ህግግታ እና ናህላዊ የሀዘን ልምዶች፡

ሰባት የሀዘን ቀና መጀመሪያ እና ከቀብር በሁላ የሚደርግ ማዕድ፦
ሰባቱ የሀዘን ቀናት መጀመሪያ፦
ቀብሩ ከተፈፀመ በኋላ ሀዘንተኞች ወደ ሟቹ ቤት ይሄዳሉ።ከዚያ ሰባቱን የሀዘን ቀናት ይቆጥራሉ። ከዚህ ጊዘ ጀመሮ በሀዘን ህግጋት ደንቦች መሰረት መከተል ይጀመራሉ። ሰባቱን ቀናት ሟቹ ሲኖርበት በነበረው ቤት ሁሉም ሀዘንተኞች መቀመጥ አስፈላጊ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀመሮ የሰባቱ የሀዘን ቀናት ህግጋት ይጀምራሉ።
በሀዘን ጊዜ የተከለከሉ የበህትውና እና የከተለያዩ ነገሮች መቆጠብ
ኦሪት አንድን ሰው ሌላው በልቡ እንዲቀርፅ ታዟል። ነገ ግን የአንድ የሞተ ሰው ለማስታወስ በአካሉ ላይ የሆነ ጉድለት እንዳያደርስ ይከለክላል። ምክንያቱም ሀዘኑ የህይወት ጣዕምናን መቀነስ ክልክል ነው። በኦሪት ነብሳችን እንድናስጨንቅ ከታዘዝነው እና ደስታ ከሚሰጡን ነገሮች መቆጠብ(መታተብ፣ መኳኳክል፣ ፀጉር መስተካከል፣ የቆዳ ጫምዎችን መጫማት እና በተዝናና ሆኔታ መቀመጥ እና የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም) ከዚህ ውጭ አንድ ሀዘንተኛ ተጨማሪ ነገር በሀዘኑ ምክንያት መጨመር የተከለከለ ነው። ሀዘንተኞች በሰባቱ ቀና ህብረተሰቡ በፍቅር አቅፏቸው ይሰነብታል። እነርሱም ሊያስተዛዝኗቸ ለሚመጡት ሀዘናቸውን ያካፍላሉ። በዚህ ጊዜ ስልሟቹ መልካም ስራ መናገራ እና ሀዘንተኞችም እራሳቸውን እንዲያፅናኑ መግፋፋት እና በህይወት እንደድሮው መኖር እግዴታ እንዳለባቸው መገፋፋት ያስፈልጋል።
ሻማ ማብራት፡
ሀዘንተኞች በተቀመጡበት ቤት ወይንም ሟቹ በነበረበት ቤት ሻማ ለነብስ ይማር ተብሎ ማብራት የተለመደ ነው። ይህ ሻማም ሰባቱን ቀናት ሁሉ መብራት አለበት። መብራቱ ሰንበትን እና በዓላትን ያጠቃልላል።
በየሀዘንተኞች ቤት ሆኔታ፦
ከሰባቱ የሀዘን ቀናት የመጀመሪያው ቀን የሟቹ ቤተሰብ በአንድ የሚሆኑበት ቀን ሲሆን፤ ከቀብሩ የሚመለሱ ሀዘንተኞች ጫማቸውን አውልቀ ከፕላስቲክ(ቆንጥር) ጫማ ይጫማሉ። ባዶ እግርን መቆየትም ይቻላል። ነገር ግን ካሉስ ማድረግ ያስፈልጋል።
ሀዘንተኞች ከትንሽ ወንበር(ኩርሳ) ላይ ይቀመጣሉ። ምክኛቱም ሀዘናቸውን ለመግለፅ ነው፡፡ በአንዳንድ ማህበረሰብ ከመሬት ይቀመጣሉ።
ከቀብር በኋላ የሚደርግ ማዕድ፦
