ህግግታ እና ናህላዊ የሀዘን ልምዶች፡

ከሞሞቱ በፊት

አንድ ሰው ሊሞት እየተናዘዘ ከሆነ እና የመጨረሻው ጊዜ ከሆነ፤ ከአጠገቡ በመቆም አብሮ በአስተሰርዮ ፆም የሚደረገውን የይቅርታ ፀሎት ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ጊዜ እርሱን መንካት የተከለከለ ነው። ምክንያቱም ሰው በሚሞትበት ጊዜ ሊጠፋ እንደተቃረበ ሻማ ይቆጠራል። ስለዚህ በሚነካ ጎዜ ወይንም የሰውነቱን አካል በሚያንቀሳቅሱ ጊዜ የሰየውን ሞት ሊያፈጥን ስለሚችል መንካት የተከለከለ ነው። ነብስ ልትወጣ ስትል "እስራኤል ሆይ ስማ እግዚአብሄር አምላካችን እግዚአብሄር አንድ ነው" የሚለውን ፀሎት ማለት ያስፈልጋል። እንዲሁም " የመንግስቱ ግርማ ሥም ለዘላለም ብሩክ ይሁን" የሚለውን ፀሎት ሶስት ጊዜ፤ ሰባት ጊዜ "እግዚአብሄር   እርሱ አምላክ ነው" የሚለውን እና አንድ ጊዜ እግዚአብሔር ንጉስ ነው፤ እግዚአብሔር ነገሰ፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሳል" ማለት ያስፈልጋል።  ነብሱ ከወጣች በኋላ እና አንድ ሰው መሞቱን የመወሰን ሀላፊነት ያለው ሰው ከወሰነ በኋላ፤ የሟቹን የቤት መስኮቶች  መክፈት ያስፈልጋል፡፡ ከሆስፒታል ከሞተ ደግሞ የሞተበን ክፍል መስኮት። ከዚህ በኋላ በእቃ የነበሩትን ውሃ ሁሉ  መድፋት ያስፈልጋል።  የሚከተሉትን ተግባራት መፈፀም የሚቻለው  ሰዬው መሞቱን ከተወሰነ ከሃይ ደቂቃ በኋል ይሆናል።

አንድ ሰው ሲሞት ምን መደረግ እንዳለበት መርሆዎችን ለመመልከት ከዚህ ይጫኑ

በአዘቦት ቀን

አንድ ሰው በአዘቦት ቀን ሲሞት የሚደረግ ሥነ-ሥር ዓት፦  አስከሬኑን ከመሬት በማውረድ እና እግሩን ወደ በሩ በኩል በማድረግ እናስቀምጠዋለን።  እንዲሁም እጁን ከሰውነቱ ጋር በማስጠጋት እና እጣቶችን በመክፈት እናቀናቸዋለን። ከዚህ በኋላ ዓይኑን መልሰን  በአንሶላ እናለብሰዋለን።  የሞተው ሰው ወንድ ከሆነ  የጣሊቱን ዘርፍ ከቋጠርን በኋላ አስከሬኑን ማልበስ ያስፈልጋል።  የሟቹን አስከሬን ከመሬት ስናወርደው ሙሉ ስሙን በመጥራት ግዴታ ይቅርታ መጠየቅ አለበን፡፡ (ማንኛውም ያደረግነው ነገር ሁሉ ለክብርህ ሲባል ነው። ስለዚህ እኛ ከአንተ (የሰውየው ስም እስከ አባቱ) ይቅርታህን እንጠይቃለን። ከዚህ በኋላ ከእራሱ በላይ ሻማ ይበራለታል። የሻማው ብዛት እያንዳንዱ እንደህብረተሰቡ ባህል ይለያያል። ነገር ግን ሻምው ሲበራ ሙቀት እና አደጋ የሚፈጥር ከሆነ፤ ማብራት አያስፈልጋም። ማቹን ብቻውን ማስቀረት አይቻልም። ቢያንስ አንድ ሰው ከሞተ ሥዓት አንስቶ እስከ ሚቀበር ድረስ  አብሮት መቆየት አለበት። የዳዊት መዝሙርን  ነብሱ እንድትማር ይፀለያል።

በሰንበት እና በባዓላት

አንድ ሰው በአዘቦት ቀን ሲሞት የሚደረግ ሥነ-ሥር ዓት፦  አስከሬኑን ከመሬት በማውረድ እና እግሩን ወደ በሩ በኩል በማድረግ እናስቀምጠዋለን።  እንዲሁም እጁን ከሰውነቱ ጋር በማስጠጋት እና እጣቶችን በመክፈት እናቀናቸዋለን። ከዚህ በኋላ ዓይኑን መልሰን  በአንሶላ እናለብሰዋለን።  የሞተው ሰው ወንድ ከሆነ  የጣሊቱን ዘርፍ ከቋጠርን በኋላ አስከሬኑን ማልበስ ያስፈልጋል።  የሟቹን አስከሬን ከመሬት ስናወርደው ሙሉ ስሙን በመጥራት ግዴታ ይቅርታ መጠየቅ አለበን፡፡ (ማንኛውም ያደረግነው ነገር ሁሉ ለክብርህ ሲባል ነው። ስለዚህ እኛ ከአንተ (የሰውየው ስም እስከ አባቱ) ይቅርታህን እንጠይቃለን።  አስከሬኑ ሌላ ሽታ እንዳይኖረው እና ሟቹ እንዳይዋረድ በርዶ ከላዪ ላይ ማስቀመጥ ይቻላል። እንዲሁም ለዚህ ዓላማ አየር ማቀዝቀዣ እንዲሠራ ለአንድ ይሁዲ ላልሆነ ሰው የአየር ማቀዝቀዣውን  እንዲያበራው መንገር ይቻላል።  ነገር ግን የተፈቀደ እቃ ከአስከሬኑ በማድረግ ከመሪተ ለማስቀምጥ እንጅ ወደ ሊለአ ቤት አይቻልም።  ካስፈለገ ታዋቂ ራብ ጋር መወያየት እና መፍትሄ ማግኘት ይቻላል። ወደ ሌላ ቤት ማስተላለፍ ካስፈለገ ደግሞ፤ ይሁዲ ባልሆነ ሰው መፈፀም አለበት።

