የጥንት መካነ መቃብር

ሥለ
በሄይፋ ከተማ የይሁዳዊያ የቀብር ሥነ ሥርዓት ጥንታዊ የይሁዳዊያን ሰፈር የተጀመረው በሚሽና እና በታልሙ ጊዜ እንደሆነ ተጠቅሷል። በቦታው ከተቀበሩ ሰዎች ታዋቂው አሞራ ረቢ አቭዲሚ ሲሆን፤ ከመቃብሩ ቀጥሎ አድራሻ የሌለባቸው ሌሎች መቃብሮች አሉ፡፡ ምንጮች እንደሚጠቁሙት የረቢ አቪዲሚ እና የረቢ ይፅሀቅ ናፍሃ መቃብሮች ጥግ ለጥግ እንድሆነ ተገልጿል ፡፡ ዛሬ ረቢ የአብዲሚ መቃብር በመካነ መቃብሩ ደቡባዊ ድንበር ላይ ቀብሩ እንደተገኘ ይነገራል። ነገር ግን ተመራማሪዎች እንደሚገልፁት የዚህ ሊቅ መቃብር በመከነ መቃብሩ መካከል እንድሆነ፤ የሀይፋ የመኪና መስመር ሲሰራ የመካነ መቃብሩ ከፊል አካል እንደፈረሰ ይገልፃሉ። ነገር ግን ተመራማሪዎች የሚስቡት የእርሱ መቃብር ያፎ-ሄይፋ መንገድ ሲሰራ ጊዜ የመካነ መቃብሩ ከፊል እንደፈረሰ ይገልፃሉ፡፡ አንዳንዶች የራቢ አቪዲሚ እና ሌሎች የጥንት ሰዎች መቃብር በጥንታዊ Haifa ሌላ ቦታ እንደነበሩ ያምናሉ። እንዲሁም ሌሎች የዚህ ሊቃ መቃብር እና የሌሎች ሊቃውንቶች መቃብር በሌላ ቦታ እንድሆነ ይገልፃሉ።
ለብዙ አመታት ወደ እስራኤል አገር የመጡ የተለያዩ ሰዎች በዚህ መካነ መቃብር እንደተቀብሩ እና መቃብራቸውም ከፃድቃን መቃብር አጠገብ እንደተቀበሩ ይታወቃል። ነገር ግን አውልቶች ብዙ ዓመታትን በመቆየታቸው መቃብሩ የማን እንደሆነ መለየት አይቻልም። እንዲሁም በአኮ ሲኖሩ የነበሩ ይሁዳዊያን በዚህ መካነ መቃብር እንደተቀብሩ ተገልጿል። ለምሳሌ በመካከለኛው ዘመን ወደ እስራኤል አገር የመጡ ራቢ ሽምሾን ምሻንፅ እና ራቢ ዮሴፍ የራቢ ይሄኤል ሜፋሪስ ልጅ እንደምሳሌ ይጠቀሳሉ።
የዚህ መካነ መቃብር አዲሱ ክፍል ዋና አገልግሎት የነበር ከ 1860-1935 ዓ.ም ሲሆን፤ ከተማዋን ያቋቋሙት የተለያዩ ሰዎች እና የከተማዋ ኖዋሪዎች ተቀብረውበታል። እንዲሁም አዲስ ሰፈራ ሲመሰረቱ የነበሩ ሰዎች የመቃብር ቦታ ስላልነበራችቸው በዚህ መካነ መቃብሩ ሲገለገሉ ነበር። በመካነ መቃብሩ ውስጥ ከተቀበሩ ሰዎች የካልፎን ቤተሰብ፣ የላስኮቭ፣ የሮትንበርግ፣ የፓቭዝነር ቤተሰቦች( ሽሙኤል ዮሴፍ ፓቭዝነር እና ሚስቱ የኤሀድ አም ልጅ) እንድተቀበሩ ተገልጿል። እንዲሁም ገዳሊያው እና ቤተሰቦቹ፣ በእስራኤል አገር የመጀመሪያው የቀዶ ህክምና ሀኪም ድ/ር አልበርት(አብርሀም) ወንደርሊህ፤ እንዲሁም በ1948 ክስተቶች የተገደሉት፤ በ 1934-1945 ክስተቶች የተገደሉት እና በበአትሊት የማህፀቤት ሶላል አደጋ ህይወታቸው ያጡ ሁሉ በዚህ መካነ መቃብር ተቀብረው ይገኛሉ። ከመቃብሮች መካከል በኦቶማን ግዛት ውስጥ ከይሁዳዊያን ዳያስፖራ የመጡ ሊቃውንቶች የመቃብር ድንጋይ እና በእስራኤል ምድር አጥንታቸውን እንዲቀብሩ ሳይሞቱ ለቤተሰቦቻቸው ትዕዛዝ የሰጡ ሰዎች የመቃብር ድንጋዮች ይገኙበታል ፡፡
