ህግግታ እና ናህላዊ የሀዘን ልምዶች፡

በሰባተኛው ቀን

በሰባተኛው ቀን ጠዋት፤ የጠዋቱን ፀሎት ከፀለዩ በሁኋ፤ ሀዘንተኞች ይቀመጣሉ። ለመፀለይ የመጡት ሰዎች "ውዶች ቁሙ" በማለት ያዟቸዋል። የስፋራዲም ማህበረሰብ ደግሞ " እግዚአብሄር የዘላለም ብርሀን ይሆናልና የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሀይሽ ከዚያ በኋላ  አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም አይቋረጥም። እናት ልጅዋን እንደምታፅናና  እንዲሁ አፅናናችኋለሁ፤ በየሩሳሌም ውስጥም ትፅናናላችሁ።" የሚሉትን ሁለት ስንኞች ያነባሉ። ከዚህ በኋላ ሀዘንተኞች በቀብሩ ሥነ- ሥርዓት የቀደዱትን ልብስ(ለሰባት ቀን የለበሱትን ልብስ) ቀይረው ሌላ ልብስ(አዲስ መሆን የለበትም) ይለብሳሉ። የሚያስተዛዝነው ሰው ከለለ እና በሰንበት ሀዘንጠኛን ማፅናናት አይስፈልግም። ምክንያቱን በሰንበት የሀዘን ትዕዛዝ መፈፀም አይቻልም።  ከፀሎት በኋላ ከፀሎት ቤቱ ከወጡበት ጊዜ ጀመሮ የሀዘኑ ሥነ ሥርዓት ያበቃል።

ሌላው የተለመደ ነገ ቢኖር እና ግዴታ ያልሆነ ነገር፦ የሟቹን መቃብር  በሰባተኛው ቀን በመሄድ ማየት ነው። ከመቃብሩ አጠገብ ሰባት የዳዊት መዝሙር ምዕራፎችን ይነበባሉ፦ መዝሙር 33፣ 16፣ 17፥ 72፣ 91፣ 104፣ 130፡ ከዚህ በኋላ የሟቹን ስም የሚይዙትን ስንኞች ይነበባሉ። የይቅርታ ፀሎት በሚባልበት ቀን "አና በኮዋህ" የሚለውን ፀሎት ይፀለያል። አስር ሰው ካለ የሙት ልጅ ካዲሽ ይደርጋል። እንዲሁም "እግዚአብሔር በምሕረት የተሞላ ነው"  የሚለውን ፀሎት ይፀለያል።

ሰባተኛው ቀን ዳሰ እና በፋሲካ በዓል በአምስቱ ቀናት ከዋለ፤  ወደ መካነ መቃብሩ በመሄድ መቃብሩን ማየት አይቻልም። ስለዚህ በዓሉ እስከ ሚያልፍ ድረስ መቆየት ያስፈልጋል። የይቅርታ ፀሎት በማይደረግባቸው ቀናት(የወሩ መባቻ፣ 33 የኦሜር ቆጠራ፣ ጥር 15፣  ሀምሌ 15 እና በመጋቢት ወር ) በእነዚህ ቀናት የሟቹን ቀብር ሄዶ ማየት አይቻላል። በሀኑካ እና በፑሪም ወደ መካነ መቃብሩ ሄዶ ቀብሩን ለማየት፤ በማህበረስቡ ባህል ጋር የተያያዘ ነው። ቀብሩ ከጎበኙ በኋል ሀዘንተኞች ወደሚፈልጉት ስራ መሄድ ይችላሉ። ከዚህ ጊዜ አንስቶ የ 30ኛው የሀዘን  ቀናት ይጀምራል።

ሰላሳኛው የሀዘን ቀናት

 

