ስለሀዘን ጥያቄዎች እና መልሶች
መልስ
ዝጋ
ከቀብሩ በኋላ የሟቹ ቤተ ዘመዶች ወደ ሟቹ ቤት ይሄዳሉ። ከዚያም እንደደረሱ ሰባቱን የሀዘን ቀናት መቁጠር ይጀመራሉ። ስለዚህ ከዚህ ጀመሮ በሰባቱ የሀዘን ቀና የሚደረጉትን ህግጋት መፈፀም ግዴታ አለባቸው።
መልስ ዝጋ
ሀዘንተኞች በሚቀመጡበት ቤት መስታወቶችን እና ከግድግዳው የተሰቀሉት ፎቶዎችን እና ቴሌቪዚያኦች ይሸፈናሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው በእግዚአብሄር ምስል ስለተፈጠረ እና አዳም ሀጢያት ከስራ በኋላ "ከአፈር ነው እና የተሰራህ ወደ አፈር ትመለሳለህ" ተብሎ ስለተረገመ፤ አዳም በስራው ኃጢአት በፈጣሪው ምስል የተፈጠረ ሰው እንደገና ወደ አፈር ስለሚለወጥ ነው። ስለዚህ በሀዘንተኞች ቤት ውስጥ መልክን የሚይሳዩ ነገሮችን መሸፈን ያስፈልጋል። ሌላው ምክንያት ደግሞ ሀዘንተኞች በመስታወት መልካቸውን ቢመለከቱ ፤ በሀዘን ላይ እያሉ ለመኳኳል የቆሙ ወይንም የቀረቡ መስለው እንዳይታዩ ነው።
መልስ ዝጋ
ከቀብር በኋላ ለሀዘንተኞች የሚቀርበው ማዕድ በጎረቤቶች አማካኝነት እንደሚዘጋጅ የተለመደ ነው። ወዲያው እንደቀርቡ ይህ ማዕድ(ሥኡዳት ሀብራአ) ይቀርብላቸዋል። ይህ ማዕድ የሚቀርበው ከሀዘንተኞች መካከል አንድ ባለሆነ ሰው ነው።ወይንም ቤተ ዘመድ ባልሆነ ሰው መቅረብ አለበት። ስለዚህ ሀዘንተኞች ይህን ማዕድ ማዘገጃት ሆነ ማቅረብ የተከለከለ ነው። የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት የተካሄደው አርብ ከሆነ ወይንም በበዓልም ሽት ከሆነ ይህን ማዕድ አይፈፀምም። ሥኡዳት ሀብራ የሚባለው ማዕድ ከምስር፣ ከተቀቀለ እንቁላል የተሰራ መሆነ አለበት። ለዚህ ምግብ የሚቀርቡ ነገሮች ድንቡቡል መሆን አለባቸው። ይህም ህይወት እና ሞትን ያመለክታል። ምክንያቱም በአለም ላይ ሁሌ ስለሚከሰቱ ነው። አንዱ ይሞታል ሌላው ይወለዳል፣ አንዱ ይነሳል፤ ሌላው ይወድቃል። ስለዚህ ይህ የሀዘን ቀን አልፎ እንደገና የደስታ ቀን ይመጣል።
ማንኛውንም የህግጋትን ጥያቄዎች በተመለከተ ለራብ ይስራኤል ሮዝንታል በሚቀጥለው ስልክ ቁጥር መደወል ይቻላል፦
ሥልክ ቁጥር- 0527965020
