ለቀብሩ ምን መውሰድ እንደሚያስፈልገው የሚጠቅም ምክር፦

 

ለቀብሩ ምን መውሰድ ያስፈልጋል፦ 

የቀብሩ ሥነ ሥርዓት እና ወደ መካነ መቃብሩ መሄድ ብዙ ጊዜ  ሊወስድ ይችላል። ስለዚህ ወጣት ሆነ አዛውንቶች በዚህ ሥነ ሥርዓት መገኘት መንፈሳዊ ወይንም አካላዊ ድክመት ሊያመጣ ስለሚችል ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል። በመሆኑም በክረምት - ሞቃታ ልብሶችን እና ጃንጥላዎችን ለብዙ ጊዜ በሥነ ሥርዓቱ ወይንም በልቅሶው ላይ ስልምትቆሙ ይህን መውሰድ ያስፈልጋል። እንዲሁም በበጋ ወቅት  እራስዎን የሚሸፍኑበት ነገር(ቆብ) እና ዉሃ መውሰድ ያስፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ ሽማግሌዎች እና የታመሙ ሰዎች የሚመጡ ከሆነ፤ ታጣፊ ወንበሮችን መውሰድ እንዲጠቀሙ  ማድረግ ያስፈልጋል።  እንዲሁም የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ሲካሄድ ልቅሶ ስለሚበዛ የእንባ ማበሻ ወረቀት ወይንም የፀሀይ መነጠር ቢያመጡ ይመረጣል።  በድሮ ባህላዊ የቀብር ሥነ ሥርዓቶች በአብዛኛዎቹ ቦታዎች የአንድን ሰው ጭንቅላት መሸፈን የተለመደ ነው ፡፡  ስለዚህ ለወንዶች ኪፓ፤ ለሴቶች መሀረም(ቆብ) መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሟቹ ወንድ ከሆነ ድሮ ሲለብስ የነበረውን ጣሊት በማምጣት አስከሬኑ እንዲለብስ ማድረግ የተለመደ ነው።  ሌላ በሰባቱ የሀዘን ቀናት ከቆዳ በተሰሩ ጫማዎች ለመሄድ የማትፈልጉ  ከሆነ፤ የጎማ ጫማ ወደ መካነ መቃብሩ  ይዛችሁ በመምጣት፤ ከቀብሩ በኋል ወዲያው መቀየር ያስፈልጋል።