ስለሀዘን ጥያቄዎች እና መልሶች
መልስ
ዝጋ
በሀዘን ምክንያቱ የልብስ ቀደዳ ሲካሄ "ባሩህ ዳያ ሀኤሜት" በማለት ይባረካል። ይህ ቡራኬ የሚባረከው አንድ ሰው መርዶ ሲሰማ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚያደርገው እውነት እና ትክክል እንድሆነ ለመቀብል ሲባል ይባረካል። አንድ ሰው ዘመድ ሲሞትበት እስከ ሚቀብር ድረስ ማንኛውንም የሀይማኖት ትዕዛዝ መፈፀም የለበትም። ነገር ግን በዚህ ችግር ላይ እያለ ግዴታ ይህን ቡራኬ መባረክ አለበት። ሰልዚህ በቡራኬ ላይ አሸር ቅድሻኑ በማለት የማይባረከው የሞተው እስካልተቀበረ ድርሰ ዘመዶቹ ሀይማኖታዊ ትዕዛዝ መፈፅም የለባቸውም። ስለዚህ ማንኛውም የምስጋና ቡራኬ እና አሸር ቅድሻኑ በሚፅቮታ የሚለው የቡራኬ ክፍል የለለበትን ቡራኬ ግዴታ መባረክ ያስፈልጋል። ምክንያቱ አንድ ሰው አባቱ መሞቱን መርዶ ሲሰማ፤ "ባሩ ዳያን ሀኤሜት" የሚለውን ስለመርዶ ሲባርክ፤ ውርሱ ለእርሱ ብቻ የሚሆን ከሆነ ደግሞ ግዴታ "ሽሄያኑ" የሚለውን ቡራኬ መባረክ አለበት። ነገር ግን ሌላ ከእርሱ ጋር ሌሎች ወራሾች ካሉ ሀቶቭ ሀሜቲቭ በማለት ይባርካል።
አንድ ካህን ለሞተ ሰው መርከስ የለበትም። ማለትም እስከ ሁለት ሜትር መቅረብ የለበትም። ወንም አስከሬኑ ካለበት ቤት መቅረብ የለበትም። ነገ ግን የሞተው ሰው ከሰባቱ ቤተ ዘመዶቹ ከሆነ ለእነዚህ ሰዎች መርከስ ትዕዛዝ አለበት። ሰባቱ የካህን ቤተዘመድ፦ አባት፣ እናት፣ ወንድ/ሴት ልጁ፣ ወንድሙ፣ እህቱ እና ሚስቱ ናቸው። ይህም ቢሆን አንድ ካህን መርከስ የሚችለው የሞተው ሰው እስከነሙሉ አካላቱ ሲሆን ብቻ ነው። ነገር ግን አንድ አካል ከጎደለው፤ መርከስ አይችልም። እንዲሁም የሟቹን የሰውነት አካል ከአጠገቡ ቢያስቀምጡት እና ወይንም ቢሰፉት፤ በተጨማሪም አንድ በሟቹ አስከሬን ላይ ኦፕሬሽን ቢደረግ ካህን የሆኑ ቤተዘመዶቹ መርከስ አይችሉም። ይህ ቢሆንም የዘመዱን አስከሬን እስከ ቀብሩ ድረስ መሸነት ይችላል። ይህ ሚሆነው ግን በመንገድ እስከ ሁለት ሜትር ርቀት መቃብር ከለለ ነው።
ይህ ሸሚዝ ወይንም ልብስ ከተቀደደበት ቀን አስንቶ እስከ ሰባተኝው ቀን ድረስ ሀዘንተኞች ለብሰውት ይቆያሉ። የተቀደደው ትልቅ ከሆነ በመርፌ ቁልፍ ማሳዝ ይቻላል። ነገር ግን ሰባቱ እስከሚያልፍ ድረስ መስፋት የተከለከል ነው። በእነዚህ ቀናትም የሀዘን ምልክት ሆኖ መታየት አለበት። ከሰባቱ የሀዘን ቀናት በኋላ ሰፍተው የሚለብሱ ሰዎች አሉ። ነገር ግን የእናት እና የአባት ሀዘን ከሆነ መስፋት ወይንም የተቀደደውን ማስተካከል አይቻልም። አንዳንዶች ደግሞ ይጥሉታል።
ዘመዱ መሞቱን የሰማ ሰው እና ሟቹ በሚገኝበት ከተማ እርሱ የማይገኝ ከሆነ፤ አስከሬኑ ከመቀበሩ በፊት ያሉትን ህግጋት መፈፀም እንዳለበት ወይንም እንደለለበት፤ የሀዘን ቀናት መቼ እንደሚጀምር የኦሪት ሊቃውንት መጠይቅ ያስፈልገዋል።
ማንኛውንም የህግጋትን ጥያቄዎች በተመለከተ ለራብ ይስራኤል ሮዝንታል በሚቀጥለው ስልክ ቁጥር መደወል ይቻላል፦
ሥልክ ቁጥር- 0527965020