በሞት አጋጣሚ የሚያገልግሉ መርሆዎች


በአንድ አባውራ ውስጥ አንዱ የአባውራው ክፍል  ሲሞት፤  ይህ ሞት መራራ እና ጥልቅ ሀዘን ያመጣል።  ስለዚህ የሀይፋ መካነ መቃብር ሄብራት ካዲሻ  የቤተሰቡን ሀዘን በመካፈል እና የቃብሩ ሥነ- ሥርዓት በተሟላ ሆኔታ ቤተሰቡ እንዲያከናውን የሚችለውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል። ሥነ-ሥርዓቱን በተሟላ ሆኔታ ለማከናውን የሚረዳችሁ መረጃ ከዚህ በታች ተፅፏል።

የቀብር ፍቃድ ማዘጋጀት፡

የመካነ መቃብሩ ኩባንያ፤ አንድ ሰው ያለፍቃድ የመቅበር ሀላፊነት የለውም። ስለዚህ የሟቹ  ቤተሰቦች ይህን ፍቃድ ማሰገኘት ይኖርባቸዋል።   አንድ ሰው በሆስፒታል ሲሞት፤ ቤተሰቦቹ  ወደ ታካሚዎች  መቀበያ ቢሮ በመሄድ የቃብሩን ፋቃድ መቀበል አለባቸው። አንደ ሰው በቤት ወይንም  በአረጋውያን  መጦሪያ ቤት ውስጥ ከሞተ፤  የቃብር ፍቃድ  የሚፈቅደው  አካል  በወረዳው የጤና ሚንስቴር  (ረሆብ ፓልያም 15፣ 19ኛ ፎቅ ላይ) የሚገኘው  የቀብር ፍቃድ ሀላፊ ክፍል ሲሆን፤  የሟቹ ቤተሰቦች ወደዚህ ቦታ የሚቀጥሉትን ሰነዶች በመያዝ  ሄደው  ፍቃዱን መቀበል ያስፈልጋል።

  1. የሟቹን መታወቂያ
  2. መሞቱን የወሰነው ሀኪም  መልዕክት (መግለጫ)
  3. የእስራኤል ፖሊስ ሟቹ እንዲቀበር  ፍቃድ  ለማውጣት ተቃውሞ  እንደለለው እና  የፖሊስ መኮነን  የፈረመበት ፍቃድ  

 

አስከሬኑን ወደ መካነ መቃብሩ ማሳለፍ/የአስከሬን ማስቀመቻ ፍሪጅ፡

የመካነ መቃብሩ ኩባንያ አስከሬኑን ወደ መካነ መቃብሩ ያለገንዝብ  የማስተላለ ግዴታ አለበት።  ይህ የሚሆነ ሟቹ በኩባንያው ሀላፊነት ስር  ሲገኝ  (መካነ መቃብሩ በሚገኝበት ከተማ) እና በስራ ሥ ዓት ነው።

የስራ  ሥዓት እና ታዳሚዎችን የመቀበያ ቀናት፡

ከእሁድ- ሀሙስ፦ ከ 8፡00-17፡00

*አንድ ሰው ሲሞት፤ ካለበት ቦታ ወደአስፈላጊ ቦታ ለመውስድ በበነገታው ጠዋት በ *0120  ከ 8፡00-15፡00 መደወል ይቻላል።

አርብ እና በብዓላት ዋዜማ  8፡00-13፡00

*አርብ ከ 13፡00 ሥዓት አንስቶ እስከ እሁድ  ጠዋት በ 8፡00 ሥዓት ድረስ ሰው ሲሞት በ *0120 በመደወል አስከሬን ወደአስፈላጊው ቦታ ለሚወስደው አካል ማስታወቅ ያስፈልጋል።

ከመቀበሩ  ከአንድ ቀን በፊት ወደ መካነ መቃብሩ አስከሬኑንን ማስተላለፍ እና አስከሬን የሚቀመጥበት ፍሪጀር  ለማስቀመጥ የሚከናወነው ድርጊት  እና በቀብሩ ቀን ሟቹን ለመቅበር የሚደረገው ሄደት ሁሉ ያልምንም ክፍያ ነው።   ነገር ግን ሟቹ የሚቀበረው በበነጋታው ከሆነ እና የኩባንያው የስራ ሥዓት ውጭ ከሆነ፤  አስከሬኑን በመካነ መቃብሩ  በሚገኘው የአስከሬን ማስቀመጫ  በሞተበት ቀን ለማስቀመጥ ከተፈለገ፤ የቢቱዋህ ልኦሚ ድርጀት በተመነው ተመን መሰረት የመካነ መቃብሩ ኩባንያ ገንዘብ  ያስከፍላል።

አንድ ሰው በሄይፋ ከሞተ እና ቃብሩ የሚከናወነው ከሄይፋ ውጭ ከሆነ፤ ይህ ድርጀት አስከሬኑን ቀብሩ ወደ ሚከናውንበት መካነ መቃብሩ ማስተላልፍ ግዴታ የለበትም። ነገር ግን ይህ ድርጅት አስከሬኑን ካስተላለፈ  የቢቱዋህ ልኦሚ በተመነ ተመን መሰረት ክፍያ ያስከፍላል።

ቀብርን በተመለከተ፣ ለቢቱዋህ ልኦሚ ድህረ ገፅ ከዚህ ይጫኑ፦

 