ከቀብር በኋላ ለሀዘንተኞች የሚቀርበው ማዕድ በጎረቤቶች አማካኝነት እንደሚዘጋጅ የተለመደ ነው። ወዲያው እንድተመለሱ ይህ ማዕድ(ሥኡዳት ሀብራአ) ይቀርብላቸዋል። ይህ ማዕድ የሚቀርበው ከሀዘንተኞች መካከል አንድ ባለሆነ ሰው ነው።ወይንም ቤተ ዘመድ ባልሆነ ሰው መቅረብ አለበት። ስለዚህ ሀዘንተኞች ይህን ማዕድ ማዘገጃት ሆነ ማቅረብ የተከለከለ ነው። የቀብሩ ሥነ-ሥራዓት የተካሄደው አርብ ከሆነ ወይንም በበዓልም ሽት ከሆነ ይህን ማዕድ አይፈፀምም። ሥኡዳት ሀብራ የሚባለው ማዕድ ከምስር፣ ከተቀቀለ እንቁላል የተሰራ መሆነ አለበት። ለዚህ ምግብ የሚቀርቡ ነገሮ ድንቡቡል መሆን አለባቸው። ይህም ህይወት እና ሞትን ያመለክታል። ምክንያቱም በአለም ላይ ሁሌ ስለሚከሰቱ ነው። አንዱ ይሞታል ሌው ይወለዳል፣ አንዲ ይነሳል፤ ሌላው ይወድቃል። ስለዚህ ይህ የህዘን ቀን አልፎ እንደገና የደስታ ቀን ይመጣል።
ክፍት በር
የአንድን ሀዘንተኛ ቤት የሚያስታውስው ነገር ቢኖር የቤቱ በር ሰባቱን ቀን ተከፍቶ ይቆያል። ይህም ሀዘንተኞችን ሊያፅናኑ የሚመጡትን ሰዎች ወደ ቤት መግባት እንደሚችሉ እና ሀዘንተኞችን ማስተዛዘን እንደሚችሉ ለመግለፅ ነው። በሩ ክፍት ሆኖ መቆየቱ ከሰባቱ የሀዘን ቀናት ህግጋት ጋር አብሮ ይመለከታል። በዚህ ጊዜ ሀዘንተኛው ከቦታ መቀመጥ አለብት፡፡ ያለምክንያት ከቦታ ቦታ መዘዋወር የለበትም። ከዚህ በተጨማሪ ሀዘንተኛውን ሀሳብ ለማስረሳት መዝጊያውን ክፍት ሆኖ ይቀመጣል። ይህ ደግሞ ሀዘንተኛው የሚያስተዛዝኑ ሰዎች ሲመጡ በየጊዜ ለመክፈት ከመነሳት ይረዳል፡፡
ለምን መስታወቶች ይሸፈናሉ
ሀዘንተኞች በሚቀመጡበት ቤት መስታወቶችን፤ ከግድግዳው የተሰቀሉት ፎቶወችን እና ቴሌቪዚያው ይሸፈናሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው በእግዚአብሄር ምስል ስለተፈጠረ እና አዳም ሀጢያት ከስራ በኋላ "ከአፈር ነው እና የተሰራህ ወደ አፈር ትመለሳለህ" ተብሎ ስለ ተወሰነ ነው።" ስለዚህ አዳም በስራው ኃጢአት በፈጣሪው ምስል የተፈጠረው፤ እንደገና ያ ምስል ወደ አፈር ስለሚለወጥ ነው። ስለዚህ በሀዘንተኞች ቤት ውስጥ መልክን የሚይሳዩ ነገሮችን መሸፈን ያስፈልጋል። ሌላው ምክንያት ደግሞ ሀዘንተኞች በመስታወት መልካቸውን ቢመለከቱ ፤ በሀዘን ላይ እያሉ ለመኳኳል የቆሙ ወይንም የቀረቡ እንዳይመስሉ ነው።
በሀዘን ጊዜ እንዴት ሰላም ይባላል
ሀዘንተኞችን ለማፅናናት የሚመጡ ሰዎች ከሀዘንተኞች ቤት ሲገቡ እና ሲወጡ ሰላም አይሉም። እንዲሁም እጃቸውን ለሰላምታ መዘርጋት ቢከለከልም፤ በአንዳንድ ማህበረሰብ የተለመደ ልምድ አለ። ሰላም በማለት ፈንታ "ከጺዮን ሀዘንተኞች ጋር እግዚአብሄር ያፅናችሁ" ይባላል። ይህም የግል ሀዘንን ቤተ መቅደሱ በምፍረሱ ካለው ህዝባዊ ሀዘን ጋር በአንድ በማድረግ እንዲህ ይባላል። ነገር ግን በሰባቱ ቀናት በመካከል ሰንበት ከሆነ ለሀዘንተኞች ሰንበት ሰላም ማለት ይቻላል። እነርሱም ሰንበት ሰላም በማለት መመለስ አለባቸው።