ነብሱ በምትወጣበት ጊዜ(በሚሞት ሥ ዓት)

ሀዘንተኞች ሰባት ቀን በሚቀመጡበት ቤት የነብስ ይማር ሻምዎች ይበራሉ።  ሻማዎችም የሚበሩት ወዲያው ነብሱ እንደወጣ ነው።  እንዲሁም ቀብሩ በሚካሄድ ሥዓት ከደረታችን በላይ ባለው ልብስ ትንሽ ይቀደዳል። ይህን ልብሱም ሀዘንተኛው ከሰንበት ውጭ እስከ ሰባት ቀን ሳያወርደው ይለብሰዋል።  ሰውየው ከሞተበት ጊዜ ጀመሮ እስከሚቀበር ድረስ አኔኑት  የሚባል ህግጋት በሀዘንተኞች ላይ ይውላል። ይህ ማለትም በኦሪት አድርግ ተብሎ የታዘዙትን ትዕዛዛት ከመፈፀም ነፃ ሆናል። ወዲያው ሰውየው እንደሞተ ወደ ሄብራት ካዲሻ ድርጅት በመደወል  የቀብሩ ሥነ-ሥርዓት ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ለበለጠ የመርሆ ማብራሪያ ከዚህ ይጫኑ

በሚሞትበት ሥ ዓት እና በቀብር መካከል

አኔኑት

አኔኑት የሚባለው ህግጋት አንድ ሰው ከሞተ ሥዓት አንስቶ እስከ ሚቀበር ድረስ  በሀዘንተኞች ላይ የሚውል ትዕዛዝ ነው።  ስለዚህ የሟቹ ሰባት ቤተ ዘመድ ሰባት ቀን በሀዘን መቀመጥ አለባቸው።   አንድ ሰው የሚገኘው በሌላ ከተማ ወይንም በሩቅ አገር ከሆነ እና ዘመዱ ሞሞቱን መርዶ ሲደርሰው ለቀብር የመምጣት ፍላጎት ከለለው፤  ወዲያው የሀዘንተኛ ህግጋት  በረሱ ላይ ይውላሉ። ሰለዚህ በዚህ ጊዜ መደረግ ያለባቸውን ነገሮች ማድረግ ይገባዋል። በአንዳንድ ይሁዳዊያን ማህበረሰብ ዘንድ አስከሬኑን አያሳድሩትም። ወዲያው እንደሞተ በምሽትም ቢሆን  በሞተበት ቀን  ይቀበራል። ለምሳሌ የሩሳሌም ከተማ። ነገር ግን ለሟቹ ክብር ሲባል፤ ዘመዶቹ ከሩቅ  ለቀብሩ እንዲደርሱ ለአንድ ቀን ማቆየት ይቻላል።

አኔኑት በአዘቦት ቀን

 አንድ ሰው በአኔኑት በሚለው ህግጋት ውስጥ ካለ ማንኛውንም ት ዛዝ መፈፀም አይችልም። ለምሳሌ ትፍሊን ማሰር፣ ፀሎት መፀለይ፣ ሽማ እስራኤል የሚለውን ፀሎት እና ቡራኬዎችን መባረክ አይችልም።  ምክንያቱም የቃብሩን ሥነ- ሥርዓት ያለምንም ችግር እና በነፃ እንዲያከናውን  ተብሎ ነው።  ለምሳሌ አንድ ሰው ዘመዱ ሞቶ እስካለተቀበረ ድረስ ምንም ትዕዛዝ አይፈፅምም። ለምሳሌ እጁን ይታጠባል። ነገር ግን ቡራኬውን አይባርክም። ምግብ ሲበላም በመጀመሪያ እና በመጨረሻ አይባርክም። ሽንት ቤት ከተፀዳዳ በኋላም አሸር ያፃር ቡርኬ አይባርክም። እንዲሁም ፀሎት ወይንም ቡራኬ ሲባረክ አሜን አይልም። በቃብሩ ሥነ- ሥርዓት ጊዜ  ካዲሽ የሚል ፀሎት አለ እርሱን ያደርርጋል። በዚህ ጊዜ ወይን እና ሥጋ መብላት የተከለከለ ነው።  እንዲሁንም ኦኔን  ገላውን መታተጠብ፣ ፀጉሩን መስተካከል እና ሰላም ማለት ይችልም። አንድ ዘመዱ የሞተበት ከቤቱ መውጣ አይችልም። ነገር ግን ለማቹ ከሆነ ይቻላል። ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ለሚቀጥሉት ሰባት ሀዘን ቀናት  ለሟቹ ዘመዶች ስራ መስራት አይችሉም። ነገር ግን ከዘምዶቹ አንዱ በንግድ የሚተዳደር እና ሰባት ቀን ሱቁን ከዘጋ የሚከስር ከሆነ፤ በእነዚህ ቀናት በህግጋቱ መሰረት መስራት ወይንም ሱቁን ለተወሰነ ጊዜ መክፈት ይችላል።  ነገር ግን ይህን በዚህ እውቀት ካላቸው ሊቃውንቶች ጋር በመወያየት መሆነ አለበት።