ለቀብሩ ቅደመ ዝግጅት ማከናወን፡

ቀብሩ የሚከናወንበት ቀን እና ሟቹ የሚቀበርበትን ቦታ ለመወሰን፤ የሟቹ ቤተሰቦች ወይንም ተወካዮች ወደ የሄይፋ መካነ መቃብር  መስሪያ ቤት  የመቅበሪያ ፍቃድ በመያዝ መጦ  መረጃ መቀብል እና የቃብሩ ምርጫዎችን  መቀበል የቤተሰቡ ሀላፊ ይሆናል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግልቶች ኩባንያው ያለ ገንዝብ የመስጠት ሀላፊነት አለበት

ቴል ረጌብ መካነ መቃብር- ሳነድሪን የቃብር ቦታ

መቃብሩን መቆፈር እና ማልበስ

አስከሬኑን ማፅዳት እና መከፈን

የቃብሩን ሥነ-ሥርዓት ማካሄድ፦ ቃብሩን የሚያከናወነው ክፍል እና ፀሎት የሚያደርግ ሀላፊ

ከላይ እንደተጠቀሰው፤ አስከሬኑን ከሞተበት  ቦታ ወደ ሚቀበርበት መካነ መቃብር ማስተላለፍ።

ያለ ክፍያ  ቀብር 

የእስራኤል አገር ኖሪ ሰው ሲሞት፤ በሚኖርበት ከተማ ይቀበራል።

የእስራኤል አገር ኖሪ  ሰው በውጭ አገር ሲሞት፤ በቢቱውህ ልኦሚ የእስራኤል አገር ኖሪ እንደሆነ ከታወቀ በሚኖርበት ከተማ ይቀበራል።

የሄብራት ካዲሻ ድርጅት ገንዘብ ማስከፍል የሚችለው መቼ ነው? 

በአገሪቱ በተወሰነው የታሪፍ ህግ መሰረት በሕይወት እያሉ የቃብር  ቦታ ለመግዛት ታሪፉ ከቦታ ቦታ ይለያያል፡

በልዩ ፍቃድ የተወሰነ የቃብር ቦታ( በቢቱሀ ልኦሚ የተፈቀደ የቃብር ቦታ)።

በተዘጋ የመቃብር ቤት (ከቦታ እጥረት የተነሳ የተዘጋ የመቃብር ቦታ)

አንድ እስራኤል አገር የመኖር ፍቃድ ያለው ሰው ሲሞት፤ ቤተሰቡ ከሚኖርበት ቦታ ትተው ከሌላ ቦታ ለመቅበር ሲወስኑ።

በእነዚህ  አጋጣሚውሚዎች ድርጅቱ የገንዘብ ክፍያ መጠየቅ ይችላል።

 

በሄይፋ የመካነ መቃብር ኩባንያ መስሪያ ቤት የተዘጋጀ የቀብር  የቀረጥ ዋጋ፡

የሳንሄድሪን የቀብር ሥነ-ሥርዓት- አይከፈልም።

የማክፔላ የቃብር ሥነ-ሥርዓት በቴል ረጌቭ - ማቹ የሚቀበረው  ከመሬት ወይንም ከተሰራ ግንብ ውስጥ ከሆነ - ለሟቹ አይከፈልም። ነገር ግን ለቤተሰቡ(ለልጁ/ ለሚስቱ) የሀይማኖት መስሪያ ቤቱ ባወጣው ታሪፍ መሰረት ይከፈላል።

የሳዴ የቃብ ሥነ-ሥርዓት በቴል ረጌቭ- ቦታው ልዩ ከሆነ ይከፈላል።

የማክፔላ የቃብር / የሳዴ ሥነ-ሥርዓት ሳዴ የሆሹዋ በተዘጋ መካነ መቃብር/ልዩ -ይከፈላል።

የማክፔላ የቃብር / የሳዴ ሥነ-ሥርዓት በሆፍ ሀካርሜል መካነ መቃብር- የተዘጋ ስለሆነ ይከፈላል።

ከቃብር ላይ(ከአውልት ላይ) የሚፈፀም የቀብር ሥነ-ሥርዓት  1,800 ብር ያስከፍላል። ነገር ግን ልዩ አውልት አፍርሶ እንደገና ለመግጠም ብር ያስጨምራል።

ከዚህ በላይ የተፃፈው መረጃዎች  በአጭሩ  እና በአጠቃላይ ስለሆነ፤ የበለጠ  መረጃ ለመቀበል  ወደ መካነ መቃብሩ ኩባንያ መስሪያ ቤት( በሄርፄል ጎዳና 63 ሄይፋ) በመሄድ ወይንም በስልክ በመደውል(04-8688000) ሰፊው እና ሙሉ መረጃ መቀበል ይቻላል።

መስሪያ ቤቱ ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጥበት ቀናት እና ጊዜያት፡

ከእሁድ እስከ ሀሙስ ከ 8፡00-17፡00

አርብ እና በብዓላት ዋዜማ  8፡00-13፡00

በሀኑካ በዓላት ቀናት ከ 8፡00-15:30

በፑሪም እና በቲሻ በአብ(ሀምሌ 9 ፆም) ከ 8፡00-12፡00

በሆል ሀሞኤድ(በፍሲካ እና በዳስ በዓል በአምስቱ ቀናት)  ከ 8፡00-12:30

በእስራኤል የነፃነት በዓል(ዮም አፅማኡት) ከ  8፡00-12:30

ከ 17፡00 በኋል  የቀብር ቀን ለመወሰን ለምሽት ተጠባባቂዎች መደወል ይቻላል፦

አቶ ሽሙኤል አድለር- 053-3123312 እና ለአቶ አብርሀም ሀስካልሶን(መልዕክት(ሜሴጅ)  መላክ ይቻላል)-053-5237048