ተጨማሪ በዚህ መካነ መቃብር ተቀብረው የሚገኙ ሰዎች፦ ሀራብ ሀቢብ ሀይም ዳቪድ ስታሆን የትቬሪያ ዋና የሀይማኖት ዳኛ፤ ሀራብ ዳቪድ ካልፎን፣ ሀራብ ርፋኤል ካልፎን፣ ሀራብ ዮሴፍ ኒሲም ኤልካቬ፣ ሀራብ ዮሴፍ አልተር፣ የሀይፋ ዋና የሀይማኖት ዳኛ ሀራብ አብርሀም ሀኮየን፣ የምዕራብ የሩሳሌም ሀኪም ሀራብ ብኒያሚን ሀሙይ፤ የካኢር ከተማ ራብ ሀራብ አሀሮን መንደል ብሀረን፣ የአድሞር ለቪ ይፅሀቅ ጎተርማን ልጅ ሀራብ ሽሙኤል እስራኤል፣ ሀራብ ይፅሀቅ ንኡራይ፣ የኢንዱስትሪ ባለሙያው ሊኦን ሽቴይን ፣ ዶ/ር ዮሴፍ ኮየን ፣ እንዲሁም በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በብሪታንያ ንጉሠ ነገሥት ግዛት ጊዜ በእስራኤል አገር አካባቢ በተደረገው ጦርነት ህይወታቸውን ካጡ በዚህ መካነ መቃብሩ ተቀብረው ይገኛሉ።
በጥንት ጊዜ ይህ የመቃብር ስፍራ እንደ ቅዱስ ስፍራ እና ወደ እስራኤል አገር ለሚመጡ ሰዎች የጸሎት ቦታ ሆኖ ሲያገለግል ነበር ፡፡ ለምሳሌ ራቢ ይፅሀቅ ባር ዮሴፍ ሄይሎ በ 1333 ዓ.ም ከስፔን ወደ እስራኤል እንደመጣ እንዲህ ይገልፃል፦ የሀይፋ ከተማ የካርሜል ተራራ ፊት ለፊት የተመሰረተች ስትሆን፤ ከተማዋም የረቢ አብዲሚ ደማን ሄይፋ ትውልድ ቦታ ነች። በከተማዋ ታዋቂ የሀሲዲም ህብረተሰብ እንዳለ እና በመካነ መቃብሩ ወደ እስራኤል አገር የሚመጡ ይሁዳዊያ በሙሉ እየሄዱ የፀሎት ሥነ ሥርዓት ያደርጋሉ። ምክንያቱም በመካነ መቃብሩ ከተለያዩ አገር የመጡ እና በአኮ ሲኖሩ የነበሩ የይሁዳዊያ ሊቃውንቶች ስለተቀበሩበት ነው።
ቦታ
የያፎ ጎዳና በታችኛው ሄይፋ(ታህቲት ሄይፋ)
የስራ ሀላፊዎች
ይህ መካነ መቃብር በሀይማኖት አገልግሎቶች ሚኒስቴር ሀላፊነት ስር ነው ያለ።.
የቦታው ስፋት
ከ 7.5 ዱናም ሲሆን፤ 850 ሰዎች በጥንቱ የሀይፋ መካነ መቃብር ተቀብረዋል። ይህ መካነ መቃብር በቢቱዋህ ል ኦሚ አማካይነይ ት መዘጋቱን ታውጇል።
የቀብር ዓይነት
የሳዴ ቀብር
የህዝብ ትራንስፖርት
የኤጌድ አውቶቡሶች፦ 3፣ 112፣ 200፣ 205
የሥራ ሥዓት
ይህ መካነ መቃብር ቀን እና ሌት ለ 24 ሥ ዓት ክፍት ነው።