በቀብሩ ሥነ-ሥርዓት በሚፈፀምበት ቀን ምን ይጠብቀናል?


በዚህ  ገጽ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በሀይፋ የሄብራት ካዲሻ ድርጀት መሰረት፤ በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከመከናወኑ በፊት  እና በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ላይ  በድርጅቱ መለያ ያደረጉ የድርጅቱ ሰራተኞች    ማብራሪያ ፣ ድጋፍ እና ጥያቄዎች ለአገልግሎትዎ ይሰጣሉ ፡፡

  ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በፊት ስለ ምዝገባው ሂደት እና ቴክኒካዊ ዝግጅቶችን ለማወቅ ከፈለጉ  ከዚህ ይጫኑ።

ወደ መካነ መቃብሩ መድረስ፦

የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ከታቀደበት ጊዜ  አስር ደቂቃ በፊት ወደ  መካነ መቃብር  በር/ አስከሬኑ ወደ ቀብር ቦታ ከሚወጣበት አዳራሽ መምጣት ያስፈልጋል።

ወደ ብታው እንደደረሳችሁ፤ የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ዋና ሀላፊ ሰራተኛ ወይንም የፀሎት መሪ ያገኛችኋል። የድርጅቱን ሰራተኞች ለመለየት በሸሚዛዝቸው  ላይ በተሰፋው  ልዩ ምልክት መለየት  ትችላላችሁ።

ከቀብሩ ሥነ ሥርዓት በፊት፦

በመካነ መቃብሩ አስከሬኑ እና ቤተዘመዱ ለተወሰነ ጊዜ የሚቆዩበት እና የሚለያዩበት ክፍል አለ። ስለዚህ በዚህ ክፍል ብቻችሁን ለመሆን ብትፈልጉ የሄብራት ካዲሻ ሰራተኞችን እንዲወጡ መጠየቅ ትችላላችሁ።  የሟቹን ፊት የሚገለፀው  ሟቹን ለመለየት በመጣው ዘመዱ  ፊት ብቻ ነው። ይህም የሚሆነው ወደ ቀብር የመጣው ሰው አስከሬን ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።  ከዚህ በኋላ የሟቹን አስከሬን ለመለየት የመጣው ሰው የፈርማል።

የፀሎት መሪው የሟቹ  የሞቱ ቤተሰቦች  ለፀሎት እና የህይወት ታሪኩን የሚያነቡትን ስዎች ማንነት ይጠይቃችኋል፡፡   

የቀብሩ ሥነ-ሥር ዓት

የሟቹ አስከሬን በድርጅቱ ሰራተኞች አማካኝነት ወደ መለቀሻ አዳራሹ ይወጣል።

የሟቹ የህይወት ታሪክ ከመነበቡ በፊት፤ የሟቹ ቤተሰቦች (ወላጆች፣ ባል/ሚስት፣ ወንድ እና ሴት ልጆች፣ ወንድም እና እህት)  አስከሬኑ ወደ ተቀመጠብት ቦታ በመቅረብ የልብስ ቀደዳ ሥነ ሥርዓት ይፈፅማሉ።

ይህን ሥነ ስርዓት የሚፈፅመውም የሄብራት ካዲሻ ሰራተኛ ሲሆን፤ ለወንዶች ወንድ ለሴቶች ደግሞ ሴት ትፈፅማለች።  ከተቻለ ደግሞ አንድ ቤተዘመድ ይህ መፈፀም ይችላል። ሀዘንተኞች የሞተባቸው እናት ወንም አባት ከሆነ- ልብሳቸውን የሚቀዱት በግራ በኩል(ልብ በሚገኝበት በኩል)ከደረታቸው በላይ  ያለውን ሲሆን፤ ለሌሎች ዘመዶች በቀኝ በኩል ይደረጋል።  ልብሱን ቢያንስ 8.5 ሴንቲ ሜትር ያህል መቅደድ ያስፈልጋል። የሄብራት ካዲሻ ሰራተኛ ትንሽ ከቀደደው በኋላ ሀዘንተኛው ከላይ ወደታች   8.5 ሰንቲ  ሜትር እስከ ከሚደርስ ይቀደዋል። ከዚህ በኋላ እንዲህ በማለት ይባርካል፦ ባሩህ አታ አዶናይ ኤሎሄኑ ሜሌህ  ቮላም  ዳያን ሀኤሜት( ብሩክ አንተ እግዚአብሄር አምላካችን  የአለም ንጉስ እውነተኛ ፍርድን የምትሰጥ።

ከዚህ የልብስ ቀደዳ ሥነ ሥርዓት በኋላ ቤተሰቦቹ በመጀመሪያ በተወሰነው ተራ መሰረት  የሟቹን የህይወት ታሪኩ ከተነበበ በኋላ አስከሬኑ ወደ ቀብሩ ቦታ ይወሰዳል።

ቀብር

አስከሬኑ  ወደ መቃብሩ ቦታ ሲደርስ ወንዶች ወይም ካዲሽ የሚሉት ሰዎች ከፀሎት መሪው አጠገብ መሆን አለባቸው።  የቀብሩ ሥነ ሥር ዓት እና አፈር  የመመለስ ሂደቱ የሚካሄደው የፀሎት መሪው የመዝሙር ዳዊት ምዕራፎ እያነበብ ነው።

በቀብሩ መጨርሻ  የካዲሽ ፀሎት በሟቹ ቤተሰቦች  ማካኝነት ይደረጋል። እንዲሁም የፀሎት መሪው ደግሞ "እግዚአብሔር በምህረት የተሞላ ነው" የሚለውን ፀሎት ያደርጋል።

ከቀብሩ በኋላ  ትንሽ ደንጋይ ከመቃብሩ ላይ ማስቀመጥ የተለመደ ነው።

ስለሀዘን እና የቀብር ሥነ ሥርዓት ህግጋት በሰፊ መረጃ ከፈለጉ - ከዚህ ይጫኑ።