ሰላሳኛው የሀዘን ቀናት ቆጠራ፦

ከፋሲካ በፊታ ያሉ  አስራ አራት ቀናት ለሰላሳው የሀዘን ቀናት ሲቆጠሩ፤ የፋሲካ በዓል የሀዘኑን ቀናት ስለሚያቋርጠው፤  16 ቀናት  ከበዓሉ በኋላ  መቁጥረ ያስፈልጋል።    እንዲሁም በሻቡኦት በዓል አስራ ስድስት ቀን ከበዓሉ በኋላ መቁጠር(መሙላት ያስፈልጋል)።ከዳስ በዓል በፊት ያሉት ቀናት ለሀዘን ቀናት ሲቆጠሩ፤ ከበዓሉ በኋላ ስምንት ቀን ለሰላሳው ቀን መቁጠር ያስፈልጋል፡፡ በብርሀነ ሰርቀ ሰላሳ የሀዘን ቀናት እስከ አስተሰርዮ  ብቻ ይቆጠራል፡፡ ምክኛቱም አስተሰርዮ የሀዘን ቀናት ስለሚያቋርጠው ነው፡፡ እንዲሁም አስተሰርዮ እስከ ዳስ በዓል ድረስ የሀዘን ቀናት ሲቆጠሩ፤ የዳስ በዓል የሀዘኑን ቀን ያቋርጠዋል፡፡

ሰላሳውን የሀዘን ቀናት ማቋረጥ፦

ሰባቱ የሀዘን ቀናት ከበዓሉ በፊት ወይንም በበዓሉ ዋዜማ ካለቀ፤ በዓሉ የሰላሳ የሀዘን ቀናት መቆጠር የሚጀምረውን ያቋርጠዋል።  ሰለዚህ ፀጉርን መስተካከል፤ ፂምር መላጨት እና በዓሉ ከመግባቱ በፊት ገላን ከቀኑ ፀሎት በኋላ መታጠብ  ይቻላል። በፋሲካ በዓል ደግሞ ከቀን እኩል በፊት ከላይ የተተቀሱትን ነገሮች ማድረግ ይቻላል።

ሰላሳ የሀዘን ቀን፡

ሰባቱ የሀዘን ቀናት ካበቃ በኋላ፤ 23 ቀናት በመጨመር የሰላሳው የሀዘን ቀናት ይሆናል። ሰለዚህ በእነዚህ ቀናት ትናንሽ የሀዘን ህግጋቶች ወይንም ምልክቶች ይፈፀማሉ።  ፀጉርን መስተካከል፤ ፂምር መላጨት እና  ጠፍሩን መጥፍር መቁረጫ መቁረጥ የተከለከለ ነው።  ነገር ግን ገላን በሙቅ ዉሃ መታጠብ ይቻላል።    የአሽከናዚም ማህበረሰብ የሆኑት ግን ለሰላሳ ቀን ያህል በሙቅ ዉሃ ገላቸውን አይታጠቡም። የታጠቡ ልብሶችን ከመልበሱ በፊት ለሌላ ሰው ለተወሰነ ጊዜ እንዲለብሰው ከሰጠው በኋላ ያን ልብስ መልበስ ይቻላል።  ወይንም የታጠብውን ልብስ ከምሬት ላይ ወይንም የተተኮሰውን ልብስ ካቁራፈደ በኋላ መልበስ ይችላል።  አዲስ ልብስ መልበስ የተከለከለ ነው።  ነገር ግን ሁለት ቀን ወይንም ሶስት ቀናት ለብሷቸው ከሆነ መልበስ ይችላል።  እንዲሁም በውጭ አገር የሰንብት ልብስ መልበስ የተከለከለ ነው። ሌላው ነገር አንድ ሀዘንተኛ የሰላሳው የሀዘን ቀን እስከሚያልፍ ድረስ ሚስት ማግባት አይችልም። ነገር ግን ሰርጉን በፊት የተወሰነ ከሆነ እና ያላገባ ከሆነ ይቻላል። የሚስት  ማጨት ሂደት በሰባቱ የሀዘን ቀናት እና   ሟቹ በተቀበረበት ቀንም ሊካሄድ ይችላል።