አኔኑት በሰንበት እና በበዓላት

አኔኑት የሚለው ህግጋት በሟቹ ቤተሰቦች ላይ የሚውለው በአዘቦት ቀን ሲሆን ነው።  ስለዚህ አንድ ሰው ሰንበት ወይንም በዓላት ሊገባ ሲል ቢሞት እና ቀብሩ የሚፈፀመው ከሰንበት በኋላ ወይንም ከበዓል በኋላ ከሆነ፤ የአኔኑት ህግጋት ከሟቹ ቤተሰቦች ሰንበት ወይንም በዓሉ እስከሚገባ ይሆናል። የሰንበት መግቢያ የቀኑን ፀሎት ወይንም የበዓሉን መግቢያ የቀኑን ፀሎት  ይፀያል። ወይንም የሰንበት ቀን እና የበዓል ቀን ከወጣ በኋላ፤ የአኔኑት ህግጋት እንደገና እስከሚቀብር ድረስ ይሆንበታል። ስለዚህ እስከሚቀብር ድረስ ማንኛውንም ትዕዛዝ መፈፀም አይችልም። ለምሳሌ የሰንበት ወይንም የበዓል  መውጫ ፀሎት መፀለይ አይችልም። እንዲሁም ሰንበትን ወይንም በዓላትን በኣቭዳላ መሸኘት አይችልም። ነገር ግን "ሀማብዲል ቤን ኮዴ ልሆል ማለት ያስፈልገዋል።" ከቀብሩ ሥነ- ሥርዓት በኋላ አብዳላ ማድረግ ወይንም ሰንብት እስከ ማክሰኞች መሸኘት አለበት። ነገር ግን በዓላት ከሆነ እስከ በነገታው ድረስ ነው አብዳላ ማድረግ የሚችለው። እንዲሁም በሰንበት ወይንም በበአላት ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም እና ኦሪት መማር  የተከለከለ ነው።  ነገር ግን ሽታይም ሚክራ ኤሀድ ትርጉም ማንበብ ይችላል።  እንዲሁም የሀዘን ህግጋትን እና ለልብ ደስታ የማይሰጡ ነገሮችን መማር ይችላል። የሰንበትን መዝሙር መዘመር፤ ስጋ፣  ወይን መብላት እና መጠጣት ይችላል።

በሰንበት የኦኔን የፀሎት ህግጋት

በፀሎት ቤት መቀመጫ ህግጋት፦ ሁሌ በሚቀመጥበት ቦታ አይቀመጥ።

ካዲሽ የሚለውን ፀሎት በአኔኑት ሰንበት፦ይህ ከባህል ጋር የተያያዘ ስለሆነ፤ እንደማህበረሰቡ ይለያያል። ነገር ግን   በህዝበ እስረኤል ዘንድ ይህን ፀሎት ዘመዱ ሞቶ ሳይቀብር በሰንበት ቀን ማለት ይችላል፡ ። 

የካሀናት ቡራኬዎች፦ የማቹ ዘመድ ኮሄን(ካህን) ከሆነ ለካሀናት ቡራኬ  ህዝቡን ለመባረክ አይውጣ። ስለዚህ "አቤቱ አምላካችን ህዝብህን እስረኤል ፍቀድ " ከሚለው ፀሎት በፊት ከፀሎት ቤቱ ይውጣ። እንዲሁም የአስራ ሥምንቱ ቡራኬዎች ድግም ንባብ እና ወደ ኦሪት የመቅረብ ህግጋት፦  የህዝብ መሪ መሆን እና ወደ ኦሪት መውጣት አይችልም።

የአኔኑት ህግጋት በዓመቱ በዓላት፦

በሆል ሀሞኤድ የአኔኑት ህግጋት መሆን ይቻላል።

በአስተሰርዮ የአኔኑት ህግጋት መሆን ይቻላል። ስለዚህ ስጋ  መብላት እና ወይን መጠጣት የተከለከለ ነው። ነገር ግን ለበዓሉ ክብር ሲባል ምቅቤ ውስጥ መጥለም ይችላል።

አንድ ዘመዱ የሞተበት ሰው(ኦኔን) በዳስ በዓል በሚገባበት ቀን ዳስ መስራት ይችላል።

ኦኔን በሆሻና ራባ በሚደርገው የኦሪት ትምህር ወይንም ንባብ የተከለከለ ነው።

በሆሻና ራብ የአኔኑት ህግጋት እንደ አዘቦት ቀን ይሆናሉ።

በሲምሀ ቶራ ዘመዱ የሞተበት ሰው ኦሪቱን ሳይዘፍን መዞር ይችላል።

በሲምሀ ቶራ "ቭዞት ብርሀ" የኦሪት ክፍል ሽታይም ሚክራ ኤሀድ ትርጉም ማንበብ ይችላል።

አንዳንድ ሊቃውንቶች ዘመዱ ሞቶ ሳይቀብር ያለ ሀዘንተኛ ወደ ኦሪት በሲምሀ ቶራ እንዲቀርብ ይፍቅዳሉ።

በሀኑካ በዓል ከቤተሰቡ አንዱ እንዲያበራ በመጀመሪያ መለመን ይችላል። ነገር ግን የሚያበራለት ሰው ከለለ እራሱ ያለ ቡራኬ ማብራት ይችላል።

በሀኑካ በዓል በመጀመሪያው ቀን የአኔኑት ህግጋት ካለፈ በኋላ ሸሄያኑ የሚለውን ቡራኬ መባርክ ይችላል።

ቀብሩ የሚፈፀመው በፑሪም ማታ ከሆነ፤ ሚጊላውን( የብራና መፅሀፉን- የአስቴርን መፅሀፍ ሲነበብ መስማት ግዴታ አለበት)፤  ከቀብሩ በኋላ ደግሞ ጊዜ ካገኘ እንደገና  ያለ ቡራኬ የአስቴርን መጽሐፍ ያንብብ።

