ህግግታ እና ናህላዊ የሀዘን ልምዶች፡

የሰንበት እና የበዓል ቀን ሀዘን፦
በሰንበት ቀን እና በበዓል ቀን የልብስ ቀደዳ ሥነ ሥርአት መፈፀም የተከለከለ ነው። በሆል ሀሞኤድ ግን እንደማህበረተሰቡ ልምድ ይለያያል። "እውነተኛ ፍርድን የሚሰጥ ስለሚለው ቡራኬ ግን ከራብ ሄዶ ማጣራት ያስፈልጋል።
የሰንበት ቀን ሀዘን፦
ከሰባቱ ቀናት አንዱ ቀን ሰንበት ሲሆን፦
የሰንበት ቀን የሀዘኑን ተከታታይነቱን አያቋርጠውም። ስለዚህ የሰንበት ቀን ከሰባቱ የሀዘን ቀናት ይቆጠራል። ነገር ግን በሰንበት ቀን የሀዘን ህግጋትን በትንሹ ይፈፀማል። ይህ ቢደረግም በአደባባይ ወይንም ሰው እያየ የሚደረጉ የሀዘን ህግጋት በሰንበት የተከለከሉ ናቸው።
የሰንበት ዋዜማ
አንድ ሥዓት ከሩቭ ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ከወንበር ወንም ከአግዳሚ ወንበር መቀምጥ እና ሌላ ጫማ መጫማት ይቻላል። እንዲሁም ለሰንበት የተቦረሹ ጫማዎች ወይንም ጫማዎችን መቦረሽ ይችላል።
የሰንበት ልብሶች፦
በሰንበት የሰንበት ልዩ ልብስ መልበስ የተለመደ ነው። የታጠቡ የውስጥ ሱሪዎች እና የጠርጴዛ ልብሶችን መቀየር ይቻላል።
ሰው በሚያየው ሆኔታ የሚደረጉ የሀዘን ጉዳዮች፦
ሰው በማያየው ሆኔታ የሚደረጉ የሀዘን ጉዳዮች በሰንበትም መደርገ አለባቸው። ስለዚህ በሰንበት ቀን በታጠብ፤ ኦሪት መማር እና የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከለ ነው።
ወደ ፀሎት ቤት የመሄድ ልምድ ያላቸው ሰዎች- ፀሎቶች፦
አንድ ሀዘንተኛ ከቤቱ ወጦ ወድ ፀሎት ቤት መሄድ ይፈቀድለታል። ነገር ግን ሀዘንተኛው ከሚንሀ በ በፊት ሆዱ የሚለውን ፀሎት አይልም። እንዲሁም በሰንበት መቀበያ ፀሎት " በሰንበት ቀን የምስጋና መዝሙር" የሚለውን ብቻ ይላል። እንዲሁም "በማ ማድልኪም" የሚለውን አይልም። በአንዳድን ቦታዎች ሀዘንተኛው ሁሉን የሚልበት ቦታዎች አሉ። በሀዘነተኞች ቤት የሰንበትን የጠዋቱን ፀሎት ከፀለዩ "ምሀሪው አባት" የሚለውን ፀሎት ይጨመራል። ነገር ግን በቀኑ ፀሎት አኒ ትፊላቲ የሚለውን ሳይል፤ ፅድቃትሃ ፄደክ የሚለው ይላል። እንዲሁም ባርሂ ናፍሽ የሚለውን በክርምት፤ ፕርኬ አቮት በበጋ አይልም።
የኦሪት ንባብ
በሰንበት ቀን ሀዘንተኛው ኦሪት ማንበብ አይችልም። ምክንያቱም የሀዘን ጊዜ ገደብ እስካላለቀ ድረስ ማንበ አይችልም። ሀዘንተኛ ወደ ኦሪት መቅረብ አይችልም። ካህን ወይንም ሌዊ ቢሆንም ወደ ኦሪት መውጣት አይችልም። ነገር ግን ኦሪቱን ማውጣት እና ማስገባት ይችላል። ከዚህ በኋላ የሟቹን ነበስ በማስታወስ እግዚአብሔር በምህረት የተሞላ ነው የሚለውን ፀሎት ይነበባል።በሰንበት ቀን የወሩ መባቻ ቢሆንም የሟቹን ነብሱ ማስታወስ ይፈቀዳል። ሀዘንተኛው ሽታይም ሚክራ እና ኤሀድ ትርጉም ማንበብ እንደሚችል ሲፈቅዱ፤ ሌሎች ደግሞ ራሽ ከሚባለ ሊቃውንት የኦሪቱን በተነተነው ፍች ጋር ሁሌ የሚማር ከሆነ፤ መማር ይችላል። ከፀሎት ቤት እስከሚመለስ ሳይበላ መቆየት አለበት።