ሰላሰኛው ቀን፦

በሰላሰኛው ቀን ወደ መካነ መቃብሩ በመሄድ የሟቹን መቃብር ይታያል። ከዚያም የተወሰኑ የዳዊት መዝሙሮች፡ "አና በኮዋህ፡ እና የሟቹን ነብስ ለማስታውስ እግዚአብሔር በምህረት ይተሞላ ነው የሚለውን ፀሎት ይነበባል። አስር ሰው ካለ ደግሞ ካዲሽ ይደረጋል። ሰላሰኛው ቀን በሰንበት ቀን ከዋለ፤ ወደ መቃብሩ የሚሄደው እሁድ ነው።  ስለዚህ በሰላሰኛው ቀን ለወንድም፣ ለእህት፣ ለባል እና ለሚስት ፀጉርን መስተካከል እና ፂምን መላጨት ይፈቀዳል። ነገር ግን ሀዘኑ የአባት ወይንም የእናት ከሆነ በሰላሰኛው ቀን ፀጉር መስተካከል እና ሌሎችን ነገሮች ማድረግ አይፈቀድም። የተወሰነ ቀን ይወስዳል።

መታሰቢያነት እና የመቃብር ገለፃ፦

ሰላሰኛው  ቀን ወደ መቃብሩ በመሄድ የመታሰቢያ ፀሎት ይደረጋል።  የሚደረገው የፀሎት ዓይነት፦ ከመቃብሩ አጠገብ ሰባት የዳዊት መዝሙር ምዕራፎችን ይነበባሉ፦ መዝሙር 33፣ 16፣ 17፥ 72፣ 91፣ 104፣ 130፡ ከዚህ በኋላ የሟቹን ስም  በተመሰረተበት የፊደል ከመዝሙር ዳዊት በአሌፍ ቤት መሰረት የተዘጋጀውን መዝሙር 119 ይነበባል ።   አስር ሰው ካለ የሙት ልጅ ካዲሽ ይደርጋል። እንዲሁም "እግዚአብሔር በምሕረት የተሞላ ነው"  የሚለውን ፀሎት ይፀለያል። ከዚህ በኋላ ከመለየታቸው በፊት ትንሽ ደንጊያ ከመቃብሩ ላይ ያስቀምጣሉ። ይህም የሚያመልክተው ሟቹን እንዳይረሱት ለማሳየት ነው።  አውልቱ ከተሰራ ግራ እጃቸውን ከአውልቱ ላይ ያደርጋሉ። ይህ የሚያምለክተው በትቢተ ኢሳያስ ስለሙታን መነሳት የተፃፈውን "ሙታን  ሕያዋን ይሆናሉ፥ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፥ ጠልህ የብርሃን ጠል ነውና፥ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም። " የሚለውን ለማስታወስ ነው።

ሰላሰኛው ቀን በሰንበት ቀን ተዋለ፦

ሰላሳኛው ቀን በሰንበት ቀን ከዋለ፤ አርብ ወይንም እሁድ ወደ መቃብሩ መሄድ ይቻላል። እንዲሁም ይህ ቀን በሻቡኦት፣ በዳስ በዓል እና በፋሲካ በዓል የመጨረሻው ቀን ከዋለ በበነገታው(በኢሱር ሀግ) ወደ መቃብሩ ይሄዳል። ነገር ግን ይህ ቀብር በፋሲካ ወይንም በዳስ በዓል በመጀመሪያው ቀን ከዋለ፤ ወደ መቃብሩ የሚሄደው በበዓሉ ዋዜማ መሆን አለበት። ከዚህ በተጨማሪ በብርሀነ ሰረቀ ወይንም በአስተሰርዮ ከሆነ፤ በዓሉ በዋለ በበነገታው ወደ መቃብሩ ይኬዳል። ነገር ግን "እግዚአብሄር በምህረት የተሞላ ነው" እና የነብስ ይማር  ፀሎት አይደረግም።

የነብስ ይማር ሻማ፦

በሰላሰኛው ቀን ለነብስ ይማር ተብሎ ሻማ ይበራል።  ይህ ሻማም ለሀያ አራት ሥዓት መብራት አለበት። ሻማውን ከቤት ከፍ ባለ ቦታ ይቀመጣል።  እንዲሁ ተጨማሪ መብራት ከፀሎት ቤት ይበራል። ሌላው ሀዘንተኞች በሰላሰኛው ቀን ኦሪቱ ወጦ ከሚነበብበት ቦታ ፊት በዚህ ቀን በሚካሄዱት ፀልቶች  ማለፍ አለባቸው።