በፑሪም ማታ ስጋ መብላት እና ወይን መጠጥት የተከለከለ ነው።

ቀብሩ የሚፈፀመው በፑሪም ቀን ከሆነ፤ በፑሪም በሚደርጉትን ትዕዛዛት መፈፀም ግዴታ አለበት(እስራኤል ሆይ ስማ የሚለውን  ፀሎት፤ እንዲሁም የአስቴርን መፅሀፍ ማንበብ  ግዴታ አለበት።)  ሌላው  በቀን የብራ መጽሐፉ ሲነበብ መስማት አለበት፡፡ ከቀብሩ በኋላ ደግሞ ጊዜ ካገኘ እንደገና  ያለ ቡራኬ የአስቴርን መጽሐፍ ያንብብ።

በፑሪም ቀን ስጋ መብላት እና ወይን መጠጣት ይቻላል። ይህም ሰውየው ኦኔን ቢሆንም።

በግንብ በተገነቡ  እና በተከበቡ ከተሞች(ሾሻን ፑሪም) በይካቲት 15 በየሩሳሌም እንዲሁም በሌሎች ከተሞች  የአኔኑት ህግጋት እንደዘቦት ቀን ይሆናል።

የቦካ ነገር በፋሲካ መፈለግ፦ ኦኔን የሆነ ሰው መጋቢት 14 ምሽት  እርሾ ያለው ነገር የሚፈትሽለት ሰው መምረጥ አለበት። ነገር ግን የሚፈትሽለት ሰው ከለለ፤ እራሱ ያለቡራኬ ይፍትሻል።

የቦካ ነገሮችን ማውደም(መሰረዝ)፦ ሀዘንተኛው ማምሻ ማውደም ይችላል። በጠዋት ደግሞ ኮል ሀምራ የሚባለውን ፀሎት ይላል።

ቤተዘመዱ ሞቶ ሳይቀበር እና የበኩር ጅ  የሆነ ሰው በፋሲካ ምሽት- ግዴታ መፆም አለበት። መፅሀፍ ተመረው ከጨረሱት ጋር ማዕድ ላይ አብሮ መቅረብ አይችልም።

በፋሲካ ምሽት ሀዘንተኛ(ኦኔት) ወደ ጎን ዘንበል አይልም።

በኦሜር ቆጠራ ያለ ቡራኬ በመጀመሪያ ይቁጠር። ነገር ግን ቆጠራው ጊዜ የሚያልፍ ከሆነ፤ ከቀብሩ በፊት  ያለ ቡራኬ ይቆጥራል። ከቀብሩ በኋል ግን የኦሜርን ቆጠራ ከቡራኬው ጋር በመቁጠር ይቀጥላል።

ሀዘንተኛ በሻቡኦት የሚነበበውን የኦሪት ክፍል ማንበብ ይችላል።

ኦኔን በሀምሌ ዘጠን ፆም ፀሎት መፀለይ ግዴታ የለበትም። እንዲሁም የኤሀ የብራና መጽሐፍ ማንበብ እና  በፆሙ የሚነበቡ የሀዘን ቅኔዎችን  ግዴታ ማንበብ  የለበትም።

ኤሩቭ ታብሽሊን፦

የበዓል ምሽት ከሰንበት አጠገብ አብሮ ሲውል እና የአንድ ሰው ዘመድ በበአሉ ምሽት ሲሞት፤  ቀብሩ የሚፈፀመው ከሰንበት በኋላ ከሆነ፤ ኤሩብ ታብሽሊን በዓሉ ከመግባቱ በፊት ቡራኬውን ባርኮ ማስቀመጥ አለበት።  ነገር ግን ቀብሩ የሚፈፀመው በበአሉ ምሽት(በዓሉ ሳይገባ) ከሆነ፤ ከቀብሩ በኋላ ያስቀምጥ።

የጨርቃ ቡርኬ

አንድ ሰው ዘመዱ ሞቶ፤ እስከሚቀበር ድረስ የጨርቃ ቡርኬ የሚባልበት ጊዜ ገደብ የሚያል ከሆነ፤ ኦኔን ማቹን ሳይቀብሩ ወሩን መቀደስ ይቻላል።

የተገራዡ ልጅ አባት በሀዘን ላይ ሲሆን 

አንድ ሰው  ወንድ ልጅ ተወልዶለት፤ እንዲሁም ከቤተሰቡ አንዱ  ሲሞት፦  የግርዛቱ ሥነ-ሥርዓት የሚፈፀመው ከቀብሩ በኋላ ነው። የማይቻል ከሆነ ን ህፃኑን ሌላ ሰው ቡራኬውን ባርኮ መገረዝ ያስፈልጋል።

ኦኔን የሆነ ሰው ለልጁ ግርዛት መሰናዶ ሲል ከቤቱ መውጣት ይችላል።   

አንድ ሰው ሀዘንተኛ ሆኖ፤ የግርዛት ሥነ ሥርዓት ለልጁ የሚይዝ፦

በመጀመሪያ አንድ ሰው ኦኔን ከሆነ ወይንም የሞተ ዘመዱን ሳይቀብር ከሆነ ለዚህ መጋበዝ አያስፈልግም። ነገር ግን ይህ ነገር ከመከሰቱ በፊት ከጋበዙት፤  በመጀመሪያ ወደ ሄብራት ካዲሽ በመደወል ለቀብሩ የሚያስፈልጉ ነገሮችን መፈፀም አለበት። ከዚህ በኋላ በግርዛቱ ሥነ-ሥርዓት መሳተፍ እና ህፃኑን በግርዛት ሥዓት መያዝ ይችላል።