ማዕድ
ሀዘንተኛው በሰንበት ማታ ሻሎም አለሄም የሚለውን መዝሙር ከፀሎት ቤት ሲመለሱ የሚሉትን መዝሙር አይልም። በሰንበት ማታ ልጆችን ሁሌ የሚባርክ ከሆነ፤ በዚህ ሰንበት መባርክ አይችልም።
የሰንበት ቀን ሲወጣ፦
ሰንበት እንደወጣ ሀዘንተኛው የእግዚአብሄር ስም ሳይጠራ "ሀማብዲል ቤን ኮዴሽ ልሆል ይላል" ። ከዚህ በኋላ ልብሱን ወደ አዘቦት ቀን የሚለብሰውን ይቀይራል። አንዳንድ ቦታ "ይሂ ኖአም" የሚለውን የፀሎት ክፍል አይሉትም። ከፀሎት በሁኋ መዝሙር ዳዊት ምዕራፍ 17 ይነበባል።
ሀብዳላ-የሰንበት መሸኛ፦
የሰንበትን መሸኛ ፀሎት ሀዘንተኛው የሚለው ከሆነ "ሂኔ ኤል የሹ አቲ" የሚለው የፀሎት ክፍ አይለውም። ቡራኬዎችን ብቻ ነው የሚባርክ። እንዲሁም ስለጥሩ ሽታ ይባርካል።
በበዓላት እና በዓመቱ ወራት የሀዘን ሥነ-ሥርዓት፦
የሀዘን ሥነ-ሥርዓት በበዓላት መቋረጥ፦
አንድ ሰው ቤተሰቡ ከሞተበት እና ከበዓሉ በፊት ከተቀበረ ፤ እንዲሁም የሀዘን ህግጋትን ለተወሰነ ጊዜ በዓሉ ከመግባቱ በፊት ከፈፀመ፤ በዓሉ ሲገባ የሀዘኑን ሥነ-ሥርዓት ያቋርጠዋል። ሀዘኑን የሚያቋርጡት በዓላት ፋሲካ፤ ሻቡኦት እና የዳስ በዓል፤ ብርሀነ ሰረቀ እና አስተሰርዮ ናቸው።
የበዓል ዋዜማ፦
በበዓሉ ዋዜማ ከሥዓት በኋላ ልብሱን ማጠብ ይችላል። ነገር ግን የሚለብሰው ማታ ብቻ መሆን አለበት። አንዳዶች ደግሞ በዓሉ ከመግባቱ በፊት የሚያጥቡ አሉ። ገላን በሙቅ ዉሃ መታጠብ ከቀኑ ፀሎት በኋላ ወይንም በዓሉ ሊገባ ሲል። በፋሲካ በዓል ከሥዓት በኋላ ሁሉንም ነገር ማድረግ ይቻላል። ምክንያቱም እንደበዓል ስለሚቆጠር እው። እንዲሁም በአስተሰርዮ በዓል የቀኑን ፀሎት ከመፀለዩ በፊት መታጠብ እና መቅቤ መጥለም ይቻላል። ሌላው የቀኑን ፀሎት አንድ ሀዘንተኛ በፀሎት ቤት ሄዶ መፀለይ ይችላል። እንዲሁም የመጨረሻውን ማዕድ ከወንበር ተቀምጦ በመገብ ይችላል።
ሥርዓተ ቀብር በሆል ሀሞኤድ፦
የቀብሩ ሥነ ሥር ዓት ለማካሄድ ከመውጣቱ በፊት ሀዘንተኛዎች የበዓሉን ልብስ አውልቀው በአዘቦት የሚለበስ ልብስ መልበስ ያስፈልጋቸዋል። ከቀብሩ ሥነ ሥርዓት በኋላ በረድፍ ይቆማል። ሀዘንተኞች ጫማቸውን አያወልቁም። ከቀብሩ በኋላ የሀዘኑን ልብስ አውልቀው የበዓል ልብስ ይለብሳሉ።
የልብስ ቀደዳ ሥነ ሥር ዓት፦