ሀውልት መስራት፦

በእስራኤል ህዝብ ባህል መሰረት ሀውልት መስራት የተለመደ ነው። ይህም በሊቃውንቶች አጠራር "ነብስ" ይባላል። እንዲሁም ከሀውልቱ ላይ  ሟቹ(ሟቿን ) የሚገልፁ አጭር ፅሁፍ ይፃፋል። ከዚህ በትጨማሪም ከሀውልቱ ላይ የሴት ሆነ  የወንድ ሀውልት   ስም/ስሟን ፤ የአባቷን  እና የእናቷን ስም  ከሀውልቱ ላይ ይፃፋል። እንዲሁም የሞተበትን ቀን በኢብራዊያን ካላንደር መሰረት ይፃፋል። ነገር ግን በጎርጎሪያን ካላንደር መሰረት አይፃፍም። ከውልቱ መጨርሻ ላይ፦ ታፍ.ኑን.ፃዲቅ. ቤት እና ሄይ (ת. נ. צ. ב. ה. )የሚባሉትን የኢብራይስጥ ፊደላት በምህረ ቃል  ይፃፋሉ።  ትርጉሙም እግዚአብሔር ነብሱን  በገነት ያኑረው ማለት ነው። አንዳንዱ በዚህ ቀን ማቹን በልቅሶ የሚያወድሱ ማህበረተስቦች ስላሉ፤ ልቅሶ በማይለቀስበት ቀን ወደ መቃብሩ አይሄዱም።

ሀውልት መስሪያ ጊዜ፦

በብዙ ቦታዎች የሟቹን ሀውልት የሚያሰሩት በሰላሳኛው ቀን ነው።  ሰለዚህ ቀድም ብሎ ሀውልቱን ከሚሰራ ሰው ጋር መዋዋል ያስፈልጋል።  ምክንያቱም  ስራው ብዙ ጊዜ ሊወስድ ስለሚችል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ሀውልቱን የሚያሰሩት ዓመት ከሞላ በኋላ ነው።

የሀዘን ዓመት፦

የሀዘን ዓመት፦

አባት እና እናት የሞቱባቸው ሰዎች እስከ አስራ ሁለት ወራት ያህል ለወላጆች ክብር ሲባል የሀዘን ምልክት ያደርጋሉ። ዓመቱ አስራ ሶስት ወራት ሲሆን የሀዘኑ ገደብ አስራ ሁለት ወር ብቻ ነው።  ሰልዚህ በአስራ ሶስተኛ ወር የሀዘን ህግጋት አይፈፀሙም።   አስራ ሁለት ወር የሚቆጠረው ከሞተበት ቀን ጀመሮ ነው።

ሀዘን

አንድ ሀዘንተኛ በማንኛውም ደስታ መሳተፍ አይችልም። ለምሳሌ በሰርግ፣ በግርዛት ሥነ ሥርዓት ላይ  መሳተፍ የተከለከል ነው። ነገር ግን የሚፈቀድበት አጋጣሚ አለ። ስለዚህ ግዴታ ከኦሪት አዋቂ መጠየቅ ያስፈልገዋል። እንዲሁም አዲስ ልብስ መልበስ የተከለከለ ሲሆን፤ መልበስ ግዴታ ካለበት በመጀመሪያ ለሌላ ሰው ለሁለት ፣ ሶስት ቀን እንዲለብሰው ከሰጠው በኋላ መልበስ ይችላል። እንዲሁም የሰንበት ልዩ ልብሶች በአዘቦት ቀን መልበስ የተከለከለ ነው።  ከዚህ በተጨማሪ ዘውትር በፀሎት ቤት የመቀየር ልምድ ሲኖር ሌሎች ደግም  በሰንበት  የመቀየር ልምድ የለላቸው ስዊች አሉ። ከአስራ ሁለት ወራት በኋላ ስለሟቹ ሲስማ ነብሱ በሰማይ ትማር(ነብሱን ይማረው) ይባላል።