ሀዘንተኛ ሆኖ እና የሚገርዝ ሰው፦

የግርዛቱን ሥነ-ሥርዓት የሚያካሄደው ሰው ኦኔን ከሆነ፤ ግርዛቱ መፈፀም ያለበት ከቀብር በኋላ ነው። ነገር ግን የማይቻል ከሆነ፤  ሌላ ሰው ቡራኬውን ከባረከው በኋላ እርሱም  ይገርዘዋል።አንድ ሀዘንተኛ እና በግርዛት ሙያ የተሰማራ ሰው ለግርዛት ሲል ከቤቱ መውጣት ይችላል።

ወንድ ልጅ መዋጀት(ፒድዮን ሀቤን)፦

አንድ ሰው ዘመዱ ሞቶበት እና ቀብሩ እስካልተፈፀመ ድረስ የመጀሪያ ወንድ ልጁን መዋጀን አይችልም። ስለዚህ ይህን የመዋጀት ሥነ-ሥርዓት ከቀብሩ በላኋ እንዲሆን ወደ ሌላ ጊዜ መለወጥ ያስፈልጋል።

ካሀኑ  በሀዘን ላይ ከሆነ የመጀመሪያ ወንድ ልጅ መዋጀት አይቻልም። ነገር ግን ሌላ ካህን ከለል መዋጀት ይቻላል።

የባራክ እና የጉርምርምታ ቡራኬዎች፦

በሀዘን ላይ ያለ ሰው የጉርምርምታ እና የባራክ ቡራኬዎችን መባረክ ግዴታ የለበትም። 

ከአልጋ ላይ የስራኤል ሆይ ስማ ንባብ እና የእንቅልፍ ቡራኬ፦

በሀዘን ላይ ያለ ሰው ከአልጋ ላይ የሚባለውን  የእስራኤል ሆይ ስማ ንባብ ግዴታ ማለት አለበት።በሀዘን ላይ ያለ ሰው ለፅዳቃ መስጠት ይችላል። ነገር ግን ለሞተው ዘመዱ ለነብሱ  ይማር(መማሪያ )ይሆን  ማለት አለበት።

የካሀናት ርክስና

ካህን ለሞተ ሰው መርከስ የለበትም።  ማለትም እስከ ሁለት ሜትር ቅርበት ወደ አስከሬኑ መቅረብ የለበትም።  አስከሬን ካለበት ቤት መግባት የተከለከለ ነው። ነገር ግን አንድ ካህን መርከስ ካለበት ከሰባቱ ዘመዶች(አባቱ፣ እናቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣  ወንድሙ፣ እህቱ(ያላገባች ከሆነች እና እህትነቱ በእናቱ ሳይሆን በአባቱ ከሆነ) እና ሚስቱ ከሆነች፤ ለእነርሱ መርከስ አለበት፡፡ አንድ  ካህን የሚረክሰው የሞተው ሰው እስከነ ሙሉ አካላቱ ከሆነ  ነው። ነገር ግን አንድ አካል ከጎደለው፤ መርከስ አይችልም።  እንዲሁም  የሟቹን የሰውነት አካል ከአጠገቡ ቢያስቀምጡት እና  ወይንም ቢሰፉት፤ በተጨማሪም አንድ በሟቹ  አስከሬን ላይ ኦፕሬሽን ቢደረግ  ካህን የሆኑ ቤተዘመዶቹ መርከስ አይችሉም። ይህ ቢሆንም  የዘመዱን አስከሬን እስከ ቀብሩ ድረስ  መሸኘት ይችላል። ነገር ግን በመንገድ እስከ ሁለት ሜትር ርቀት መቃብር የለለበት መሆነ አለበት።

ንፅህ  እና መታጠብ፦

የሙታን የንፅህና እና  የመታጠብ ሥነ ሥርዓት የሚካሄደው በሄብራት ካዲሻ ድርጅት በሚሰሩ ሰራተኞች ይሆናል። እነዚህ ሰራተኞች ደግም  በይሁዳዊያን  የሀይማኖት ህግጋት እና ልምዶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፉ  በመጡት የሀይምኖት ሥርዓተ- ደንብ መሰረት ነው። ስለዚህ የሟቹ ክብር በተጠበቀ በት መንገድ ወንዶች የወንድ አስክሬን ሲያፀዱ፤ ሴቶች ደግሞ የሴቶችን አስከሬን ያፀዳሉ።

ሥርዓተ-ቀብር እና የቀብር ሥነ-ሥርዓት፦

ሥርዓተ-ቀብር

ሥርዓተ ቀብሩ የሚጀምረው ከማቹ ቤት ወይንም ከመካነ መቃብሩ በር አጠግብ ነው። አስከሬኑን ወደ ቀብር ከመወሰዱ በፊት አንድ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ቤተ ዘመዶች ሟቹን ዘመዳቸውን እንዲለዩ ይጠየቃሉ። ከዚህ በኋላ የቀብሩን ሥነ- ሥርዓት የሚያካሄደው የሄብራት ካዲሻ ሰራተኛ  ካዲሽ ሲሆን ፤ ከመዝሙር ዳዊት የተወሰደ ፀሎት ያደርጋል።