አንዳንድ ማህበረሰቦች ሁሉም ቤተ ዘመድ ለሀዘን ምልክት ልብሳቸውን በሆል ሀሞኤድ ይሚቀዱ አሉ። እንዲሁም ሌላ ማህበረሰብ ደግም በሆል ሀሞኤድ ልብሳቸውን የሚቀዱት እናት ወይንም አባት ሲሞቱ ብቻ ነው። ሌሎች ቤተሰቦች ግን በዓሉ ካልፈ በኋላ ሥነ ሥርዓቱ ይፈፅማሉ። ነገር ግን ሁሉም ቤተ ዘመዶች "እግዚአብሔር እውነተኛ ፍርድን የሚሰጥ" የሚለውን ቡራኬ በሆል ሀሞኤድ ይባርካሉ።
ከቀብር በኋላ የሚደርግ ማዕድ(ሥኡዳት ሀብራአ)፦
በበዓል ቀን ከቀብር በኋላ የሚደረገውን ማዕድ መመግብ አይቻልም። ነገር ግን በሆል ሀሞኤድ ከወንበር በመቀመጥ መመገብ ይቻላል። ነገር ግን የተቀቀለ እንቁላል መመግብ የተከለከለ ነው። ስለዚህ በማዕዱ ላይ የሚቀርቡ ምግቦች እንደኬክ የመሳሰሉ መሆን አለባቸው። አንዳንድ ማህበረሰብ እናት ወይንም አባት ሲሞት ብቻ ይህም ማዕድ የሚፈፅሙ። ለተቀሩት ቤተ ዘምድ ግን አይፈፅሙም።
ሀዘን
የሀዘን ህግጋት በግልፅ በበዓላት ቀን አይፈፀሙም። ነገር ግን በስውር ይደረጋል። ለምሳሌ ገላን መታጠብ እና የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከለ ነው። በመጨረሻው የበዓል ምሽት በሙቅ ዉሃ ገላን መታጠብ፤ እንዲሁም የታጠቡ ልብሶች መልበስ የተፈቀደ ነው።
ሰላሳ የሀዘን ቀናት
የበዓላት ቀናት ለሰላሳ የሀዘን ቀናት ይቆጠራሉ። ስለዚህ ሰላሳው የሚያበቃው ከተቀበረበት ቀን ንስቶ ተቆጥሮ ሲሆን፤ በመካከል በዓል ቢሆን የበዓላቱ ቀናት ለሰላሳው ይቆጠራሉ። የሀዘን ህግጋት በሰላሳዎቹ ቀናት እና በሆል ሀሞኤድ ይፈፀማሉ።
ሻማ ማብራት
በሰባቱ የሀዘን ቀናት ሻማ ማብራት የተለመደ ሲሆን፤ በሆል ሀሞድ ና በበዓል ቀናት ሻምው መብራት አለበት። ነገር ግን ሰባቱን የሀዘን ቀናት በአሉ ስለሚያቋርጠው ሀዘንተኞች አይቀመጡም።
በዓሉ ሲወታ፦
በዓሉ ሲወጣ፤ ሰባቱን የሀዘን ቀናት ለመቀጠል በሀዘንተኞች ድንኳን ሀዘንተኞች ሰባተኛው ቀን እስከሚያል ይቀመጣሉ።
ፑሪም
የፑሪም በዓል እንደሌሎች በዓላት የሀዘን ቀናትን አያቋርጥም። ነገር ግን በአደባባይ (በግልፅ) የሀዘንም ምልክቶች አይደረጉም። ይህም በይካቲት 14 እና 15 ቀናት ነው። ይህ ቢሆንም በስውር የሚደረጉ የሀዘን ህግጋት ግን ይፈፀማሉ። ይህ ማለት ገላን መታጠብ፤ ኦሪት መማር እና የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከሉ ናቸው። የፑሪም ቀናት ከሰባቱ የሀዘን ቀናት ይቆጠራሉ። የሀዘን ልብስን በበዓል ልብስ መቀየር ይቻላል። ነገር ግን ደስታውን መቀነስ እና በልክ ማድረግ ያስፈልጋል። ሀዘንተኞች ከተቀመጡበት ቤት አስር ሰው ሞልተው