የካዲሽ ፀሎት፡

አንድ ሰው ሲሞት፤ ከሞተበት ቀን ጀምሮ  ወንድ ልጆቹ ለአስራ አንድ ወራይ ያህል ካዲ የሚባለውን ፀሎት ሲያደርጉ፤ ሌሎች ደግሞ ለአስራ ሁለት ወራት የሚያደርጉ አሉ። ሊቃውንቶ በፃፉት መፅሀፍ ላይ ለሟቹ ትልቅ ስራ እና ገነት እንዲገባ ያደርገዋል። ይህ ፀሎት በሰንበት እና በበዓላት ቀናት ይባላል። ስለዚህ አንድ ሰው ካዲሽ የሚልለት ሰው ከለለ፤ ሌላ ሰው ቀጥሮ ይህ ፀሎት እንዲያደርግ ማድረግ ይቻላል። ይህ የተቀጠረ ሰው ሁልቀን ከፀሎት በፊት  ጠዋት ካዲሽ የሚደርገው ፀሎት ለከ--------ነብስ ይማር እንዲሆን ነው ማለት አለበት።  ነገር ግን የዚህ ፀሎት ሽልማት የሟቹ ልጅ ካለው ነው። ስለዚህ የሟቹ ልጅ ካዲሽ የሚያደርግ  ከሆነ፤ ካዲሽ ለሚያደርገው ፀሎት ትልቅ አስተዋፅ ኦ አለው።  እንዲሁ በዚህ ጊዜ የሚፀለየው ፀሎት ከካዲሹ የበለጠ ሽልማት አለው። ካዲሽ መድርጉን በሚያቋርጥበት ቀን ወደ ኦሪት መውጣት አልበት።

ዓመታት፦

አባት/ እናት ሲሞቱ  ለአስራ ሁለት ወራት  የሀዘን ልምድ  ይደረጋል። ለሌሎች ዘመዶች ግን  ለሰላሳ ቀናት ብቻ ነው።  ነገር ግን ካዲሽ  ለዓመት ያህል ይደረጋል። ስለዚህ ሀዘንተኛው በደስታ እስከ አስራ ሁለት ወራት መሳተፍ አይችሉም።  ከዚህ በተጨማሪም አዲስ ልብስ መግዛት፣ አዲስ የቤት እቃዎችን መግዛት የተከለከለ ነው። ነገር ግን እቃው ወይንም ልብሱ አስፈላጊ ከሆነ መግዛት ይቻላል። እንዲሁም አዲስ ቤት መቀየር የተከለከለ ነው።  እንዲሁም የፀሎት መሪ መሆነ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ቦታ አንድ የተወሰነ ፀሎት መሪ ስለሚኖር፤ ግዴታ ስላለበት ፀሎቱን ልምራ ማለት አይችልም። እንዲሁም ሀዘንተኛው የምስጋና ፀሎት በሚፀልይበት ቀን(የወሩ መባቻ ወይንም በዓል)ሲሆን የፀሎት መሪ መሆን እና ለአዲስ ነገር የሚባረከው ቡራኬ በሚባረክበት ቀን የኦሪት በፀሎት ቤት አንባቢ መሆን  አይችልም።  አስራ ሁለት ወራት ከሆነ ካዲሽ ማድረግ አያስፈልግም። በዚህ ፈንታ ለነብስ ይማር  የኦሪት ትምህርት መማር ያስፈልጋል።  ከዚህ በኋላ ካዲሽ ደረባናን የሚባለውን ካዲሽ ልጁ ያደርጋል።

የዓመታት ቀን መወሰን፦

አንድ ሰው ሲሞት፤ የሞተበት ቀን የወሰነው በኢብራዊያን ካላንደር መሰረት ነው።  ሰውየው ከሞተ ከሁለት ቀን በኋላ ከተቀበረ፤ የአመታቱን ቀን የሚወስነው በተቀበረበት ቀን ይሆናል። ነገር ግን ሰውየ ከሞተ በሁለተኛ ዓመት ጀመሮ የዓመታቱ ቀን  በሞተበት ቀን እንዲሆን መወሰን ያስፈልጋል።