ለሰው ክብር ሲባል መቆም፦
አንድ ሀዘንተኛ ለተከበረ ሰው መቆም አይሳፈልገውም። ነገር ግን ኦሪት ሲያልፍ ካየ ወይም ካመጡ መቆም ግዴታ አለበት። እንዲሁም ሀዘንተኛው ሲቆም ተቀመጥ ማለት ክልክል ነው።
ፀሎት፦
አስር ሰዎች አሰባስቦ ከሟቹ ቤት ፀሎት ማካሄድ ትልቅ ትዕዛዝ ነው። ነገር ግን ከሞተበት ቦታ መፀለይ ካልተቻለ፤ ሰውየው የሞተው ሆስፒታል ውስጥ ከሆነ፤ ሀዘንተኞች ሰባት ቀን ከሚቀመጡበት ቦታ መፀለይ ያስፈልጋል። ሀዘንተኞች በመጀመሪያው የሀዘን ቀን ትፍሊ አያስሩም። ሀዘንተኞች ከወጋግራ(አሙድ) ፊት በመቆም ፀሎት ይፀልያሉ። እንዲሁም ለአስራ አንድ ወር ያህል ካዲሽ ያደርጋሉ። በሀዘንተኞች ቤት የይቅርታ ፀሎት እና "የመዝሙራን አለቃ" የሚለውን ፀሎት አይደረገም። የካሀናት የህዝብ ቡርኬ በሀዘንተኞች ቤት አይባላም። እንዲሁም በወሩ መባቻ የምስጋና ፀሎት(ሀሌል) አይፀለይም። ከጠዋቱ ፀሎት በኋላ እና ከምሽቱ ፀሎት በኋላ መዝሙር ዳዊት ምዕራፍ 49 ይነበባል። የይቅርታ ፀሎት በማይደረግባቸው ቀናት የዳዊት መዝሙር 16 ይነበባል።
የሚሽንዮት ትምህርት፦
ለሟቹ የነብሱ እንዲማር ሰባቱን ቀናት በሙሉ ሚሽንዮት(ኦሪት) ይማራሉ። እንዲሁም አንዳንድ ሰዎች በሟቹ ስም መሰረት የተዘጋጁ ሚሽንዮት ይማራሉ። ከዚህ በኋላ ደግሞ 4 ሚሽንዮት በማሰሄት ሚክቫኦት ምዕራፍ 7 ይማራሉ። ከዚህ በኋላ "አና" የሚባል ፀሎት ይደረጋል። ሀዘንተኞች ኦሪትን መማር አይችሉም። ነገር ግን ከሌሎች መስማት እና የሊቃውንት ካዲሽ ማለት ይችላሉ።
ከሀዘንተኞች ቤት የሆነ ነገር መውሰድ፦
የተወሰኑ ማህበርሰብ ከሀዘንተኞች ቤት እቃ ሆነ ማንኛውም ነገር በሰባቱ የሀዘን ቀናት መውሰድ ያልተለመደ ነገር ነው። ምክንያቱም መጥፎ መንፈስ ከሀዘንተኞች ቤት ስለሚገኝ እው።
ኦሪት ማንበብ
ከሀዘንተኞች ቤት ኦሪት አምጦ ሁለት ጊዜ ቢያንስ ማንበብ ይቻላል። እንዳንዶች ደግሞ ሶስት ጊዜ አምጠው እንድያነቡ የሚያድርጉ አሉ። ሀዘንተኛ ወደ ኦሪት መቅረብ አይችልም። ካህን ወይንም ሌዊ ቢሆንም ወደ ኦሪት መውጣት አይችሉም። ነገር ግን ኦሪቱን ማውጣት እና ማስገባት ይችላል። እንዲሁም ኦሪትን እንዲያነሳ እና እንዲጠቀልል ሊጋበዝ ይችላል። ከዚህ በኋላ ኦሪቱን እንደያዘ ከወንበሩ መቀመጥ ይችላል።
ሀዘንተኞችን ማፅናናት፦
