ፒያአስክ ሉብልን
ማህደረ ትውስታቸው በሆፍ ሀካርሜል መካነ መቃብር ይገኛል።
ቦታ፦ ፖላንድ
ከሆሎኮስት(ሽዋ) በፊት በ 1938 የነበሩ ይሁዳዊያ፦ 42, 130 ሰዎች

ይሁዳዊያን ወደ ሉብሊን የመጡት በ 1316 ዓ.ም ለንግድ ስራ እንደሆነ ይገመታል። ከሀያ ዓመት በኋላ ፓአቲ በምትባለው ከተማ ለመኖር ፍቃድ ቢሰጣቸው፤ ይሁዳዊያን በሉብሊን በተደራጀ መንገድ ለመኖር የተፈቀደላቸው ከሁለት መቶ ዓመት በኋላ ነው። ከዚህ በኋላ በ 16 ክፍለ ዘመን አጋማሽ ትልቅ ፀሎት ቤት እና የይሁዳዊያን ቋሚ ሱቆች ተከፈቱ። በ 16 ክፍለ ዘመን በስልሳዎች አመታት በዚህ ቦታ ኦሪት መመሪያ ቦታዎች በመከፈት፦ ኦሪትን፤ ታልሙድ እና ካቫላ ትምህርት የተሰጠብት ኢዜ፤ እንዲሁም በፖላንድ ውስጥ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት የሃይማኖት ማዕከላት አንዱ ሆነ ፡፡ ረቢ ሻሎም ጎረቤት ፣ በሊብሊን ውስጥ የየሺቫ ሃላፊ እና በ 16 ኛው ክፍለ ዘመን ከታላላቅ ሊቃውንት መካከል አንዱ የሆነው በፖላንድ ንጉሥ “የይሁዳዊያን ጉዳዮች ንጉስ” ልዩ ማዕረግ ተሰጥቶት ነበር፡፡ ይህም “ለመደበኛ ገለልተኛ ያልሆኑትን” ጨምሮ ለሁሉም በፖላንድ ከተሞች ያለምንም ችግር ከቦታ ቦታ እንዲያልፍ ተፈቀደለት።
ይህ ቢሆንም በ 17 እና 18 ክፍለ ዘመን የሉብሊን ይሁዳዊያን በጣም( አስቸጋሪ ክስተቶች) አከፊ ችግር ደርሶባቸዋል። በ 1648-49 ዓ.ም የኩዝካዊያን አመፅ ጊዜ በይሁዳዊያን ላይ የጀምላ ጭፍጭፍ ተደርጎባቸዋል። እንዲሁም ብዙዎች ተገደሉ። ከሰባት ዓመት በኋላ በሲዊድን እና በፖላንድ በተደረገው ጦርነት የሉብሊን ከተማ ለከባድ ጥቃት ወድቃ ነበር። የከተማዋ ትልቁ ክፍል የሚባለው እና የሉብሊን ትልቁ ፀሎት ቤት በእሳት ተቃጠለ። ከዚህ በኋላ በፖላንድ የነበሩ የካቶሊክ ሀይማኖት መሪዎች ይሁዳዊያን ለማጥፋት ብዙ ጦርነት በማድረግ እና በ 1795 ዓ.ም ይሁዳዊያን ከሉብሊን ከከተማዋ እንዲባረሩ እና ወደ ከተማ ዳሮች እንዲተላለፉ ተደረገ።
በ 19 ክፍለ ዘመን በሉብሊን ከተማ የነበሩ ይሁዳዊያን 9,000 ይሁዳዊያን ነበሩ። ይህ ቢሆንም በይሁዳዊያን ላይ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ማቀቦች ግን አልተሰረዙም። ነገር ግን ይሁዳዊያን በኢኮኖሚ ደርጀ በጣም በከተማዋ ከፍተኛ ቦታ ከተወሰነ ዓመት በኋላ ያዙ። እንደምሳሌ የሚጠቀሰው የሲጋሪያ ማምረቻ ትልቅ ፍብሪካ የአንድ ይሁዲ ነበር። እንዲሁም 95% የልብስ ስራዎች በይሁዳዊያ ስር ነበሩ። ይህም ብዙ ይሁዳዊያን ስራ የማዋሉ ሚና መጫውት ተችሏል። ስለዚህ የሶሻሊስትነት “ባንድ” እንቅስቃሴ ለመገድፍ አስተዋፅኦ ነበረው። እስከ 19 ክፍለ ዘመን መጨረሻ በሉብሊን ከተማ የይሁዳዊያ ት/ቤቶች ፡ አክራሪዎች፣ ለዘብተኞች በአንድ እና የይሁዳዊያን ሆስፒታል ፤ እንዲሁም ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች- ጽዮናዊ ፣ ሃይማኖታዊ እና ሶሻሊስት ተቋቁመው ሲሰሩ ነበር።
በመጀመሪያው የአለም ጦርነት ጊዜ በሉብሊን 35,000 ይሁዳዊያን ሲኖሩ እንደነበረ እና በከተማዋ ከሚኖረው ህዝብ አንድ ሶስተኛ እንደሆኑ ይታወቃል። ሶሻሊስት የኢጉድ ሀፖአሊም የሚለው ድርጅት በሉብሊን ከተማ ሲያቋቁሙ፤ ጺዮናዊና የፖለቲካ ፓርቲ ደግሞ ወጣቶችን ወደ እስራኤል አገር እንዲመጡ ይገፋፏቸው ነበር። አክራሪ ሀይማኖተኞች ደግም በሉብሊን "የሺባት ሀህሜ ሉብሊን" የሚባለውን የኦሪት መማሪያ ቦታ አቋቋሙ። ይህ ቦታ በራብ ሜኢር ሻፒራ አማካኝነት በ 1925 ዓ.ም ሲቋቋም፤ በኢሮፓ ከነበሩት የኦሪት መማሪያ ቦታዎች አንደኛ እና በጣም ከፍተኛ ደረጃ የነበረው የኦሪት መማሪያ ቦታ ነበር። በ 1940 ዓ.ም የጀረመናዊያን ጦር ሀይል በዚህ ቦታ የነበሩትን የኦሪት መማሪያ መፅሀፎች ሁሉ አወደሟቸው።
ጀርመናዊያን በመስከረም 18 ቀን 1939 ዓ.ም ወደ የሉብሊን ከተማው ከተቆጣጠሯት በኋላ፤ በከተማዋ ጀርመናዊያን ሁለት የይሁዳዊያን ካፖች ሰሩ። በእነዚህ ካምፖችም 35,000 ይሁዳዊያን አስቀመጧቸው። በ 1941 ይሁዳዊያን ከካምፑ እንዳይወጡ ከተከለከሉ በኋላ፤ በከተማው የሚገኙትን ይሁዳዊያን ማጥፋት ተጀመረ። ከመጋቢት ወር 1942 ጀምሮ ወደ በልዝፅ የይሁዳዊያን ህይወት ማጥፊያ ካምፕ 30,000 ይሁዳዊያን ተላኩ። በከተማዋ የቀሩት ይሁዳዊያን በፋብሪካ ሲሰሩ ከቆዩ በኋል በ 1943 ዓ.ም ወደ ምይዳንክ የይሁዳዊያን ህይወት ማጥፊያ ካምፕ ተላኩ።
የቀይ ጦር(ፃቫ አዶም) በሀምሌ 24 ቀን 1944 ዓ.ም በፖላንድ ነፃ ካወጣቸው ከተሞች ሉብሊን የመጀመሪያዋ ከተማ ነበርች። ከጦርነቱ መጨርሻ እስከ 1950 ዓ.ም ወደ ሉብሊን ተመልሰው የመጡት ይሁዳዊያን ወደ 4,000 ቢደርሱም፤ በፀረ- ሴማዊያን ፍርሀት ፖላንድን ለቀው ወደ ሌላ አገር ተሰደዱ። ዛሬ በከተማዋ የሚገኙ ይሁዳዊያ በአስር የሚቆጠሩ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ እድሜቸው ከ 55 ዓመት በላይ ይሆናል።