የፀሎት መሪ እና ማፍቲር፡

የዓመታቱ ቀን ከመደርሱ በፊት በሚውለ ሰንበት፤ ለሀዘንተኛው በፀሎት ቤት ጠዋት በመሄደ ወደ ኦሪት በመጨረሻ ይቀርባል። ስለዚህ  የመጨረሻውን የኦሪት ንባብ እና የነቢያት የሚነበውን ንባብ ለሀዘንተኛው ይጠበቃል። እንዲሁም ከኦሪቱ ንባብ በኋላ የሰንበትን ተጨማሪ (ሙሳፍ) ፀሎት ይፀልያል። ሌላ በሰንበት መውጫ የማታውን ፀሎት ሀዘንተኛው የፀሎት መሪ ሆኖ  ይፀልያል። በዚህ የማታ ፀሎት ጊዜ አንዲት ነበስ ወደ ገሀነም የምትመለስበት ጊዜ  ስለሆን ነው። ስለዚህ የአንድ  ሰው ልጅ ይህን ፀሎት በማድረግ ወደዚያ ከመሄድ የማዳን እድል ሊኖረው ይችላል።ይህም ለሟቹ ነብስ ይማር ከፈተኛ ተፅዕኖ ስላለው ነው።  እንዲሁም በሰንበት በቀበያ ፀሎት ማታ ሀዘነተኛው በፀሎት መፀለያው መድረክ ያልፋል።

የነብስ ይማር ሻማ፦     

በዓመታቱ ቀን  ለነብስ ይማር  ሻማ ከቤት እና ከፀሎት ቤት  ለሀያ አራት ሥዓት የሚበራ ሻማ ይበራል።  ሻማው ከአንድ ቀን በላይ ቢበራም፤ ሻማው በራሱ ጊዜ አልቆ እስከ ሚጠፋ ድረስ ማጥፋት አይቻልም። በዓመታቱ ቀን ሀዘነተኛ  በሶስቱ ፀሎቶች  ካዲሽ ያደርጋል።  ከጠዋቱ ፀሎት በቀኑ ፀሎት፤ እንዲሁም በማታ ፀሎት መካከል ባሉት ጊዜያት ለሟቹ ነብስ ይማር ተብሎ ኦሪት ይማራሉ። የሟቹ ስም  ፊደል ካሉበት የምሽና መፅሀፍ  ነበሱ እንዲማር ይማራሉ።  ሌሎች ደግሞ አራት የምሽና ትምህርቶችን፤ የማሰሄት  ሚክቫኦት መጽሐፍ ሰባተኛው ምዕራፍ ላይ ይማራሉ።

ሚንያን ቶቭ፦

አንዳንድ ማህበረሰብ  ክፍል ደግሞ እንደ ሰላሳው ቀን በዓመታቱ በማሰሄት ኪሊም ምዕራፍ 24 ይማራሉ። ይህ ምዕራፍ ደግሞ 17 የምሽና ትምህርቶችን የያዘ እና ተስፋን እና ብርሀን የሚያሳይ ትምህርት ነው።  እያንዳንዱ የምሽና ትምህርት የሚያበቃው ንፁህ ነው ወይንም ንፁህ ናት በሚል ቃል ነው።

የዞዓር ምዕራፎች እና ፆሞች፦

ከትምህርቱ በኋላ ሀዘንተኛው ካዲሽ ያደርጋል።  በስፋራዲም(ኤዶት ሀሚዝራህ) በዓመታቱ  ከዞዓር መጽሐፍ   የተወሰኑ ምዕራፎችን ይማራሉ።  ከኦሪቱ ትምህርት በኋላ በዓመታቱ ማምሻ፤ ቤተሰብ፤ ጓደኞች በአንድ ሆነው ማዕድ ይመገባሉ። ከምግቡ በኋላም ለሟቹ የነበስ ይማር  ፀሎት እና ለሟቹ ቤተሰቦች ቡራኬ ይደረግላቸዋል።  በዚህ ቀን አንዳንድ ሰዎች የሚፆሙ  ሰዎች አሉ። ነገር ግን በዚህ ቀን ስጋ እና ወይን አለመጠጣት  እና ለሰው ልጅ ደስታን የሚሰጡ ነገሮችን አለመጠቀም የተመረጠ ይሆናል።

