ስለሀዘን ጥያቄዎች እና መልሶች
መልስ
ዝጋ
ሰንበት የሀዘን ቀኑን አያቋርጠውም። ምክንያቱም ትንሽ የሀዘን ምልክት (ዲኔ አቭሉት በፂናአ ኖአጊም በሻባት) በሰንበት ስለሚቆጠር እው፡፡ ይህ ቢሆንም በአደባባይ ወይንም በግልፅ የሀዘን ምልክቶች አይደረጉም።
መልስ ዝጋ
አንድ ሰው ዘመዱ ሞቶ በዓሉ ከመግባቱ በፊት ከተቀበረ ፤ በዓሉ እስከሚገባ ድረስ የሀዘን (ለተወሰነ ሥዓት ቢሆንም) ምልክት ያደርጋል። ስለዚህ በዓሉ ሰባቱን የሀዘን ቀናት ያቋርጠዋል(ይሰርዘዋል)። ይህ የሚያደርጉ በዓላት ደግሞ፦ ፋሲካ፣ ሻቡኦት፣ የዳስ በዓል፣ በርሀነ ሰረቀ እና አስተሰርዮ ናቸው።
መልስ ዝጋ
የበዓላት ቀናት ለሰላሳው የሀዘን ቀናት ይቆጥዕራሉ። ስለዚህ ሰላሳ የሚቆጠረው ከተቀበረበት ቀን አንስቶ ስለሆነ፤ በዓሉ አያቋርጠውም።.
መልስ ዝጋ
ሰላሳኛው ቀን በሰንበት ቀን ከዋለ፤ አርብ ወይንም እሁድ ወደ መቃብሩ መሄድ ይቻላል። እንዲሁም ይህ ቀን በሻቡኦት፣ በዳስ በዓል እና በፋሲካ በዓል የመጨረሻው ቀን ከዋለ በበነገታው(በኢሱር ሀግ) ወደ መቃብሩ ይሄዳል። ነገር ግን ይህ ቀን በፋሲካ ወይንም በዳስ በዓል በመጀመሪያው ቀን ከዋለ፤ ወደ መቃብሩ የሚሄደው በበዓሉ ዋዜ መሆን አለበት። ከዚህ በተጨማሪ በብርሀነ ሰረቀ ወይንም በአስተሰርዮ ከሆነ፤ በዓሉ በዋለ በበነገታው ወደ መቃብሩ ይኬዳል። ነገር ግን "እግዚአብሄር በምህረት የተሞላ ነው" እና የነብስ ይማር ፀሎት አይደረግም።
ማንኛውንም የህግጋትን ጥያቄዎች በተመለከተ ለራብ ይስራኤል ሮዝንታል በሚቀጥለው ስልክ ቁጥር መደወል ይቻላል፦
ሥልክ ቁጥር- 0527965020