የልብስ መቅደድ ሥነ ሥርዓት- ይህ የሀዘን መግለጫ ምልክት ነው።  ስለዚህ የፀሎት መሪው ወይንም የቀብሩን ሥነ- ሥርዓት የሚያካሄደው ሰው  በመቆረጭት የሀዘንተኞችን ልብስ ከደረታቸው በላይ ትንሽ ይቀዳል። ይህንም ሥነ ሥርዓት ሲካሄድ፤ ሀዘንተኛው  እንዲ በማለት ይባርካል፦ ባሩህ አታ አዶናይ ኤሎሄኑ ሜሌህ  ቮላም  ዳያን ሀኤሜት ( ብሩክ አንተ እግዚአብሄር አምላካችን  የአለም ንጉስ እውነተኛ ፍርድን የምትሰጥ።)

ሀዘንተኞች የሞተባቸው እናት ወይንም  አባት ከሆነ- ልብሳቸውን የሚቀዱት በግራ በኩል(ልብ በሚገኝበት በኩል) ያለውን ሲሆን፤ ለሌሎች ዘመዶች በቀኝ በኩል ይደረጋል።

አስከሬኑን ወደ መቃብር መሸኘት ትልቅ ትዕዛዝ ነው። ይህም "ጓደኛህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ " ከሚለው ትዕዛዝ አንዱ ነው። በዚህም ምክንያት ይህን ትዕዛዝ የፈፀመ ሰው በዚህ አለም ጥሩ ነገር ያገኛል ፡፡ እንዲሁም በሚመጣው አለም ከእግዚአብሄር መልካም ሽልማት ይጠብቀዋል። አንድ ሰው ሲሞት በተቻለ መጠን በዚያው ቀን ለመቅበር ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። አንድ አስከሬን ወደ ቀብር ሲሸኝ ከመዝሙር ዳዊት የተወሰኑ ምዕራፎችን ይነበባሉ። በተላይ ምዕራፍ 91 ሲባል ሴት ከሆነች ደግሞ ምዕራፍ 36 ይባላል።

ሥርዓተ ቀብሩ ሲካሄድ ምፅዋት ለነብሱ ይማር ተብሎ ሲሰጥ ይህን ይባላል፦ ይህን ምፅዋት የምሰጠው የማቹን ነብስ  እግዚአብሔር ይህን የሞተ ሰው  ከጥፋት ሁሉ  እንዲያድነው እና ፃድቃን ከደረሱበት ደርጃ እንዲደር ነው። 

አንድን ቦታ አስከሬኑን ይዞ በፀሎት ቤት ሲያልፉ፤ አልጋውን ይዘው በመቆም "አኪቫ ቤን ማለለኤል ኦሜር(ማሰሄት አቮት ምዕራፍ ሶስት) እንዲሁም ሁለት ስንኞችን ከፂዱቅ ሀዲን "ሀፁር ታሚም"፣ ጋዶል ሀኤፃ እና ራቭ አሊላ" የሚለውን  ከተባለ በኋላ ቤተሰቦች ወይንም ልጆች ሙሉ ካዲሽ ያደርጋሉ።

ካዲሽ ከተደረገ  በኋላ  እግዚአብሔር በምሕረት የተሞላ ነው የሚለውን ፀሎት ከተባለ በኋላ አስከሬኑን የሚሸኙት ሰዎች በሁለት ተራ ይቆማሉ። ሀዘንተኛውም ጫማውን አውልቆ በሁለት ተራ በቆሙት ሰዎች መካከል ያልፋል። እነርሱም እንዲህ በማለት ያስተዛዝኑታል፦ ከጺዮን ሀዘንተኞች ጋር እግዚአብሄር ያፅናችሁ።"  በሆል ሀሞኤድ ይህ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል። ነገር ግን ሀዘንተኛው ጫማውን አያወልቅም።

ከመካነ መቃብሩ ውጭ ስንወጣ እጃችን ታጥበን ማድረቅ የለብንም።  አንድ ሰው የእጅ መታጠቢያውን እንደጨረሰ ወዲያ ተቀብለን መታጠብ የተለመደ አይደልም። ስለዚህ ከቦታው እስከሚመልሰው ድረስ መጠብቅ ያስፈልጋል። ከጨረሱ በኋላ እቃውን ቁልቁል ይደፋዋል። ሌው የተለመደ ነገር ቢኖር ከመካነ መቃብሩ እስከ ቤታቸው ሀዘንተኞችን  መሸኘት ነው።

ሟቹን መለየት፦

በመካነ መቃብሩ አስከሬኑ እና ቤተዘመዱ ለተወሰነ ጊዜ የሚቆዩበት እና የሚለያዩበት ክፍል አለ። ስለዚህ በዚህ ክፍል ብቻችሁን ለመሆን ብትፈልጉ የሄብራት ካዲሻ ሰራተኞችን እንዲወጡ መጠየቅ ትችላላችሁ።  የሟቹን ፊት የሚገለፀው  ሟቹን ለመለየት በመጣው ዘመዱ  ፊት ብቻ ነው። ይህም የሚሆነው ወደ ቀብር የመጣ አስከሬኑን ማንነት  ለማረጋገጥ ነው።