ካህን በዓመታት ቀን፦

ዓመታቱን የሚያደርገው ወይንም ሟቹ የካህን ዘመደ ከሆነ፤ በዓመታቱ ቀን ወደ መካነ መቃብሩ በመሄድ እና የሟቹን መቃብሩ እስከሚያይበት ቦታ መሄድ አለበት።  ይህም ከቃብሩ አጠገብ ሄዶ እንደቆመ ይቆጠርለታል።

ነበስን ማስታወስ፦

ከሞተበ ቀን ጀምሮ ዓመት ካለፈ፤ የነብስ ማስታወስ በሚደረግበት ቀን ማስታወስ ያስፈልጋል። በተላይ የዚህ ፀሎት ዋና ስም ፡ያስታውስ/ይዝኮር" ይባላል።  ይህ ፀሎት የሚደረገው  በዮም ኪፑር፣ በሲምሀ ቶራ፣ በፋሲካ ሰባተኛው ቀን እና በሻቡኦት በዓል  በፀሎት ቤት ይደረጋል። ይህ ፀሎት ለአባት፣ ለእናት፣ ለባል/ሚስት፣ ለልጅ፣  ለወንድም እና እህት የሚደረገው ኦሪት ከተነበበ በኋላ እና የሙሳፍ(የዕለቱ ተጨማሪ ፀሎት) ከመፀለዩ በፊት ይሆናል። በዚህ ጊዜ በቦታው የሚገኙት ሰዎች የሞተባቸውን ሰው በማስታወስ እና ለነብሳቸው መማሪያ በፍላጎታችን(ያለ ስለት) እነለግሳለን በማለት ስማቸውን ያስጠራሉ።  በውጭ አገር በፋሲካ በስምንተኛው ቀነና በሻቡኦት በሁለተኛው ቀን  ይህም  ፀሎት ይደረጋል። ከፀሎት ፀላዮች መካከል እናት እና አባታቸው በህይወት ካሉ በዚህ ፀሎት ጊዜ ከፀሎት ቤቱ መውጣ አለባቸው።

የኦሪት ትምህርት በዓመታቱ  ቀናት መማር፦

ለሟቹ ነብስ ይማር ተብሎ ኦሪት ይማራሉ። የሚማሩት የኦሪት ትምህርት ደግሞ የሟቹ ስም  ፊደል ካሉበት የምሽና መፅሀፍ  ነው።  እንዲሁም  ሌሎች ደግሞ አራት የምሽና ትምህርቶችን፤ የማሰሄት  ሚክቫኦት መጽሐፍ ሰባተኛው ምዕራፍ ላይ  በ ኑን. በሺን. በሜም. በሄይ (נ. ש. מ. ה. ) ፊደል የሚጀምሩት ምሽንዮት ይማራሉ። ከዚህ በኋላ "እባክ/አና " የሚለውን ፀሎት እና የሟቹ ልጆች ወይንም ቤተዘመዶች ካዲሽ ደራባናን ያደርጋሉ። 

የሟቹን መቃብር መጎብኘት፦

ወደ መካነ መቃብሩ በመሄደ የሟቹን መቃብር ማየት የተለመደ ነው። በዚህ ጊዜ ደግሞ  ከመዝሙር ዳዊት የተወሰኑ ምዕራፎች፤ "አና/እባክህ"፤ እና እግዚአብሔር በምህረት የተሞላ ነው በሚለው ፀሎት የሟቹ ነብስ በፀሎት ትታወሳለች።