ሀዘንተኞችን ማስተዛዘን ትልቅ ትዕዛዝ እና የታመመ ሰው ጠይቆ ከሚቀበለው ትዕዛዝ ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም ሐዘን በሕይወት ላሉት እና ለሞቱት የምህረት ሀዘን ስለሆነ ነው። የሀዘን አፅናኝዎች ሀዘንተኛው መናገር እስከሚጀምር ድረስ መናገር አይችሉም፡፡ ሀዘንተኞችን ጥሩ ነገሮችን በመናገር ማወያየት ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ለማስተዛዘን ሲመጣ በሚገባበት እና በሚወጣበት ጊዜ “ሠላም” አይልም፡፡ ሲወጣ ግን ከጺዮን ሀዘንተኞች ጋር እግዚአብሄር ያፅናችሁ በማለት ይወጣል፡፡ እነርሱም አሜን በማለት ይመልሳሉ፡፡ ነገር ኝ ግዴታ አይደለም፡፡
ሰባተኛው የሀዘን ቀን፦
በሰባተኛው ቀን ጠዋት፤ የጠዋቱን ፀሎት ከፀለዩ በሆሏ፤ ሀዘንተኞች ይቀመጣሉ። ለመፀለይ የመጡት ሰዎች "ውዶች ቁሙ" በማለት ያዟቸዋል። የስፋራዲም ማህበረሰብ ደግሞ " እግዚአብሄር የዘላለም ብርሀን ይሆናልና የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሀይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም አይቋረጥም። እናት ልጅዋን እንደምታፅናና እንዲሁ አፅናናችኋለሁ፤ በየሩሳሌም ውስጥም ትፅናናላችሁ።" የሚሉትን ሁለት ስንኞች ያነባሉ። ከዚህ በኋላ ሀዘንተኞች በቀብሩ ሥነ- ሥርዓት የቀደዱትን ልብስ(ለሰባት ቀን የለበሱትን ልብስ) ቀይረው ሌላ ልብስ(አዲስ መሆን የለበትም) ይለብሳሉ። የሚያስተዛዝነው ሰው ከለለ እና በሰንበት ሀዘንጠኛን ማፅናናት አይስፈልግም። ምክንያቱን በሰንበት የሀዘን ትዕዛዝ መፈፀም አይቻልም። ከፀሎት በኋላ ከፀሎት ቤቱ ከወጡበት ጊዜ ጀመሮ የሀዘኑ ሥነ ሥርዓት ያበቃል።
ሌላው የተለመደ ነገ ቢኖር እና ግዴታ ያልሆነ ነገር፦ የሟቹን ቃብር በሰባተኛው ቀን በመሄድ ማየት ነው። ከቃብሩ አጠገብ ሰባት የዳዊት መዝሙር ምዕራፎችን ይነበባሉ፦ መዝሙር 33፣ 16፣ 17፥ 72፣ 91፣ 104፣ 130፡ ከዚህ በኋላ የሟቹን ስም የሚይዙትን ስንኞች ይነበባሉ። የይቅርታ ፀሎት በሚባልበት ቀን "አና በኮዋህ" የሚለውን ፀሎት ይፀለያል። አስር ሰው ካለ የሙት ልጅ ካዲሽ ይደርጋል። እንዲሁም "እግዚአብሔር በምሕረት የተሞላ ነው" የሚለውን ፀሎት ይፀለያል።
ሰባተኛው ቀን ዳሰ እና በፋሲካ በዓል በአምስቱ ቀናት ከዋለ፤ ወደ መካነ መቃብሩ በመሄድ መቃብሩን ማየት አይቻልም። ስለዚህ በዓሉ እስከ ሚያልፍ ድረስ መቆየት ያስፈልጋል። የይቅርታ ፀሎት በማይደረግባቸው ቀናት(የወሩ መባቻ፣ 33 የኦሜር ቆጠራ፣ ጥር 15፣ ሀምሌ 15 እና በመጋቢት ወር ) በእነዚህ ቀናት የሟቹን ቀብር ሄዶ ማየት የተለመደ አይደለም። በሀኑካ እና በፑሪም ወደ መካነ መቃብሩ ሄዶ ቀብሩን ለማየት፤ በማህበረስቡ ባህል ጋር የተያያዘ ነው። ቀብሩ ከጎበኙ በኋላ ሀዘንተኞች ወደሚፈልጉት ስራ መሄድ ይችላሉ። ከዚህ ጊዜ አንስቶ የ 30 ቀናት ሀዘን ይጀምራል።