የልብስ ቀደዳ ሥነ-ሥርዓት

ቤተሰቡ እና የቅርብ ጓደኞቹ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ በሚቀርብበት ‹መድረክ› አቅራቢያ በሚገኘው የቀብር ቤት ውስጠኛ ክፍል ይሰበሰባሉ ፡፡ በእስራኤል ባህል መሠረት ሟቹን ሊሸኙ የመጡ ካሀናት በዚህ ቦታ በአንድ ጣሪያ ስር አይቆሙም ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ለካሀናት ተብሎ ለብቻው  የሚዘጋጅ ዳስ አለ። ከዚያ ዳስ ሆነው አስክሬኑን ማየት የሚችሉበት ቦታ እና የሟቹ ታሪክ ሲነበብ የሚሰሙበት ቦታ ይዘጋጅላቸዋል።  ከዚህ ቦታ የሟቹ እናት እና አባት፣ ባል/ሚስት፣ ልጆች እና እህትን ወንድሞች ወደ መድረኩ በመቅረብ የልብስ ቀደዳ ሥነ-ሥር  ይፈፅማሉ።  አንዳንድ ማህበረሰብ ላይ ይህ ሥነ ሥርዓት  በመካነ መቃብሩ አይፈፀም።  ምክንያቱም ከቤት የሞት መርዶ ሲሰሙ ስለሚቀዱ። ለምሳሌ የየመን ይሁዳዊያን መጥቀስ ይቻላል። እንዲሁም ከቃብር በኋላ የሚፈፀሙ የስፋራዲም ማህበረሰብ አሉ።

የልብስ ቀደዳ ሥነ-ሥርዓት የሚካሄደው በህብረተሰቡ የተለመደ ባህል እና ሀዘንተኞች ልብሳቸውን የሚቀዱት፤  ዘመዳቸው በመሞቱ የተፈጠረውን ክፍተት ወይንም ከባድ የጥፋት ሀዘን የሚያመልክት  ነው።  የዚህ ሥነ ስርዓት ምንጭ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ሲሆን፤  ያቆብ በልጁ  በዮሴፍ መጥፋት ምክንያት ሞቷል ብሎ ስላዘነ(ኦሪት ዘፍጥረት 37,34) ልብሱን ስለቀደደ ከዚህ ነው የተወሰደው።  ድሮ ሰዎች የሞት መርዶ ሲሰሙ ነበር እራሳቸው ልብሳቸውን የሚቀዱት የነበር። አሁን ግን አብዛኛው ማህበረሰብ ይህን ሥነ ሥርዓት የሚፈፅመው በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ጊዜ ነው። ይህን ሥነ ስርዓት የሚፈፅመውም የሄብራት ካዲሻ ሰራተኛ ሲሆን፤ ለወንዶች ወንድ ለሴቶች ደግሞ ሴት ትፈፅማለች።  ከተቻለ ደግሞ አንድ ቤተዘመድ ይህ መፈፀም ይችላል። ሀዘንተኞች የሞተባቸው እናት ወንም አባት ከሆነ- ልብሳቸውን የሚቀዱት በግራ በኩል(ልብ በሚገኝበት በኩል)ከደረታቸው በላይ  ያለውን ሲሆን፤ ለሌሎች ዘመዶች በቀኝ በኩል ይደረጋል።  ልብሱን ቢያንስ  8.5 ሴንቲ ሜትር ያህል መቅደድ ያስፈልጋል። የሄብራት ካዲሻ ሰራተኛ ትንሽ ከቀደደው በኋላ ሀዘንተኛው ከላይ ወደታች   8.5 ሰንቲ  ሜትር እስከ ከሚደርስ ይቀደዋል። ከዚህ በኋላ እንዲህ በማለት ይባርካል፦ ባሩህ አታ አዶናይ ኤሎሄኑ ሜሌህ  ቮላም  ዳያን ሀኤሜት( ብሩክ አንተ እግዚአብሄር አምላካችን  የአለም ንጉስ እውነተኛ ፍርድን የምትሰጥ።) ሰየው የሞተው በበዓል ከሆነ ሰባቱ ከበዓሉ በኋል ይሆናል።  አንድንድ ሰዎች ደግሞ የልብስ ቀደዳውን ሥነ ሥርዓት  ከበዓሉ በኋላ የሚያደርጉ አሉ።  እንዲሁም እናት ወይንም አባት ሲሞት በሆል ሀሞኤድ የልብስ ቀደዳውን ሥነ ሥርዓት የሚፈፀሙ አሉ።  እንዲሁም  ከእናት ወይንም ከአባት ውጭ ላሉ ዘመዶቻቸው የሚፈፅሙ እና የተቀደደው ልብስ በሆል ሀሞኤድ ሰባቱን ቀን ሁሉ ለብሰውት ይቆያሉ።  የተቀደደው ትልቅ ከሆነ በመርፌ ቁልፍ ማሳዝ ይቻላል። ነገር ግን ሰባቱ እስከሚያልፍ ድረስ መስፋት የተከለከል ነው። በእነዚህ ቀናትም የሀዘን ምልክት ሆኖ መታየት አለበት። ከሰባቱ  የሀዘን ቀናት በኋላ ሰፍተው የሚለብሱ ሰዎች አሉ። ነገር ግን የእናት ወይንም የአባት ሀዘን ከሆነ መስፋት ወይንም የተቀደደውን ማስተካከል አይቻልም። አንዳንዶች ደግሞ ይጥሉታል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓት፦

የልብስ ቀደዳውን ሥነ ስርዓት ከፈፀምን በኋላ እና "እውነተኛ ፈራጅ" የሚለውን ቡራኬ ከባረክነ በኋላ አስከሬኑን ወደ ቀብር ይወሰዳል። አልጋውን የሚይዙት ሰዎች ሀዘንተኞች ሳይሆን ለሟቹ የመጨረሻ ክብር ለመስጠት የመጡ ሰዎች መሆነ አለባቸው።  አፈር በሚመለስበት ጊዜ ሶስት ጊዜ "እርሱ ቸር ነው ይቅር ይላል፣ አያጠፋም፣ ቁጣውንም መመልስ ያበዛል፣ ቁጣውን ሁሉ አይወርድም፣ አቤቱ አድነነ በጠራነውም ጊዜ ንጉሳችን ይመልስልነ።" የሚለውን ስንኝ ይባላል። ከዚህ በኋላም አንድ የመዝሙር ዳዊት ምዕራፍ፣ ካዲሽ  እና  እግዚአብሔር በምሕረት የተሞላ ነው የሚለውን ፀሎት ያባላል።