የሚፀልዩ ከሆነ እና የአስቴር የብራና መጽሐፍ የሚያነቡ ከሆነ፤ ከዚያው ያደርጋሉ፡፡ አለብዚያ ግን ሰው ከታጣ ወደ ፀሎት ቤት ሄዶ መፀለይ እና ማንበብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ አስር ሰው በቀን ከሀዘንተኞች ቤት መሙላት የማይችል ከሆነ፤ በፑሪም ቀን ወደ ፀሎት ቤት ሄዶ መፀለይ ይችላል። በፑሪም የልብስ ቀደዳ ሥነ-ሥርዓት ይደረጋል። ከቀብሩ በኋልም የሀዘን ልብሳቸውን አውልቀው የበዓል ልብስ ይቀይራሉ። እንዲሁም ከቀብር በኋላ የሚደረገውን ማዕድ ይመገባሉ። ነገር ግን የተቀቀለ እንቁላል በማዕዱ መብላት አይቻልም። ሀዘንተኞች በፑሪም ማዕድ እና ለድሀዎች የሚላከውን ስጦታ(ሚሽሎዋህ ማኖት) መፈፀም ግዴታ አለባቸው። ይህ ቢሆንም ለሀዘንተኛ እስከ ሰላሳ ቀናት ድረስ ስጦታ መላክ አይቻልም። እንዲሁም ሀዘንተኞች እናት ወይንም አባት ከሞተባቸው እስከ አስራ ሁለት ወር ስጦታ(ሚሽሎዋህ ማኖት)አይልኩም።
የሀምሌ ዘጠኝ ቀን ፆም፦
በሀምሌ ዘጠኝ ፆም ሀዘንተኞች በማታው ፀሎት ወደ ፀሎት ቤት መሄድ ይችላሉ። እንዲሁም በቀን እስከ ሀዘን ፀሎት እስከሚደረግ ድረስ መሄድ ይችላሉ። እንዲሁም በሰባቱ የሀዘን ቀናት ከሆኑ ወደ ኦሪት መቅረብ ይችላል።
ሀዘንተኞች በሰባቱ የሀዘን ቀናት፦
አጠቃላይ መረጃ፦
ሟቹ ከተቀበረ በኋላ አኔኑት የሚለው ህግጋት ሲያበቃ፤ ሰባቱ የሀዘን፤ ሰላሳ ቀና እና አስራ ሁለት ወር መቁጥረ ይጀመራል። ሟቹ የተቀበረው ፀሀይ እንደገባች ከሆነ፤ ያን ቀን የመጀመሪያው የሀዘን ቀን እንዲሆን መቁጠር ይቻላል። የሟቹ ቅርብ ዘምድ ሥርዓተ ቀብሩ እና በቀብሩ ላይ በከተማው ካልተገኘ ፤ የሀዘን ቀናት መቼ እንደሚጀምር የኦሪት ሊቃውንት መጠይቅ አለበት።
አንድ ሰው ሀዘንተኛ የሚባለው ለየትኛው ዘመዱ ነው
አንድ ሰው ሀዘንተኛ ነው የሚባለው/ይምትባለው፦ 1_ወላጆች እልጆች፣ ለወንድም እና ለእህቱ፣ ለባል/ለሚስት ናቸው። ሰላሳ ቀን ያልሞላው ህፃን ሲሞት የሀዘን ህግጋትን መፈፀም አይስፈልግም።
2_በህግጋቱ መሰረት ለሚቀጥሉት ለስምንት ቤተ ዘመድ ፦ለአባት፣ ለእናት፣ ለወንድም፣ ለእህት፣ ለወንድ ልጅ፣ ለሴት ልጅ፣ ለሚስት እና ለባል ማዘን ያስፈልጋል፡
3_የሀዘኑ ጊዜ ገደብ፦ ሰላሳ ቀናት ሲሆኑ፤ ለአባት እና ለእናት ግን አመቱን በሙሉ ይታዘናል።
ሀዘንተኛው የተከለከላቸው ነገሮች
አንድ ሰው ከላይ የተጠቀሱት ቤተ ዘምዶቹ ሲሞቱ፤ ለሰባት ቀናት ያህል ስራ መስራት፣ ገላውን መታጠብ፣ መኳኳል፣ ጫማ መጫማት፣ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም፣ ኦሪት መማር፣ ሰውን ሰላም ማለት፣ ልብሱን ማጠብ እና መልበስ፣ ከወንበር ላይ መቀምጥ፣ ፀጉሩን መስተካከል እና ፂሙን መላጨት፣ ከቤቱ መውጣት እና በደስታ ላይ መካፈል የተከለከለ ነው።
