ቤቱን ለሰባቱ የሀዘን ቀናት ለማዘጋጀት ተቃሚ ምክር፦
ቤቱን ለሰባቱ የሀዘን ቀናት ማዘጋጀት፦
ከቀብሩ በኋላ ሀዘንተኞች የሚሄዱት ሰባቱን የሀዘን ቀናት ከሚያሳልፉበት ቤት መሆን አለበት። ስለዚህ ከየትኛው ቤት መሆን እንዳለባቸው ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል። በአብዛኛው ጊዜ የሚደረገው በሟቹ ቤት ይሆናል። እንዲሁም ለማስተዛዘን እና ፀሎት ለማካሄድ ለሚመጡት ሰዎች እና ለሀዘንተኞች ተስማሚ እና ሰፊ ቦታ ያስፈልጋል። አንዳንድ ቦታ ደግሞ የሀዘንተኞች ድንኳን ለሰባት ቀን የሚሰራበት ቦታ አለ። በዚህ አጋጣሚ የነብስ ይማር ሻማ፤ ወንበሮችን፤ የፀሎት መጽሐፍትን፤ ለወንዶች ኪፓ እና ኦሪት ወጦ በሚነበብበት ቀን ማምጣት ያስፈልጋል። በሀዘንተኛው ቤት መስታውቶችን መሸፈን የተለመደ ስለሆነ፤ ከተቻለ ከቀብሩ በፊት መሸፈን አለበዚያም ደግሞ ከቀብሩ በኋላ መሸፈን ያስፈልጋል። ከቀብሩ በኋላ ሰዎች ለማስተዛዘን ስለሚመጡ ቤቱን ቀድሞ ማዘጋጀት ያስፈልጋል።