ከቀብሩ ሥነ ሥርዓት በኋላ፦

የይቅርታ ልመና፦

"እግዚአብሔር በምሕረት የተሞላ ነው" ከሚለው ፀሎት በኋላ የሀዘን ተካፋዮች ትንሽ ደንጊያ ከቃብሩ ላይ ያስቀምጣሉ።  ይህ ልማድ የሟቹ ሰው ትውስታ በሰዎች ልብ ውስጥ እንደተቀረጸ ለማሳየት  ነው። ከዚህ በኋላ ይቅር እንዲላቸው ይጠይቁታል።

ለወንድ

ስሙን እና የአባቱን ስም በመጥራት፤ እኛ ከአንተ የምንለምነው  ይቅርታ እንድታደርገልን ነው። እንደሚገባህ ክብር አላደረግነም፤  ነገር ግን በተቀደሰችው አገራችን በሚደረገው ባህል መሰረት አድርገናል። በሰላም ሂድ፤  በሰላም በምኝታህ እርፍ፤ ሙታን ሲነሱ በእድልህ የምትነሳ ይሁን።

ለሴት

ስሟን እና የአባቷን ስም በመጥራት፤ እኛ ከአንቺ የምንለምነው  ይቅርታ እንድታደርጊልን ነው። እንደሚገባሽ ክብር አላደረግነም፤  ነገር ግን በተቀደሰችው አገራችን በሚደረገው ባህል መሰረት አድርገናል። በሰላም ሄጂ፤  በሰላም ከምኝታሽ  እርፊ፤ ሙታን ሲነሱ በእድልሽ  የምትነሺ ይሁን።

ውዳሴ

አንድ ሰው ሲሞት ከቀብሩ አጠግ የሰራውን መልካም ስራ እና የነበረውን ደርጃ መናገር የተለመደ ነው። የኦሪት ህግጋት የሰውየን ታሪክ መቀነስ አይስፈልግም ።  ስለዚህ ከነበረው ደርጃ ትንሽ እንኳ መጨመር የተፈቀደ ነው። ነገር ግን ከልክ በላይ መሆነ የለበትም። ይህም የምንማረው አብርሀም ለስራ ካደረገላት ውዳሴ ነው።

አንድ ሰው ሲሞት እንዳያወድሱት ትዕዛዝ ከሰጠ ትዕዛዙን ማክበር ግዴታ ያስፈልጋል። በወሩ መባቻ፣ በሀኑካ እና በፑሪም ቀናት እና የመጋቢታ እና በመስከረም ወር ለሞተ ሰው ውዳሴ አለማድረግ ተገቢ ነው።

የሀዘንተኞች ማፅናኛ መስመር፦

ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ አስተዛዛኝ ወንዶች በሁለት  ትይዩ ረድፎች ፊት ለፊት ቆመው ከመካነ መቃብሩ መውጫ በር ቆመው ሀዘንተኞችን ያስተዛዝናሉ። ቢያንስ በረድፉ አምስት ሰዎች መሆን አለባቸው፡፡ ሀዘንተኞች ጫማቸውን አውልቀው በአጠቃላይ በሁለቱ ረድፎች መካከል ያልፋሉ። በረድፍ የቆሙትም እንዲህ በማለት ያፅናኗቸዋል፦ "ከጺዮን ሀዘንተኞች ጋር እግዚአብሄር ያፅናችሁ።" በሆል ሀሞኤድ ጫማ የማውለቅ ልማድ  የተለመደ አይደልም።

ተጨማሪ ባህሎች፦ 

ከቀብሩ በኋላ ሰዎች ሲመለሱ፤ ወደቀብሩ በሄዱበት መንገድ ሳይሆ፤  በተለየ መንግድ መመለስ የተለመደ ነው።  ሲመለሱ መንግዱን ማስረዝም የተለመደ ነው። ምክንያቱም በሞቱ ምክንያት ሀዘኑን ለመግለፅ። ሀዘንተኞች እና የሀዘን ተካፎዮች እጃቸውን መታጠብ ግዴታ አለባቸው።  ሲታጠቡም በእያንዳንዱ እጅ ሶስት ጊዜ ዉሃ ማፍሰስ ያስፈልጋል። የታጠቡበትን ማስታጠቢያ ከእጅ ወደ እጅ አይተላለፍም። አንድ ሰው ከታጠበ በኋላ ሲያስቀምጠው፤ ሌላው ደግሞ አንስቶ ይታጠባል። እንዲሁም እጃችን ከታጠብን በኋላ ማድርረቅ(በጨርቅ /በሶፍት) አይስፈልግም።  ምክንያቱም ከሟቹ ጋር ላለመለያየት። ዉሃ ከእጃችን ተሎ ሲወድቅ ሟቹን ያስተውሰናል።

የክፋን ልብስ

በእስራኤል የክፈና  ባህል መሰረት  በስምንት የክፋል ልብስ አስከሬኑን ያለብሱታል። እነዚህ ልብሶች ደግሞ ከነጭ ጨርቅ የተሰፉ መሆነ አለባቸው።  የበለጠ ክብር ያለ እንዲሆን ከጥጥ የተሰራ ይሆናል። የክፋኑ ልብስ ከማንኛውም ነገር የነፃ እና ንፁህ መሆን ግዴታ አለበት።  የአለበበሱ ባህልም በእስረኤል ህዝብ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ባህል መሰረት ነው። ትንሽ በተለያዩ ማህብረሰቦች የባህል ልዩነት አለ።