ሥራ መስራት
በሰባቱ የሀዘን ቀናት ስራ መስራት ወይንም የንግድ እቃዎችን ማንቀሳቀስ አይፈቀድም። ነገር ግን ለቤት ስራ ለምሳሌ ምግብ ለማብሰል፣ እቃ ማጠብ እና ቤቱን ማፅዳት የተፈቀደ ነው። አንድ ሀዘንተኛ ሱቅ ወይንም የሆነ የንግድ ስራ ቦታ ካለው፤ ግዴታ ሰባቱን ቀናት በሙሉ መዘጋት አለባቸው። ነገር ግን ስራ ወይንም ሱቁ የጋራ ከሆነ እና ያ የሚጋራው ሰው ስለሚዘጋ የሚከስር ከሆነ፤ ከኦሪት ሊቅ ከሆነ ሰው ጋር መወያየት እና ምን ማድረግ እንዳለበት ምክር መቀብል ያስፈልጋል።
ገላን መታጠብ እና መኳኳል፦
ሀዘንተኞች ሰውነታቸውን በሙቅ ሆነ በቀዝቃዛ ዉሃ መታጠብ የተከለከለ ነው። ነገር ግን እጃቸውን እና ፊታቸውን በቀዝቃዛ ዉሃ መታጠብ ይችላሉ። ሀዘንተኛው የጤና ችግር ካለው፤ ከሀኪሙ ጋር በመወያየት በሙቅ ዉሃ መታጠብ ይቻላል። አንዲ ሴት የወር አበባ ከጨረሰች በኋል እና በሰባቱ የሀዘን ቀናት የመጥለሚያ ጊዜ ከሆነ፤ መጥለም አትችልም። ሰባቱን የንፅህና ቀናት ለመቁጠር በሙቅ ዉሃ በሚያስፈልጉት የሰውነት አካላቷ መታጠብ ትችላለች። ከዚህ በተጨማሪ ለደስታ ሀዘንተኛው ሰውነቱን በወይራ ዛይት ወይንም በቅባት ነገር ማሸት የተከለከለ ነው። ነገር ግን ወዙን ለማስለቀ ወይንም ለህክምና ከሆነ ይቻላል። አንዲት ሴት በሰላሳ የሀዘን ቀናት እራሷን ማስጌጥ አትችልም። ነገር ግን የተዳረችው ከሰባቱ የሀዘን ቀናት በኋላ ከሆነ፤ እራሷን ማስጌጥ ትችላለች። እንዲሁም አንዲት ሙሽራ በተዳረች ወር እስከሚሞላት ወይንም ባል ለማግባት ከባሏ ጋር ትውውቅ ላይ ከሆነች በሰባቱ ቀናትም እራሷን ማስጌጥ ትችላለች።
ጫማ መጫማት፦
ከቆዳ የተሰሩ ጫማዎችን መልበስ የተከለከለ ነው። ነገር ግን ቆንጥር ጫማ ወይንም ከፕላስቲክ የተሰራ መሆን አለበት።
የግብረ- ስጋ ግንኙነት መፈፀም:-
አንድ ሀዘንተኛ በሰባቱ የሀዘን ቀናት የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈፀም የተከለከለ ነው። ይህም ሰንበትን ያጠቃልላል። እንዲሁም ማቀፍ እና አብሮ በአንድ አልጋ መተኛት የተከለከለ ነው።
የኦሪት ትምህርት፦
ኦሪት ማንበብ እና ማንኛውም የኦሪት ትምህርት(ታልሙድ፣ ምሽና፣ መጽሐፈ ቅዱስ) መማር በሰባቱ የሀዘን ቀናት የተከለከለ ነው። ይህም በሰንበት ቀን ጭምር ነው። ነገር ግን የእዮብ እና ኤሀ መፅሀፍ ማንበብ ይቻላል። እንዲሁም የሀዘን ህግጋትን እና ትምህርታዊ የኦሪት ክፍሎችን መማር ይቻላል። የዳዊትን መዝሙር በይቀኑ የሚል ከሆነ፤ እንደ ፀሎት እና በልመና አድርጎ ማንበብ ይችላል።
