በሽዋ የሞቱ ይሁዳዊያ መታሰቢያ በሄይፋ መካነ መቃብር የሚገኙ ኪህሎት(ህብረተሰቦች)

በሽዋ (ሆሎኮስት)ስለሞቱት ህብረተሰቦች
ህዝበ እስራኤል ከሁለት ሺ ዓመት በላይ በስደት ከተሰደደበት ቀን ጀምሮ፤ ህዝቡ ተከፋፍሎ በአለምት ከቦታ ቦታ ያለ ውድ በግድ የተዘዋወሩ ይኖር ነበር። በአንዳንድ ቦታ የተወሰነው ህብረተሰብ ለስደት ሲዳረግ፤ በሌላ ቦታ ደግሞ ህብረተሰቡ የግል ህይወቱን በሥነ- ሥርዓት ለሁለት ሺ ዓመት አቋቁመ ሲኖር ነበር። በእነዚህ ህብርተሰቦች)ኪሂሎ( በእምነታቸው ጠንተው እና ህይወታቸውን የሚመሩ በተቀደሰው ኦሪት መሰረት ነበር። በዚህም መሰረት አድገው፤ ተምረው፤ ተድረው እና ወልደው ልጆቻቸውን አሳድገው፣ እንዲሁም ድረው ኩለው ቤታቸውን መስርተው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን ይሁዳዊያን ለማጥፋት የታቀደው እቅድ)ሽዋ( መጦ ህብረተሰቡን ለዘር እንኳ ሳይቀር ሁሉንም አጠፋው።
ከእነዚህ ህብረተሰቦች በህይወት የተረፉት፤ ለእነርሱ ማህደረ ትውስታ በሆፍ ሀካርሜ መካነ መቃብር አውልት አሰርተዋል። በዚህ ቦታም በሽዋ ካንፕ ውስጥ የተቃጠሉት ሰዎች አጥን፤ አፈር እና አመድ ከጀርመን ተመጦ ከዚህ ቦታ ይገኛሉ።