያ መጦሪያ ቤት እና ከግል ቤት ሲሞት ወደ መካነ መቃብሩ በኩባንያው መኪና ያለ ገንዘብ ይሥተላልፋል።

አስክሬን ለማስተላለፍ በስራ ሥዓት በ -04-8688000   በመደወል በሥዓቱ እንዲተላለፍ ተራ ማሳዝ ይቻላል። ከስራ ሥዓት በኋል ከሆነ ደግሞ ወደ ጥሪ መዕከል በ *0120 መደወል ይቻላል።

በበጋ የስራ ጊዜያት፡ - ከእሁድ እስከ ሀሙስ  ከ 8፡00-18፡00

አርብ እና በበዓል ዋዜማ  8፡00-14፡00

በክረምት የስራ ጊዜያት፦ ከእሁድ እስከ ሀሙስ  ከ 8፡00-16፡00

አርብ እና በበዓል ዋዜማ  8፡00-13፡00

 

አስከሬን ማስቀመጫ ፍርጀር አገልግሎቶች

የአንድ ሰው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ሲዘገይ ወይንም በበነገታው እንዲቀበር ከተወሰነ፤  የሄብራት ካዲሻ ኩባንያ ያለምንም ክፍያ አስከሬኑን የአስከሬን ማስቀመጫ ፍሪጀር ውስጥ ያስቀምጣል። ነገር ግን ከ 48 ሥዓታት በኋላ ቢቱዋህ ልኦሚ በወሰነው ተመን መሰረት ኩባንያው አስከሬኑ ከላይ ከተጠቀሰው ሥዓት በላይ ለማቆየት ክፍያ ይጠይቃል። 

 

በነፃ የሚሰጡ የቃብር ሥነ-ሥር ዓት አገልግሎቶች፡

አገልግሎቱ የሚያጠቃልላቸው ፦ አስከሬኑን  ለቃብሩ ማዘጋጀት፣  የወንድ አስከሬኖችን ወንዶች ያፀዱታል፤ እንዲሁንም የሴቶችን አስክሬን ሴቶች ያፀዳሉ፡፡ ከጥጥ የተሰራ የአስከሬን ክፋን፣ ቃብሩን መቆፈር እና የቃብሩን ሥነ-ሥር ዓት ማከናወን ናቸው።

ቀብሩ በሚካሄድበት ጊዜ የሚደርገ የፀሎት አገልግሎት፡

በማንኛውም የቀብር ሥነ-ሥርዓት ከኩባንያው  ውስጥ የሚሰራ እና ደሞዝ የሚከፈለው   የፀሎት መሪ አለ። እርሱም  የቀብሩን ሥነ-ሥርዓት የሚመራ እና ለሞተው ሰው ካዲሽ የሚደረገውን ፀሎት  ያደርጋል።

መቃብሩ በእንክብካቤ ለመያዝ  የሚሰጡ አገልግሎት፡ 

የሟቹ ቤተሰቦች መቃብሩን በጥንቃቄ ለመያዝ  ሲፈልጉ፤ መቃብሩን  ለማፅዳት  እና  ከመቃብሩ አጠገ የተተከሉትን አትክልቶች እና አበባዎችን   በሥርዓት ለመጠበቅ  የሚፈልጉ ከሆነ፤  ለዚህ አገልግሎት ክፍያ በመክፈል  መቃብሩ በጥሩ ሆኔታ መያዝ  ይቻላል።