ሰላምታ ማቅረብ፦
በሰባቱ የሀዘን ቀናት ለማንኛውም ሰው ሰላምታ ማቅረብ አይቻልም። አንድ ሰው ሀዘንተኛ መሆኑ ሲያውቅ በሶስቱ የመጀመሪያዎች ቀን ሰላምታ ከጠየቀው ሀዘንተኛው ሳይመልስ፤ ሀዘንተኛ ስለሆነ መመለስ እንደተከለከለ ማስረዳት አለበት። ከሶስት ቀና በኋላ ግን መመለስ ይችላል። ሀዘንተኛው ለጓደኛ መልካም ነገር እንደሚያሟላለት እና እንኳን ደስ አለህ ማለት ይችላል። እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ለሀዘንተኛው ይህ ማለት ይችላሉ። ሌላው እጃቸውን ዘርግተው መልካም ነገር ሊመኙለት ይችላሉ። ለሀዘንተኛው እስከ ሰላሳ ቀናት ስጦታ መላክ የተከለከለ ነው። ወላጆቹ ለሙቱበት ሀዘንተኛ ደግም እስከ አንድ ዓመት መላክ የተከለከለ ነው።
ልብስ ማጠብ እና መልበስ፦
ሀዘንተኛዎች ልብሳቸውን በሰባቱ የሀዘን ቀናት ማጠብ እና መልበስ አይችሉም። እንዲሁም ሌሎች የሀዘንተኞችን ባይለብሱት ልብስ ማጠብ ሆነ መተኮስ አይችሉም። ነገር ግን ለልብስ ማጠቢያ ቦታ መርዶውን ሳይሰማ ከላከው ልብሱ ማጠብ ይችላሉ። ነገር ግን የታጠቡ ልብሶችን በሰባቱ የሀዘን ቀናት መልበስ የተከለከለ ነው። ይህም ልብሶች ከመርዶው በፊት ቢታጠቡም። የሀዘንተኞች ቤተሰቦች(ሀዘንተኛ ያልሆኑ ሰዎች- የዝምድና ርቀት ያላቸው ቤተሰቦች) ልብሳቸውን ማጠብ እና መልበስ ይችላሉ።
ከወንበር ላይ መቀመጥ፦
ከወንበር እና አግዳሚ ወንበር ላይ መቀመጥ አይቻልም። በሀዘን ጊዜ ከሠላሳ ሴንቲ ሜትር በታች በሆነ ወንበር ላይ ነው መቀመጥ የሚቻለው። ሀዘንተኛው ግዴታ ሁሌ መቀመጥ የለበትም። መቀመጥ ግዴታ ያለበት እርሱን ሊያፅናኑት ሰዎች ሲመጡ ብቻ ነው።
ፀጉር መሰተካከል እና ፂም መላጨት፦
አንድ ሀዘንተኛ ሰው እስከ ሰላሳ ቀናት ፀጉሩን መስተካከል እና ፂሙን መላጨት፤ እንዲሁም የእግሩን እና የጁን ጠፍር በጠፍር መቁረጫ መቁረጥ አይፈቀድለትም። ነገር ግን በጥርሱ ወይንም በእጁ መቁረጥ ይፈቀዳል። እንዲሁም በጥፍር መቁረቻ ጀምሮ በእጁ መጨረስ ይችላል።
ከቤት መውጣት፦
አንድ ሀዘንተኛ ከቤቱ መውታት የለበትም። ይህም ት ዕዛዝ ለመፈፀም ቢሆንም የተከለከለ ነው። ወላጆቹ ከሞቱ ደግሞ ዓመት እስከ ሚሞላው ድረስ በልጁ የግርዛት ሥነ- ሥር ዓት እና በልጁ ሰርግ በሰባቱ የሀዘን ቀናት ጭምር መሳተፍ ይችላል። ከቤቱ አስር ሰው ከለለ እና ፀሎት ቤት ሄዶ ፀሎት ለመፀለይ መሄድ እና ካዲሽ ማድረግ ይፈቀዳል። አንድ ሀዘንተኛ ከሀዘኑ ቤት መታና የምያችል ክሆነ ማት ሰው ሁሉ ከተና በኋላ ወደ ቤቱ ሄዶ መተናት ይችላል።