የሀዘን ባህላት፦

በዓመታቱ በሰርግ ላይ መሳተፍ የተከለከለ ነው።

የዓመታቱ ቀን

የዓመታቱ ቀን የሚወሰነው በሞተበት ቀን እንጅ በተቀበረበት ቀን አይደለም። ይህም በመጀመሪያ ዓመት ቢሆንም አመታቱ በሞተበት ቀን  ነው መሆን ያለበት። ከሞት በኋላ ከሁለት ቀን በኋል ከተቀበረ፤  አንዳንዶች በመተበት ቀን ዓመታቱ እንዲሆነ የሚወስኑ ሲኖሩ፤ ሌሎች ደግሞ በተቀበረበት ቀን የሚወስኑ አሉ። ነገር ግን በሁለተኛው ዓመት በሞተበት ቀን ይወሰናል።  በኢብራዊያን ካላንደር አንዳንዴ ዓመቱ አስራ ሶስት ወራት የሚሆነበት ጊዜ፤ አስራ ሶሥተኛው ወር በይካቲት ወር ነው የሚሆነው። ስለዚህ የመጀመሪያ የይካቲት ወር እና የሁለተኛው የይካቲት ወር ተብሎ የጠራል። በመሆኑም አንድ ሰው የሞተው በይካቲት ወር  ዓመቱ አስራ ሁለት ወር  በሚሆንበት ጊዜ ከሆነ፤ ዓመታቱ በይካቲ ወር አስራ ሶስትኛ ወር በሚሆንበት ወር ሲወጣ፤ አንዳንዶች በይካቲት በመጀመሪያ ወር አመታቱ የሚፈፅሙ ሰዎች አሉ። ሌሎች ደግሞ በይካቲት በሁለተኛው ወር ያደርጋል። እንዲሁም በሁለቱ ወራት የሚያደርጉ አሉ።

ነብስን ማስታወስ

አንድ ሰው ሲሞት ዓመት እስከ ሚሞላው ድረስ "እግዚአብሔር በምህረት የተሞላ ነው" በሚለው ፀሎት በየሳምንቱ በሰንበት ቀን እና ዓምት ከመሙላት በፊት በሚወለው የሰንበት ቀን የነብስ መታሰቢያ ፀሎት ለሟቹ ይደረግለታል። ለሟቹ ነብስ  እንድትማር የሚደርገው ነገር ግን በስሙ የሚሰጥ ልግስና ነው።  የይቅርታ ፀሎት በማይደረግባቸው ቀናት የነብስ መታሰቢያ ፀሎት አይደረግም።

ከዓመት በኋል- ይዝኮር/ይማር የሚለው ፀሎት፦

እያንዳንዱ የይዝኮር/ይምር የሚለውን ፀሎት ለአባት እና ለእናቱ ወይንም ቤተ ዘመዶች  ሲሞቱ በዮም ኪፑር፣ በሲምሀ ቶራ፣ በሰባተኛው የፋሲካ በዓል እና በሻቡኦት በዓል መፀለይ የተለመደ ነው።

ወደ መቃብሩ መሄድ፦

አንድ ሰው ሲሞት በመጀመሪያ ዓመት ከሰባቱ እና ከሰላሳው የሀዘን ቀናት ውጭ ወደ መቃብሩ መሄድ የተለመደ አይደለም። ነገር ግን ዓመት ከሞላው በኋላ በዓመታቱ ብቻ መሄድ ይቻላል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ  በወሩ መባቻ ፣ በሀኑካ፣ በፑሪም፣ በመጋቢት ወራ እና በሆል ሀሞኤድ ወደ መቃብር የማይሄዱ ሰዎች አሉ።

"እናንተን የፈጥራችሁ" የሚለው ቡርኬ፦(አሸር ያፃር ኤትሄም)፦

አንድ ሰው በሰላሳ ቀናት ውስጥ የይሁዳዊያ መካነ መቃብር ካላየ፤ ወደ መካነ መቃብሩ ሲመጣ የሚቀጥለውን ቡራኬ መባረክ አለበት፦ "ባሩ አታ አዶናይ ኤሎሄኑ ሜለህ ሀኦላም አሸር ያፃር ኤትሄም በዲን፤ ቭኪልኄል ኤትሄም በዲን፤ ቭሄሚት ኤትሄም በዲን፤ ቭዮዴአ ምስፓር ኩልሄም  በዲን፤ አቲድ ለሀህዚር  ቭልሀህዮትሄም በዲን፤ ባሩህ አታ አዶናይ ምሀየ ሀሜቲም።" በማለት ከባረከ በኋላ፤ አታ ጊቦር  ወዘተ የምለውን ከአስራ ስምንቱ ፀሎቶች ሁለተኛውን ቡራኬ እስከመጨረሻው(ሙታትን የሚያነሳ እስከሚለው ድረስ) ይላል።

በሟቹ የስም ፊደላት መሰረት ለመፀልይ ከዚህ ይቻኑ፦