በደስታ መሳተፍ፦
አንድ ሀዘንተኛ ሰላሳ ቀን እስከሚሆን በደስታ መሳተፍ አይችልም። በአባት እና በእናት ሀዘን ያለ ሰው ለዓመት ያህል በደስታ መሳተፍ አይችልም። ነገር ግን በልጁ የግርዛት ሥነ- ሥርዓት እና በልጁ ሰርግ በሰባቱ የሀዘን ቀናት ጭምር መሳተፍ ይችላል። አንዳንድ አጋታሚዎች በደስታ የሚሳተፍበት ጊዜ ሎኖር ይችላል። ነገ ግን የኦሪት ሊቅ ከሆነ ሰው ጋር መወያየት እና መጠየቅ ያስፈልጋል። ሌላው ሀዘንተኛው የጨርቃ ቡርኬ ከሰባቱ ቀናት በኋል ለማለት የሚያስችለው ጊዜ ካለ፤ በሰባቱ ቀናት ማለት የለበትም። ጊዜው የሚያልፍ ከሆነ የጨርቃን ቡራኬም ማለት ይችላል። ሰላም ለእናንተ ይሁን(ከቡራኬው በኋል ሻሎም አለሄም የሚለውን ቡራኬ) ማለት አይችልም። እንዲሁም የቢርካት ሀጎሜል ቡራኬ እና ሽሄያኑ የሚለውን ቡራኬ አዲስ ፍሬ ሲያገኝ እና ቢርካት ቭቶቭ ሀሚቲቭ የሚሉትን ቡራኬዎች መባረክ ይችላል።
የሩቅ መርዶ፦
የቅርብ መርዶ
አንድ ሰው ዘመዱ መሞቱ ሳይሰማ ከሰባቱ የሀዘን ቀናት በኋላ ወይንም በሰላሰኛው ቀን ከሰማ የቅርብ መርዶ ይባላል። ስለዚህ ይህ ሰው እንደሰማ ሰባት እና ሰላሳ የሀዘን ቀናት መፈፀም አለበት።
የሩቅ መርዶ፦
አንድ ሰው ዘመዱ መሞቱ ከሰላሳ ቀን በኋላ ወይንም በሞተ በሰላሳ አንደኛው ቀን ከሰማ፤ ይህ የሩቅ መርዱ ይባላል። ስለዚህ ይህን ሲሰማ ሁሉ የሀዘን ህግጋት አይፈፅምም። ለተወሰን ሥዓት ብቻ የሀዘን ምልክት ያደርጋል። ለምሳሌ ጫማውን ማውለቅ ወይንም ዝቅ ካለ ወንበር መቀመጥ። ከዚህ በኋላ በመነሳት እና ጫማውን መጫማት ይችላል። አባቱ ወይንም እናቱ ከሞተች ግን የልብስ ቀደዳ ሥነ ሥርዓት መፈፀም አለብት። ነገር ግን ማዕድ መፈፀም አያስፈልገውም። ከዚህ በተጨማሪ ለሰውየው መርዶ የደረሰ በስንበት ቀን ወይንም በበዓል ቀን ከሆነ፤ የሀዘን ህግጋት ወይንም ምልክት አይደርግም። ስለዚህ ሲሰማ የዘሀን ምልክት ካልፈፀመ ግዴት እንደገና መፈፀም አለበት። እንዲሁም የአባት እና የእናት ከሆነ አስራ ሁለት ወር የሀዘንን ህግጋት መፈፀም አለበት።
መርዶ የማርዳት ግዴታ፦
አንድ ሰው ለሆነ ሰው ዘመዱ ከሞተ ግዴታ ዘመዱ ለሞተው ሰው ግዴታ ማርዳት የለበትም። በመሆኑም እስከ አልሰሙ ድረስ የሀዘን ህግጋትን አይፈፅሙም ማለት ነው። ስለዚህ ለሰርግ ማዕድ ወይንም በደስታ እንዲካፈል መጥራት ይቻላል። ነገር ግን እነርሱ ስለሞተው ሰውዬ ቢጠይቅ ግዴታ እውነቱን መናገር ያስፈልጋል። ከወላጆ አንዱ ሲሞት ለወንድ ልጆች ተሎ ይነገራቸዋል። ምክንያቱ ካዲሽ እንዲያደርጉ ነው። በበዓላት እና በፑሪም የበዓሉን ደስታ እንዳይቋረጥ መርዶ ማስረዳት የተከለከለ ነው።